You are currently viewing የነቀምቴ ገነተ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ታሠሩ፤ ቤተ ክርስቲያኑም ወረራ ተፈጸመበት። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     የካቲት 20 ቀን 2015 ዓ/ም…

የነቀምቴ ገነተ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ታሠሩ፤ ቤተ ክርስቲያኑም ወረራ ተፈጸመበት። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 20 ቀን 2015 ዓ/ም…

የነቀምቴ ገነተ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ታሠሩ፤ ቤተ ክርስቲያኑም ወረራ ተፈጸመበት። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 20 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት የሚገኘው የነቀምቴ ገነተ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በሕገ ወጡ ቡድን ወረራ የተፈጸመበት ሲሆን የደብሩ አስተዳዳሪ አባ ወልደ ገብርኤል በቀለ በሕገ ወጡ ቡድን ድጋፍ እየሰጡ በሚገኙት የጸጥታ ኃይሎች ታሥረዋል። አስተዳዳሪው የታሠሩበት ምክንያትም ሕገ ወጡ ቡድን ቤተ ክርስቲያኑን ለቅቀው እንዲወጡ ቢጠይቃቸውም ፈቃደኛ ባለመሆናቸው እንደሆነ ተገልጿል። ከአስተዳዳሪው በተጨማሪም በደብሩ ካህናት እንዲሁም ወጣቶች ላይ አፈሳና እስር እንደተፈጸም ነው የተነገረው። የጸጥታ ኃይሎች ጠዋት ላይ ተኩስ ከፍተው እንደነበር የገለጹት የመረጃ ምንጮቻችን ኦርቶዶክሳውያኑ ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት እንደደረሰም አስረድተዋል። ከተጎጂዎች መካከል ሀብታሙ ደቢሳ የተባለ ዘማሪ እንደሚገኝበት የተገለጸ ሲሆን በነበረው ሁካታ ምክንያት ሥርዓተ ቅዳሴ መታጎሉንም ተናግረዋል። ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል (ተሚማ) እንደዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply