የነዳጅ ማደያዎች ወደ አገልግሎት ሊመለሱ ነው!ግጭት ተከስቶባቸው በነበሩ አካባቢዎች የነዳጅ ማደያዎች ስራ አቋርጠው መቆየታቸው ይታወሳል፡፡በአሁኑ ወቅት ግን በአጭር ጊዜ ዳግም ወደ አገልግሎት…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/slLJulYXHmYRq9lBQ-rO67tiV_BbaEcyFuMaQEH6o9ocfATNpKn9Ui8z5fnKzIxh4zWZhs22QJiDyj5zncsXrVpPcgMl8rufiWNeilZrIkKdrZlPY9tSu5UA5Lrdn1WWLvrQhOBrb9GvcES9wYws7IREDZsrvUllQCIZvKfIwetEtgkJSCnhmQ4CxqJCKTSKlgK-sXBuTmTd_V1uifcYNQFjzsAEuARu-Bf5Ao5vUpU0mUje9FHQVESPl0SrhCdrnoiV4FUVzpsgcOgMsdj83I_bg-pOwsVR1E2PYNEBLZIGyrBaFVLgi5dl3LfDC3tJa8wdNncAZJXg49sJGJQIaA.jpg

የነዳጅ ማደያዎች ወደ አገልግሎት ሊመለሱ ነው!

ግጭት ተከስቶባቸው በነበሩ አካባቢዎች የነዳጅ ማደያዎች ስራ አቋርጠው መቆየታቸው ይታወሳል፡፡

በአሁኑ ወቅት ግን በአጭር ጊዜ ዳግም ወደ አገልግሎት ለመመለስ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታውቋል።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ እንደገለጹት÷ ለሰብዓዊ ድጋፍ የሚቀርበው ነዳጅ ሳይስተጓጎል ተደራሽ እንዲሆን ከማድረግ ባሻገር የነዳጅ ማደያዎች ተጠግነው ዳግም አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡

እስካሁን ባለው ሂደትም በሃራና ቆቦ አካባቢዎች በሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች ነዳጅ የማቅረቡ ሥራ መጀመሩን ገልጸው÷ አላማጣ በሚገኙ ማደያዎች ከሚቀጥለው ሣምንት ጀምሮ ነዳጅ ለማቅረብ እየተሠራ መሆኑን አብራርተዋል።

በማይጸብሪ ፣ በአብዓላና አፍዴራ የሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች ቶሎ ተጠግነው በቅርቡ ወደ ሥራ ለማስገባት እየተሠራ መሆኑን መናገራቸውን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል፡፡

እስከ ሽረ ያሉትን የነዳጅ ማደያዎች መረጃ የማጥራት ሥራ መከናወኑን ጠቁመው÷ በቀጣይ እስከ መቀሌ ያሉትን የነዳጅ ማደያዎች ፈትሾና ጉዳት የደረሰባቸውን ጠግኖ ወደ ሥራ ለማስገባት ቅድመ ዝግጅት ተጠናቋል ብለዋል፡፡

እስከ ሽረ ያሉት አካባቢዎች በቀጣይ ሙሉ ለሙሉ ነዳጅ እንዲያገኙ የነዳጅ ታንከሮችንና የነዳጅ መቅጃዎችን መልሶ የመጠገን ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ህዳር 24 ቀን 2015 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply