የነዳጅ ምርት ሽያጭ ላይ የሰዓት ገደብ

ኢትዮጵያ የነዳጅ ማደያ ጣቢያዎችን የሥራ ሰዓት ገደበች፡፡ ገደቡ የተጣለው በነዳጅ ምርቶች ዝውውር፣ ስርጭት እና ግብይት ላይ ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ እንደሆነ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡በመሆኑም በአዲስ አበባ የሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች ከጥቅምት 27 ጀምሮ ከጧቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት ድረስ ብቻ እንዲሰሩ ገደብ ተጥሎባቸዋል፡፡
በአንፃሩ በክልሎች የሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች ከጧቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1 ሰዓት የሚሰሩ ይሆናል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply