የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ክለሳ መደረጉ ተገለፀ

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ክለሳ መደረጉ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 30፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ክለሳ መደረጉን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ሚኒስቴሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው የዘርፉ ተሳታፊዎች ትርፍ ህዳግ እንዲሻሻል መንግስት በሰጠው ውሳኔ መሰረት የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋን በመከለስ አዲስ ዋጋ ተዘጋጅቷል፡፡
በዚህም መሰረት ፡-
ቤንዚን በሊትር 23 ብር ከ67 ሳንቲም
ኤታኖል ድብልቅ ቤንዚን በሊትር 23 ብር ከ27 ሳንቲም
ነጭ ናፍጣ በሊትር 21 ብር ከ03 ሳንቲም
ኬሮሲን በሊትር 21 ብር ከ03 ሳንቲም
ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 18 ብር ከ17 ሳንቲም
የአውሮፕላን ነዳጅ በሊትር 32 ብር ከ76 ሳንቲም መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በአዲስ አበባ ከጥር 1 እስከ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ተግባራዊ ይደረጋል ነው የተባለው፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ክለሳ መደረጉ ተገለፀ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply