የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል ተባለ።ከዛሬ ጀምሮ የሁሉም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንዲቀጥል መወሰኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል…

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል ተባለ።

ከዛሬ ጀምሮ የሁሉም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንዲቀጥል መወሰኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ታኅሣስ 20 ቀን 2014 ዓ.ም ባደረገው 3ኛ መደበኛ ስብሰባ ባስተላለፈው የነዳጅ ውጤቶች የዋጋ ግንባታ የአፈጻጸም ውሳኔ መሠረት የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በየጊዜው እየተከለሰ ሥራ ላይ እንዲውል ሲደረግ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

በዚህም መሰረት ከግንቦት 28 ቀን 2016ዓ.ም ማለትም ከዛሬ ጀምሮ የሁሉም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በስራ ላይ በነበረበት ዋጋ እንዲቀጥል መወሰኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcas

Source: Link to the Post

Leave a Reply