የነዳጅ ድጎማን በህገወጥ መንገድ ሲጠቀሙ የነበሩ 40 ሺህ ተሽከርካሪዎች ከስርአቱ እንዲወጡ ተደርጓል ተባለየታለመለት የነዳጅ ድጎማን ላልተገባ ዓላማ ሲጠቀሙ የነበሩ 40 ሺህ ተሽከርካሪዎች ከ…

የነዳጅ ድጎማን በህገወጥ መንገድ ሲጠቀሙ የነበሩ 40 ሺህ ተሽከርካሪዎች ከስርአቱ እንዲወጡ ተደርጓል ተባለ

የታለመለት የነዳጅ ድጎማን ላልተገባ ዓላማ ሲጠቀሙ የነበሩ 40 ሺህ ተሽከርካሪዎች ከድጎማ ስርዓቱ እንዲወጡና ዕዳ እንዲከፍሉ መደረጉን የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ ገለጹ።

ከዚህም ባለፈ መንግስት ለህዝብ ተጠቃሚነት እንዲሰሩ ሲሰጣቸው የነበረውን የድጎማ ገንዘብ በዕዳ መልኩ መልሰው እንዲከፍሉ መደረጉን አስረድተዋል።

ሚኒስትሯ ይህን ያሉት የመንግሥት የ2016 የመጀመሪያ የሩብ ዓመት አፈጻጸም በተገመገመበት ወቅት ሲሆን የግምገማው ተሳታፊዎች “ድጎማው ሃብታሞችን እንጂ ድሃውን ማህበረሰብ በሚፈለገው ልክ አልጠቀመም” ሲሉ ተችተዋል። መንግሥት የችግሩን ጥልቀት ምን ያህል ያውቀዋል፤ ምንስ እርምጃ ወስዷል ሲሉም ጠይቀዋል።

የፕላንና ልማት ሚኒስትሯ ዶክተር ፍጹም በሰጡት ምላሽ፤ መንግስት የድጎማ ስርዓቱን ሲዘረጋ አቅም የሌላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች በብዙሃን ትራንስፖርት ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ መሆኑን አንስተዋል።

ህዳር 21 ቀን 2016 ዓ.ም
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply