የኑሮ ውድነት ላለፉት 16 ዓመታት በእጥፍ ጨምሯል ተባለ፡፡

የኑሮ ውድነቱ መናር ሸማቾች ሸምተው ለማደር በእጅጉ ፈተና እንደሆነባቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ተናገሩ፡፡

በሃገሪቱ የኑሮ ውድነቱ እንዲባባስ የዋጋ ግሽበቱን የሚያመጡ መንስኤዎችን መለየት እንደሚያስፈልግም አስታውቀዋል፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ ልዩ ስብሰባ በመካሄድ ላይ ሲሆን በተደጋጋሚ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድም ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ከቀረቡላቸው ጥያቄዎች መካከል የኑሮ ውድነት መባባስ አሳሳቢ እየሆነ እንደመጣ ተጠይቀዋል፡፡

ለዚህ ምላሽ የሰጡት ዶ/ር አብይ፣ የአቅርቦትና ፍላጎት ያለመጣጣም ፤በአቅርቦት ሰንሰለቱ ያለው ሳንካ ፤የአምራቾች ምርትን ያለአግባብ መያዝና ሌሎችም ችግሮች ተዳምረው ለዜጎች የኑሮ ውድነት መባባስ ምክንያት እንደሆኑ አንስተዋል፡፡

እስካሁን መንግስት ይህንን የኑሮ ውድነት ለማሻሻል ምግብ ነክ የሆኑ ሸቀጦች ከውጪ እንዲገቡ ማድረግ፤ለሸማቹ በቂ የግብይት ሰንሰለትን መፍጠር፤የግሉ ሴክተር ተጨማሪ ታክስ ሳይከፍል እንደ ስንዴ፤ዘይት፤የህፃናት ምግብ ከውጪ እንዲገቡ መደረጉን በማንሳት እነዚህ ሙከራዎችም የዋጋ ግሽበቱን ባይቀንሰውም መሻሻል አሳይቷል ብለዋል፡፡

ለዚህ የኑሮ ውድነት መናር ዘለቂታዊ መፍትሄ ነው የሚያስፈልገው ያሉት ዶ/ር አብይ ኢትዮጲያዊያን መሬትን አርሰን ምርትን ማሳደግ ፤የበጋ ስንዴ ውጤትን ማሳደግ፤ ኩታ ገጠም ልማትን ማሳደግ፤ አረንጓዴ ገፅታን ወይንም ዛፍ የመትከል ልማድን ማሳደግ፤ 9 በመቶ ድርሻ ወጪ ብቻ የሚደረግበትን የግብርና ምርትን ማሳደግ፤ ዘርፉን በቴክኖሎጂ፤በፋይናንስ፤መደገፍ፤የሃገር ውስጥ የምግብ ፍጆታን በሃገር ውስጥ እንዲመረት ማድረግ ፤ እንደሚገባና ሌሎችንም አማራጮች በማስፋት የኑሮ ውድነቱ መባባስ ለመቀነስ እንደሚቻል አመላክተዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችንቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

በየዉልሰዉ ገዝሙ

ሰኔ 28 ቀን 2013 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply