የኒዥር ዋነኛ የፖለቲካ መንበረ ስልጣን ተቀናቃኝ ማህማኔ ኡስማኔ የሀገሪቷን ምርጫ በጠባብ ብልጫ ማሸነፋቸውን አውጀዋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም ከፍተኛ ብጥብጥ በሀገሪቷ የተለያዩ ከተሞች እየተፈጠረ ነው የሚሉ ዘገባዎች እየወጡ ነው፡፡የቀድሞው የሀገሪቷ የውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ማህመድ ባዙም 55 ነጥብ 7 በመቶ ድምፅ በማግኘት ማሸነፋቸው ሲገለፅ ዋነኛ ተቀናቃኛቸው በ44 ነጥብ 2 በመቶ ድምፅ ተሸንፈዋል፡፡

ታዲያ ተሸናፊው ተቀናቃኝ የድምፅ ስርቆት ተፈፅሟል በማለት ራሳቸውን አሽናፊ አድርገው በመናገራቸው በሀገሪቱ ሁከትና ግጭት እየተፈጠረ ነው፡፡የሀገሪቷ ብሔራዊ የምርጫ ኮሚሽን ውጤቱ ህጋዊና ፍትሐዊ ነው እያለ ቢሟገትም የፀጥታ ኃይሎች ከተሸናፊው የፖለቲካ ፓርቲ መሪ ደጋፊዎች ጋር ግብ ግብ እንደገጠሙ እየተነገረ ነው፡፡

ዘገባው፡- የአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ነው

ቀን 19/06/2013

አሐዱ ራድዮ 94.3

Source: Link to the Post

Leave a Reply