የናይል ተፋሰስ ትብብር ቋሚ ህጋዊ እና ተቋማዊ ማእቀፍ ሊዘጋጅለት ይገባል ሲሉ የውሃና ኢነርጂ ሚንስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ተናገሩ፡፡

ሚንስትሩ ኢትዮጵያ የናይል ተፋሰስ ትብብርን እውን ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት እያደረገች እንደምትገኝም ገልጸዋል፡፡

በቡሩንዲ ቡጁምቡራ እየተካሄደ በሚገኘው 25ተኛው የናይል ቀን እየተሳተፉ የሚገኙት የውሃና ኢነርጂ ሚንስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ፣ ኢትዮጵያ የናይል ተፋሰስ ትብብርን እውን ለማድረግ እያደረገች ያለችውን ከፍተኛ ጥረት አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

የናይል ቤዚን ኢኒሼቲቭ ለሩብ ክፍለ-ዘመን የዘለቀው ጉዞው ሲገመገም፣ በ25 ዓመታት ጥሩ ውጤቶችን እንዳመጣ የተናገሩት ሚንስትሩ፤በተለይ በተወሰኑ የተፋሰሱ አካባቢዎች የልማት ስራዎችን ማከናወን መቻሉን ጠቅሰዋል፡፡

ምንምን እንኳን ህጋዊ አካልነት ባያገኝም፤ በአባል ሀገራት መካከል የውውይት ፎረሞችን በመፍጠር፣ የአቅም ግንባታ ስራዎችን በማከናወን፤ ስለተፋሰሱ ግንዛቤ በማስጨበጥና የተፋሰሱ የእውቀት ምንጭ በመሆን ጥሩ እንቅስቃሴ ማድረጉም ገልጸዋል፡፡

ሚኒስትሩ ቋሚ ህጋዊና ተቋማዊ ማእቀፍ በፍጹም ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ እንዳልሆን አንስተው፤ ቋሚ ህጋዊ እና ተቋማዊ ማእቀፍ የናይል ተፋሰስ አባል ሀገራት አስተዋጽኦና ተሳትፎ ቋሚና ወጥ እንዲሆንና በአባል ሀገራት የመንግስታት መቀያየር ምክንያት ተጽእኖ ውስጥ የማይወድቅ ጠንካራ ተቋም ለመፍጠር ያግዛል ብለዋል፡፡

ይህ የብርዮ በልዩ በዓል አባል ሀገራት የናይል ተፋሰስ የትብብር ማእቀፍ ስምምነትን በማጽደቅ ወደፊት ለመራመድ ወሳኝ ሰዓት መሆኑን ገልጸው፤ ኢትዮጵያም የናይል ተፋሰስ ትብብርን እውን ለማድረግ ግንባርቀደምነቷን አጠናክራ እንደምትቀጥል ማረጋገጣቸውን የሚንስቴሩ ኮሚንኬሽን የላከልን መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

የካቲት 14 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply