የኔልሰን ማንዴላ ፋውንዴሽን የዶናልድ ትራምፕን ሽንፈት በደስታ አሳለፈ፡፡ፋውንዴሽኑ ትራምፕ በመሸነፋቸው የተሰማውን ደስታ በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበረ እንደሚገኝ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ዶናልድ ትራም…

የኔልሰን ማንዴላ ፋውንዴሽን የዶናልድ ትራምፕን ሽንፈት በደስታ አሳለፈ፡፡

ፋውንዴሽኑ ትራምፕ በመሸነፋቸው የተሰማውን ደስታ በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበረ እንደሚገኝ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ዶናልድ ትራምፕ ወደ ስልጣን ከመጡበት ጊዜ አንስቶ ዘረኝነትን እያንጸባረቁ ነበር ሲልም ነው ፋውንዴሽኑ ያስታወቀው፡፡

አሁን ጆ ባይደን ትራምፕ የፈጠሩትን ክፍተት ይጠግኑታልም ብሏል ፋውንዴሽኑ፡፡

ዘረኝነት እና የጾታ አድሎ በአለማችን እንዲስፋፋ ዶናልድ ትራምፕ ሲጥር ነበር የስልጣን ጊዜውን ያሳለፈው ሲል ፋውንዴሽኑ በፕሬዝዳንቱ ላይ ትችቱን የሰነዘረው፡፡

እንደ ሌሎቹ የአለም ሀገራት ሁሉ እኛም የትራምፕ ሽንፈትን በደስታ እያከበርን ነው ብሏል ፋውንዴሽኑ ባወጣው መግለጫ፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply