የኔቶ አዛዥ የሩሲያና የኔቶ ስብሰባ በጥር ወር እንዲካሄድ ይፈልጋሉ

30 ሃገሮች አባል የሆኑበት የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን አባል አገሮች ወይም የኔቶ ዋና አዛዥ ጄንስ ስቶልትንበርግ፣ በሚቀጥለው ወር ይደረጋል በተባለው የኔቶ ሩሲያ ተወካዮች ስብሰባ ላይ ሩሲያ የምትገኝ መሆኗን ማረጋገጣቸው ተገለጸ፡፡

ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ አንድ የኔቶ ቃል አቀባይ ትንናት እሁድ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት በኔቶና በሩሲያ መካከል የሚደረገው ውይይት እንዲቀጥል ከሩሲያ ጋር ግንኙነት መደረጉንና ስምምነቱ መገኘቱን ተናግረዋል፡፡

ምዕራባውያን ሞስኮ ሠራዊቷን ወደ ዩክሬን እያስጠጋችና ደጋፊዎችዋ የሆኑ የዩክሬን ተገንጣዮችን በመርዳት በአካባቢው አደጋን ደቅናለች ሲሉ ይከሷታል፡፡ 

ሩሲያም በኔቶ አማካይነት ምዕራባውያን አገሮች ወታደራዊ ይዞታቸውን ወደ ሩሲያ ድንበርና አጎራባች አገሮች እያሰፋፉ ነው በማለት ያላትን ስጋት ትገልጣለች፡፡

ሩሲያ ኔቶ ወታደራዊ መስፋፋቱን ስለማቆሙ ዋስትና ሊሰጠኝ ይገባል የሚል አቋም በመያዝ በውይይቱ ላይ ላለመገኘት ስታቅማማ መቆየትዋ ተመልክቷል፡፡ 

ሁለት ቀን የሚፈጀው ስብሰባ እኤአ ጥር 12 ብራስልስ ውስጥ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡  

Source: Link to the Post

Leave a Reply