የንግድና ቀጠናዊ ሚኒስቴር በታሸጉ ምርቶች ላይ የይዘትና የክብደት ትክክለኛነት የሚረጋግጥ ስርዓት ዘርግቻለሁ አለ::የታሸጉ ምርቶች መጠናቸው እና በማሸጊያውቸው ላይ የተገለፀው ሁኔታ ትክክል…

የንግድና ቀጠናዊ ሚኒስቴር በታሸጉ ምርቶች ላይ የይዘትና የክብደት ትክክለኛነት የሚረጋግጥ ስርዓት ዘርግቻለሁ አለ::

የታሸጉ ምርቶች መጠናቸው እና በማሸጊያውቸው ላይ የተገለፀው ሁኔታ ትክክል መሆኑን እያረጋገጠ እንደሆነም አስታውቋል ።

በንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የሕጋዊ ሥነ ልክና የቴክኒክ ደንብ ማስተባበር መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ጌታቸው ወለል ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናግሩት የታሸጉ ምርቶች ሲባል ከውጪ ሀገር የሚገቡትን ጨምሮ የሀገር ውስጥ ምርቶችን ያከተተ ቁጥጥር አንሚደረግ አንስተዋል።

በ35 የታሸጉ የምርቶች አይነቶች ላይ የተጣራ ክብደት ትክክለኛነት ላይ ክትትል እና ቁጥጥር እየተደረገ ነውም ብለዋል።

በመደበኛ እንዲሁም በድንገተኛ መልኩ ቁጥጥር እንደሚደረግና በምርቶቻቸው ላይ ከፍተኛ ጉድለት የታየባቸው ላይ ከማስጠንቂያ ጀምሮ የማሸግ እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው ብለዋል።

ነዳጅ ከጅቡቲ እየተቀብሉ ወደ ሀገር ውስጥ የሚያመላልሱ ቦቴ የተባሉ መኪኖች ላይ ድንገተኛ ክትትል ከተደረገባቸው 20 መኪኖች የሚይዙት መጠን ተለክቶ ጉድለት የተገኘባቸው 12ቱ ላይ እርምጃ መወሰዱን ተናግረዋል።

ስራው በ2015 እቅድ ተይዞለት ወደ ስራ ቢገባም ብዙ ሊኬድበት ባለመቻሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ሲሰሩ ቆይተው በ2016 ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልፀዋል።

ውስን የሆኑ የመለኪያ መሳሪያዎች እና በዘርፉ ያሉ የሰው ሀይሎች ጥቂት በመሆናቸው አሁን ላይ በዋነኛነት አዲስ አበባ ላይ ብቻ እየሰሩ እንደሚገኙ አቶ ጌታቸው ተናግረዋል።

ህብረተሰቡም እንደዚህ አይነት ህገ ወጦችን ሲመለከት ጥቆማ በ መስጠት መተባባር አለበት ብለዋል።

በሀመረ ፍሬው

ሚያዝያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply