የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በ 19 ፋብሪካዎች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ፡፡የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የኮሚኒኬሺን ስራ አስፈፃሚ በላይነሽ ረጋሳ በ19 በፋብ…

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በ 19 ፋብሪካዎች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ፡፡

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የኮሚኒኬሺን ስራ አስፈፃሚ በላይነሽ ረጋሳ በ19 በፋብሪካዎች ላይ የላብራቶሪና ኢንስፔክሽን ስራዎች መካሄዳቸውን ለጣቢያችን ተናግረዋል።

በዚህም ቁጥጥር ከተደረገባቸው 2 መቶ 55 ፍብሪካዎች ውስጥ በ19 ፋብሪካዎች ጥራት የሌለው ግብዓት ሲጠቀሙ የተገኙ በመሆኑ የማምረት ሂደታቸውን እንዲያቆሙ አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዶባቸዋል ብለውናል፡፡

በተጨማሪ በ5 አምራች ድርጅቶች የምርት ጥራት ስርተፍኬት ሳይዙ ወደ ገበያ በመግባታቸው የማስጠንቀቂያ እርምጃ መወሰዱን ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡

በፋብሪካ ቦታዎች በተደረገው የጥራት ማረጋገጥ ስራዎች ከደረጃ በታች በሆኑ ባለ 8ና ባለ 12 ሚሜ ዲያሜትር በፍሬ ወደ 24 ሺህ 112 የአርማታ ብረት መወገዱን ነግረውናል ።
ከደረጃ በታች የሆኑ ለስላሳ መጠጦችና የልብስ ሳሙ ወደ ገበያ እንዳይቀርቡ ከአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ጋር በጋራ በመቀናጀት እንዲወገዱ ተደረረጓል ብለዋል።
ህብረተሰቡ ሸቀጦችን ሲገዛ የጥራት ሰርተፊኬት መኖሩን በመመልከት ራሱንም ቤተሰቡንም መጠበቅ አለበት ተብሏል፡፡

በልዑል ወልዴ

ግንቦት 19 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply