
መኮንን አሊ የተባለው ግለሰብ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 2 ንግድ ፅ/ቤት ሃላፊ ሲሆን በሙስና ወንጀል ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር የዋለው የካቲት 30 ቀን 2015 ዓ/ም ነው፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ እንዳስታወቀው አቶ ሲሳይ ገ/ፃዲቅ የተባሉት ግለሰብ የንግድ ፈቃድ ለማሳደስ ወደ ወረዳው በሄዱበት ወቅት የንግድ ፅ/ቤቱ ሃላፊ መኮንን አሊ የንግድ ፈቃዱ የዕድሳት ጊዜው ያለፈበት መሆኑን ሰበብ በማድረግ ከ1 ወር በኋላ እንደሚታደስላቸው እና ለዚህም 50 ሺህ ብር ጉቦ እንዲሰጡት ይጠይቃቸዋል፡፡
የግል ተበዳይ ግን የተጠየቁትን ገንዘብ የመክፈል አቅም እንደሌላቸው ሲነግሩት 45ሺህ ብር እንዲሰጡት ያግባባቸው ቢሆንም መብቴን በገንዘብ አልገዛም ብለው ሁኔታውን ለፖሊስ በማሳወቃቸው ተጠርጣሪው በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ቦታው ሚካኤል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ብሩን ሲቀበል በክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ አባላት እጅ ከፍንጅ እንዲያዝ ማድረጋቸውን እና ምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መጋቢት 01 ቀን 2015 ዓ.ም
ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራምና የዩቲዩብ ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ!
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን
Source: Link to the Post