#የንግግር ህክምና የስነ ልቦና ወይም የንግግር ህክምናን በተመለከተ በህብረተሰቡ ዘንድ የተሳሳተ አረዳድ መኖሩ ይነገራል፡፡ ይህም የንግግር ህክምና የምክር አገልግሎት መስጠት ነው የሚል እሳቤ…

#የንግግር ህክምና

የስነ ልቦና ወይም የንግግር ህክምናን በተመለከተ በህብረተሰቡ ዘንድ የተሳሳተ አረዳድ መኖሩ ይነገራል፡፡
ይህም የንግግር ህክምና የምክር አገልግሎት መስጠት ነው የሚል እሳቤ ነው፡፡
የምክር አገልግሎት ለአእምሮ እክል ወይም ህመም የሚሰጥ ቢሆንም የንግግር ህክምና ነው ማለት አለመሆኑም ይገለጻል፡፡

በንግግር ህክምና የአይምሮ እክል ያጋጠመውን ታካሚ የልጅነት ጊዜ አስተዳደግን የሚመረምር እና ያጋጠመውን ችግር ከስር ከመሰረቱ የሚያጤን ሲሆን፤ ታካሚው የችግሩን መንስኤ እንዲገነዘብ የሚረዳ የህክምና መንገድ ነው ተብሏል፡፡

ለጭንቀት፣ ድባቴ እና መሰል አእምሮ እክሎች የንግግር ህክምናን እንደ መጀመሪያ የህክምና ሂደት እንደሚሰጥ የአእምሮ ሀኪም የሆኑት ዶክተር እስጢፋኖስ እንዳላማው ተናግረዋል፡፡

በዚህ የህክምና ሂደትላይ ታካሚዎች የሚሰማቸውን የውስጥ ሀዘን ፣ ንዴት፣ ሃሳባወቸውን እና ያለፉበትን መልካም ሆኑ መጥፎ አጋጣሚዎችን በነጻነት የሚናሩ ሲሆን፤ ባለሞያው ችግሩን በትኩረት በመረዳት የትኛው ጉዳይ በህይወቸው ላይ ተጽዕኖን ሊያሳድር እንደሚችል እና የህመሙ ሚታከምበትን ሁኔታ የሚመረምር ይሆናል፡፡

የህክምና ሂደቱ በባለሞያው እና በታካሚው መካከል የሚካሄድ በመሆኑ የታካሚው ሚስጥር እንዲጠበቅ ያደርጋል ተብሏል፡፡

#የንግግር ህክምና አይነቶች

የንግግር ህክምና እንደ ህመሙ አይነቶች እንደሚለያይ ተነግሯል፡፡

•ድንገተኛ ሃዘን ሲያጋጥም

•ከአደጋ መኋላ የሚከሰት ለአይምሮ እክልን

•በትዳር ህይወት ለሚያጋጥሙ ግጭቶች

•ለሱስ ለተጋለጡ ሰዎች

•አረዳድ እና ባህሪን ለማረቅ

•ጠባሳ ሆነው የቀጠሉትን በልጅነት ጊዜ የተከሰቱ መጥፎ የህይወት አጋጣሚዎች ለማከም የሚሰጥ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

ባለሞያው እንደገለጹት፤ በልጅትነት ጊዜያት ላይ የሚያልፉ ጥሩም ሆኑ መጥፎ የህይወት ክስተቶች ለሰዎች የወደፊት ህይወት እና ስነ ልቦና ላይ ከፍተኛ ጫና የሚያሳድሩቡት ሁኔታ መኖሩን ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች ልጆቻቸውን የሚናገሩት ንግግር የተገራ፣ የሚተገብሯቸው ድርጊትች የተቆጠቡ ሊሆኑ ይገባል ብለዋል፡፡ ምክንያቱም የብዙዎች የአእምሮ እክሎች በልጅነት ጊዘያት ላይ በሚፈጠሩ መጥፎ ተባሳዎችን ተከትሎ የሚከሰቱ መሆናቸው ገልጸዋል፡፡

የሰዎች አሉታዊ ንግግር በሌሎች ላይ ለበታችነት ስሜት፣ ምንም ማድረግ አልችልም ብሎ ለማሰብ እና አንዳንዴም ከልክ በላይ ለራስ ክብርን መስጠት ሊያጋልጥ በመቻሉ፤ አንደበት ሊታረም እና ለሰዎች አይምሮ መጠንቀቅ አስፈላጊነቱ ተጠቁሟል፡፡

የንግግር ህክምና ውጤማነቱን የነገሩን ባለሞያው በማህበረሰቡ ዘንድ የተለመደው የተሳሳተ አረዳደድ ሊታረም እንደሚገማ እና ሰዎች የሚያስጨንቸውን እና የሚያጋጥማቸውን መጥፎ የህይወት ክስተቶችን ከባለሞያ ጋር በመነጋገር የአእምሮ ጤናቸውን መጠበቅ ይቻላል ብለዋል፡፡

ህክምናው በዋናነት በልጅነት የእድሜ ክልል ያጋጠሙ ሁኔታዎችን የሚያውስ፣ የትኛው የህይወት ገጠመኝ የሰዎች ስነ ልቦና እና የዕለት ተዕለት ህይወት ላይ ጫና የሚያሳድሩትን መንስዔዎች የሚመረምር በመሆኑ በወላጅ አልያም በአሳዳጊዎች ዘንድ ቢለመዱ ያሏቸውንም የልጆች አስተዳደግን ነግረውናል፡፡

በተቻለ መጠን ቁጡ አለመሆን፣ የልጆች ባህሪ ላይ ለማረቅ መስራት፣ ከቁስ በተጨማሪ ፍቅርን ለልጆች መስጠት እና ልጆች የሚተማመኑበት ወላጅ መሆን አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

በእሌኒ ግዛቸው

ሚያዝያ 18 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply