የንጹሃን ዜጎች ግድያ መፈናቀልና የንብረት ውድመት የተወሳሰበውና ቶሎ ሊቆም ያልቻለው ድብቅ የፖለቲካ አላማ ባላቸው በመንግስት አካላት ተባባሪነት ጭምር እንደሆነ ተገለጸ…

የንጹሃን ዜጎች ግድያ መፈናቀልና የንብረት ውድመት የተወሳሰበውና ቶሎ ሊቆም ያልቻለው ድብቅ የፖለቲካ አላማ ባላቸው በመንግስት አካላት ተባባሪነት ጭምር እንደሆነ ተገለጸ…

የንጹሃን ዜጎች ግድያ መፈናቀልና የንብረት ውድመት የተወሳሰበውና ቶሎ ሊቆም ያልቻለው ድብቅ የፖለቲካ አላማ ባላቸው በመንግስት አካላት ተባባሪነት ጭምር እንደሆነ ተገለጸ አሻራ ሚዲያ ጥር፡-13/05/13ዓ.ም ባህር ዳር ኢፌዴሪ 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል፡፡ በውይይቱ ላይ በንጹሃን ዜጎች ላይ ማንነትን መሰረት ያደረገ አሰቃቂ ሞት፣ የአካል ጉዳት፣ መፈናቀልና የንብረት መውደም መድረሱ ተረጋግጧል፡፡ በመድረኩ ላይ መንግስት የህብረተቡን የቆየ አብሮነት ለማስቀጠል ህዝቡን ያሳተፈ ተከታታይና ቀጣይነት ያለው የፖለቲካ ስራና የህዝብ ማወያየት ስራ መስራት እንደሚገባው ተነስቷል፡፡ እንዲሁም የዜጎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥም ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡ በተጨማሪም መንግስት በመተከል ዞን የተፈጠረውን ችግር በመደበኛው ህግ ለመቆጣጠርና ማስቆም ካልቻለ ህግና ስርአትን ለማስከበር እንዲሁም የንጹሀንን ህይወት ለመታደግ ሌላ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሳያስፈልግ በትግራይ ክልል ታውጆ የነበረውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማስፋት በመተከል ዞንም ተግባራዊ እንዲያደርግ የምክር ቤቱ አባላት ጠይቀዋል፡፡ በመጨረሻም በመተከል የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት የዜጎችን ህይወት መታደግና የንጹሀንን እንግልት ማስቆም ስላልቻለ መንግስት የመተከልን ጉዳይ ትኩረት ሰጥቶ ማየት እንዳለበት ተመላክቷል ነው የተባለው፡፡ ዘጋቢ፡-ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply