የንፁሃን ጅምላ ግድያ

በጋሸና እና ሰሜን ሸዋ አንፆኪያ አካባቢ ከ100 በላይ ንፁሃን ዜጎች በጅምላ መገደላቸውን መንግስት አስታወቀ።

ይህ ድርጊት የሕወሓት የሽብር ቡድን በአማራና በአፋር ክልል እፈጸመ ለሚገኘው የዘር ማጥፋት ድርጊት ማሳያ ነው ሲሉም የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስጽር ዴኢታ ሰላማዊት ካሳ ተናግረዋል፡፡

የህወሓት የሽብር ቡድን እየፈፀመ የሚገኘውን የዘር ማጥፋት ተግባር መቀበል ለቸገራቸው አንዳንድ ተቋማት በግልጽ እንዲመለከቱ ያደረገ ነውም ብለዋል።

ሚኒስቴር ዴኢታዋ አክለውም መንግስት የጅምላ ግድያ በተፈጸመባቸው ስፍራዎች በቂ ማጣራት አድርጎ ለዓለማቀፋ ማህበረሰብ ያሳውቀዋል ብለዋል።

መሠረታቸውን ሰብዓዊነት ላይ አድርገው የሚንቀሳቀሱ ዓለም አቀፍ ተቋማትም ሁነቱን በማጣራት ለዓለም እንዲያሳውቁም ጠይቀዋል፡፡

የሽብር ቡድኑ በአማራ ክልል በደቡብ ጎንደር ዞን በቅርሶች ላይ ባደረሰው ውድመት 23ሚሊየን ብር መታጣቱንም አሳውቀዋል፡፡

በተመሳሳይ በአፋር ክልል በዚህ ዓመት ከቱሪዝም ይገኛል ተብሎ የታሰበው 25ሚሊዮን ብር መታጣቱም ተገልጿል።
የሽብር ቡድኑ በሁሉም ግንባሮች ላይ ሽንፈት እየተከናነበ መሆኑንም መንግስት ጠቁሟል።

ቀን 27/03/2014

አሐዱ ቴሌቪዥን!

Source: Link to the Post

Leave a Reply