
“የኛ ቲቪ” የተሰኘው የዩቲዩብ ሚዲያ ጋዜጠኞች ለዘገባ በወጡበት መታሰራቸው ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 1 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በአዲስ አበባ ከታገደው የባጃጅ ትራንስፖርት ጋር በተገናኘ ዜና ለመስራት በመንቀሳቀስ ላይ የነበሩ “የኛ ቲቪ” የተሰኘው የዩቲዩብ ሚዲያ ጋዜጠኞች ማታሰራቸው ተሰምቷል፡፡ የየኛ መልቲ ሚዲያ ሥራ አስኪያጅ እንግዳ ሰው ገበየሁ ለአዲስ ማለዳ እንደገለጹት፣ የታሰሩት አንድ ጋዜጠኛ እና አንድ የካሜራ ባለሙያ ናቸው፡፡ ጋዜጠኞች የታሰሩት በቀረጻ ላይ እያሉ መሆኑን የገለጹት ሥራ አስኪያጁ፣ የታሰሩት ዓድዋ ድልድይ አካባቢ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት መታገዱን ተከትሎ፣ በተለይ የባጃጅ ትራንስፖርት በሚበዛባቸው አካባቢዎች ላይ የትራንስፖርት እጥረት ማጋጠሙ እየተገለጸ ይገኛል፡፡ ዘገባው የአዲስ ማለዳ ነው።
Source: Link to the Post