የኛ ፍላጎትና አቋም ህዝባችን የሚመርጠዉን እና ፍላጎቱን መደገፍ ስለሆነ በወልቃይት፣ በጠገዴ፣ በካፍታ ሁመራ፣ በጠለምትና በራያ ያለዉ የወገናችን ፋላጎት እንዲሰማና እንዲከበር አጥብቀን መንግ…

የኛ ፍላጎትና አቋም ህዝባችን የሚመርጠዉን እና ፍላጎቱን መደገፍ ስለሆነ በወልቃይት፣ በጠገዴ፣ በካፍታ ሁመራ፣ በጠለምትና በራያ ያለዉ የወገናችን ፋላጎት እንዲሰማና እንዲከበር አጥብቀን መንግስትን እናሳስባለን ! ————————–…———————— የአገሪቷ “ሕገ መንግስት” የሚባለው ከመቋቋሙ በፊት የበጌምድር ክፍለ ሃገር አካል የነበሩት የወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ካፍታ ሁመራና ጠለምት፣እንዲሁም የወሎ ክፍለሃገር አካል የነበረው ራያ በጉልበት ወደትግራይ ክልል እንዲካተቱ ተደርገዋል። ኋላም የጎጃም ክፍለ ሃገር አካል የነበረው መተከል ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እንዲካተት ተደርጓል። ሰሞኑንን ከሕወሃት ጋር በተደረገው ውጊያ በከፍተኛ መስዋዕትነት የተመዘገበውን ድል ተከትሎ ከቤጌምድርና ከወሎ የተወሰዱት አካባቢዎች ከሕወሃት እጅ ወጥተዋል። ሕወሃት ዴሞግራፊን ለመቀየር በነዚህ አካባቢዎች የፈጸማቸው የዘር ማጥፋት ወንጀሎች በስፋት እየተዘገቡ ነው። ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ዜጎች ተፈናቅለዋል፤ ተሰደዋል። በብዙ ቦታዎችም የጅምላ መቃብሮች እየተገኙ ነው። ይሄም ልባችንን እጅግ አድምቶታል። ከነዚህ አካባቢዎች የተፈናቀሉትን ወገኖቻችን መልሰው እንዲቋቋሙ በመርዳት ፋንታ፣ የሕወሃት ሕገ ወጥ ተግባር ትክክል እንደነበረ በሚያሳስብ መልክ ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ካፍታ ሁመራ፣ ጠለምትና ራያን አዲስ በተመሰረተው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ መንግስት ስር እንዲተዳደሩ ለማድረግ የሚወሰደውን ማናቸውንም አይነት እንቅስቃሴ አጥብቀን እንቃወማለን። አገር ተረጋግታ ሕዝባዊ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ ሕዝቡ እራሱን በራሱ የማስተዳደር መብቱ እንዲከበርለት እንጠይቃለን። ሆኖም የህግ የበላይነትን በማስከበር ስም መንግስት የወያኔን እና የኦነግን ህገመንግስት እየጠቀሰ እነዚህን አካባቢዎች አለ ፈቃዳቸዉ ወያኔ በ1983 ዓም በጉልበት ወደ አካለላቸዉ ክልል ተካተዉ እንዲቀጥሉ ማስገደድ ካሰበ እጅግ ትልቅ መዘዝ እና ጣጣ ለመንግስት ለራሱ ይዞበት እንደሚመጣ ካሁኑ ማሳሰብ እንወዳለን:: የኛ ፍላጎትና አቋም ህዝባችን የሚመርጠዉን እና ፍላጎቱን መደገፍ ስለሆነ በወልቃይት፣ በጠገዴ፣ በካፍታ ሁመራ፣ በጠለምትና በራያ ያለዉ የወገናችን ፋላጎት እንዲሰማና እንዲከበር አጥብቀን መንግስትን እናሳስባለን:: የአማራ ወገናችንም በአጠቃላይ እና በጋራ በመንቀሳቀስ አሁን በእጁ የገባዉን ድል ማስጠበቅና እንዲሁም በመላዉ ሀገሪቱ ህልውናውን የማረጋገጥ ትግሉን ዳር ሳያደርስ እንዳይዘናጋ አጥብቀን እንመክራለን:: ———————————— ዘጠኝ ስብስቦች በጋራ ያወጡት ባለ ሰባት ነጥብ መግለጫ ————————– 1. ኢትዮጵያዊነት–(ሰሜን አሜሪካ) 2. ሀገር አድን–(ሰሜን አሜሪካ) 3. የኢትዮጵያ ህልዉና አድን ህብረት-¬-(ሰሜን አሜሪካ) 4. የዓለም አቀፍ የአማራ ህብረት–(ሰሜን አሜሪካ) 5. ሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት–(ሰሜን አሜሪካ) 6. ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ሴቶች ድርጅት-(ሰሜን አሜሪካ) 7. የባልደራስ ለእዉነተኛ ዲሞክራሲ የድጋፍ ማህበር በሰ/ሜን አሜሪካ–(ሰሜን አሜሪካ) 8. የታህሳስ ሶስት መታሰብያ ለአንድነትና ዴሞክራሲ–(ሰሜን አሜሪካ) 9. ሀገራዊ የምክክር አደባባይ–(ሰሜን አሜሪካ) https://www.ethiopoint.com/amharic/archives/113479…

Source: Link to the Post

Leave a Reply