You are currently viewing የአሁኑንም ለትምህርት እናድርገው! ****************************  መምህርት መስከረም አበራ  መንግስት እነ አቦይ ስብሃትን መፍታቱን ተከትሎ በህዝቡ ዘንድ ብዙ መደናገር፣መበሳ…

የአሁኑንም ለትምህርት እናድርገው! **************************** መምህርት መስከረም አበራ መንግስት እነ አቦይ ስብሃትን መፍታቱን ተከትሎ በህዝቡ ዘንድ ብዙ መደናገር፣መበሳ…

የአሁኑንም ለትምህርት እናድርገው! **************************** መምህርት መስከረም አበራ መንግስት እነ አቦይ ስብሃትን መፍታቱን ተከትሎ በህዝቡ ዘንድ ብዙ መደናገር፣መበሳጨት ፣ተስፋ ማጣት እየተስተዋለ ነው። በበኩሌ ውሳኔው ብዙ አልገረመኝም። ፈች እና ተፈች ደቀመዝሙር እና መምህር፣ ከሁሉም በላይ የአንድ ጎራ ሰልፈኛ(አማራው በድሎኛል ባይ የዘውግ ብሄርተኛ) መሆናቸውን ለአንድም ቀን ዘንግቸው አላውቅምና ነው ብዙ ያልገረመኝ። በፖለቲካ ትግል ውስጥ እንደ ርዕዮት ዓለም ዝምድና አጥብቆ የሚያስተሳስር ነገር የለም። የርዕዮት ዓለም ዝምድና ነው የአንድ ጎራ ሰልፈኛ የሚያደርገው። የአንድ ጎራ ሰልፈኛ ደግም ለጊዜው ይጋጭ፣ይጣላ ይሆናል እንጅ አይቆራረጥም፣አይጨካከንም። ይህን መረዳት በፖለቲካ መድረክ የጥበብ መጀመሪያ ነው። በሃገራችን የሚንቀሳቀሱ የዘውግ ብሄርተኞች ደግሞ በዚህ ጥበብ የተካኑ ናቸው ፤ ጎራቸውን አይደበላልቁም ፤ ከጎራቸው ውጭ ላለ ቡድን ጥርሳቸውን እንጅ ልባቸውን አይሰጡም፣ ክክለኛ ቀን የመጣ ሲመስላቸው ደግሞ ጥርሳቸውንም ይነፍጉና ሰይፋቸውን ያነሳሉ። ወደድኩህ ከሚላቸው የሌላ ጎራ ሰልፈኛ ይልቅ በጎራቸው ያለ ጠበኛ ይሻላቸዋል ። ወደድኳችሁ ከሚላቸው የሌላ ጎራ ሰልፈኛ ይልቅ ያኮረፈውን የጎራቸውን ቡድን ልብ መልሰው ስለሚያገኙበት መንገድ አብዝተው ይጨነቃሉ ። ሰሞኑን ኦህዴድን እና በህወሃት መካከል የተከሰተው ይሄ ነው! አዲስ ተአምር አልመጣም። ዋናው ቁምነገር ከዚህ ምን እማራለሁ? ማለቱ ነው። እንደ ህዝብ በመሰረታዊነት መማር ያለብን ነገር መንግስት እግር በእግር እየተከታተሉ የሚጠይቁት እንጅ ዝም ብለው የሚያፈቅሩት አካል እንዳልሆነ ነው። የመንግስት ተጠያቂነት የሚበጀው ለህዝብ ብቻ ሳይሆን ለራሱ ለመንግስትም ጭምር ነው።የሚጠይቅ ህዝብ የሚመራ ተጠያቂነትን የተለማመደ መንግስት እንዲህ እንደ ሰሞኑ ያለ ውሳኔ አይወስንም። ብጠየቅ ምን እመልሳለሁ ብሎ ያስባልና ጥንቃቄ ያልጎደለው ሚዛናዊ ውሳኔ ይወስናል። ጥፋቱ ሁሉ ፅድቅ ሆኖ የተቆጠረለት፣አዝማሪው ይበዛለት መንግስት ደግሞ አዝማሪዎቹን ሳይቀር እንደ ብራ መብረቅ ክው የሚያደርግ ጥፋት ያጠፋል፣ሃገር የሚግባባበት ዕምነት የሚያጠፋ ግዴለሽነት ይጠናወተዋል፣ሰው ጤፉ ይሆናል፣ትላንት የተናገረው ከዛሬው ጋር ይሂድ አይሂድ የሚጨነቅበት ምክንያት የለውም። ይህ የመንግስት ብቻ ጥፋት ያመጣው ነገር አይደለም ፤የእኛም ጥፋት አለበት። እንደ ባለአእምሮ አስበን መንግስትን ተጠያቂነት የምናለማምድበት ብዙዎች አጋጣሚዎች ነበሩን። ሶስት አመት ሙሉ ያላባራው ግን ደግሞ ማንም ያልተጠየቀበት፣ማንም አጥፍቻለሁ ያላለበት በአማራ ህዝብ ላይ ያነጣጠረ ዘር ተኮር ጭፍጨፋ ሰምተን እንዳልሰማ አልፈነዋል ፣ጭራሽ “መንግስት ምን ያድርግ?”ብለናል። የሰው ልጅ እንደቆሻሻ በስካቫተር ተዝቆ ሲቀበር ስካቫተሩ የእንቶኔ ነው የሚል የአረመኔ ክርክር አምጥተናል። መንግስት በገዛ አፉ ቁማርተኛ ነኝ ብሎ ተናግሮ፣የዕለት ተዕለት ስራውም ይሄንኑ እየመሰከረ እያየን መንግስትን በማመናችን ቀጥለናል። አንድ ጠቅላይ ሚኒስትር የሃገሪቱ ሁለመና ሲሆኑ፣ሁሉም ነገር ውስጥ ሲገቡ ነገሩ የተቋማዊነት እድል መመናመን አደገኛ ነገር ሳይሆን ጎበዝ መሪ የማግኘት ምልክት መስሎ ታይቶናል። ዜጎች መታወቂያቸው እየታየ ወደ ሃገራቸው ዋና ከተማ እንዳይገቡ ሲደረጉ መጥፎ ምልክት ሆኖ አልታየንም። እኛ ዝም ብለን ያፈቀርነውን መንግስት ሌሎች ዝም ብለው ላያፈቅሩት ስለሚችሉ የመጠየቅ መብት እንዳላቸው መገንዘብ ችግር ሆኖብናል። በመጥፎ መንገድ እየነጎደ ያለውን መንግስት ችላ ብለን በግለሰብ ሞጋቾች ላይ ጦር መዘናል፣እንዲታሰሩ አሳስበናል። ስልጣን የያዙ ወገኖች ኢትዮጵያን የሚያዩዋት በዘውጋቸው በኩል ብቻ መሆኑን ረስተን ኢትዮጵያን ሲሉ አብረውን ወያኔን ሲታገሉ የነበሩ ሰዎችን የኢትዮጵያ ጠላት አድርገን “መንግስት እንዳሻው ያድርጋቸው ከኢትዮጵያ አይበልጡም” ብለናል። ይህ ሁሉ ተደምሮ ነው መንግስት ዛሬ የደረሰው ደረጃ ላይ እንዲደርስ ያደረገው። የመንግስት የዛሬው ስህተቱም የታየን በወያኔ በኩል ስለተሳሳተ ነው። ኢፍትሃዊነት ፣ በደል ፣ዘረኝነት፣አምባገነንነት፣ሌብነት፣የፖለቲካ ሸፍጥ በወያኔ በኩል ብቻ የሚገለጥ ይመስለናል። ፀባችን ከወያኔ ይሁን ከኢፍትሃዊነት ግልፅ አይደለም። ትልቁ ጥፋታችን ይህ ነው! ሌላው ወሳኝ ነገር እኛ ከምናምነው የፖለቲካ አስተሳሰብ ጎራ ውጭ ያለ አካል የመንግስት ስልጣን ሲይዝ አካሄዱን በበለጠ በአንክሮ መከታተል እንጅ ምኞታችንን ተከትለን “መንግስት ያጥፋኝ፣እሱ ያሻግረኝ” ማለቱ ሃገር ሊያሳጣን የሚችል አደገኛ ነገር እንደሆነ መረዳቱ ነው። አሁንም ተስፋ ማጣታችንን ትተን፣ የመንግስትን ብቻ ሳይሆን የራሳችንንም ጥፋት መርምረን፣ለራሳችን ይቅርታ አድርገን ሃገራችን የምትቆይበትን መንገድ ለመተለም የሚያስችል የአስተዋይ ሰው ትግል የምናደርግበትን ጥበብ መላበሱ ይበጃል። #ትግል_አይቆምም ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም :- https://t.me/asharamedia24 ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- https://t.me/asharamedia24 Facebook :- https://www.facebook.com/asharamedia24 ዩትዩብ:- https://bit.ly/33XmKro

Source: Link to the Post

Leave a Reply