You are currently viewing #የአሆላሌ ጨዋታን የጎዳና ላይ ፌስቲቫል በማድረግ በማይዳሰስ ቅርስነት ለማስመዝገብ እንቅስቃሴ ተጀምሯል!    ደሴ:-የካቲት 9 ቀን 2015ዓ.ም        አሻራ ሚዲያ…

#የአሆላሌ ጨዋታን የጎዳና ላይ ፌስቲቫል በማድረግ በማይዳሰስ ቅርስነት ለማስመዝገብ እንቅስቃሴ ተጀምሯል! ደሴ:-የካቲት 9 ቀን 2015ዓ.ም አሻራ ሚዲያ…

#የአሆላሌ ጨዋታን የጎዳና ላይ ፌስቲቫል በማድረግ በማይዳሰስ ቅርስነት ለማስመዝገብ እንቅስቃሴ ተጀምሯል! ደሴ:-የካቲት 9 ቀን 2015ዓ.ም አሻራ ሚዲያ የአሆላሎን ፌስቲባል ለመታደም ክብርት ዶክተር አርቲስት ማሪቱ ለገሰ እና የደቡብ ወሎ ዞን ባህልና ቱሪዝም የአሆላሎ አምባሰደር ድምፃዊት ሃናን አብዱ በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ጥረቱን ወደ ስኬት ለመቀየር ብዙ ርቀት ኪሎ ሜትሮችን በውጣ ውረድና ጠመዝማዛ መጓዝን እንደሚጠይቅ ተገልጿል። ለዚያ ስኬት የሚሆን አንድ ጠጠር በአሻራነት እኛ እንወርውር። ስለሆነም በሐይቅ ከተማ አስተዳደር “ባህላችን ለሠላማችን፣ ለአንድነታችን በሚል መሪ ቃል የአሆላሌ ፌስቲቫል ተከብሯል።… አሆለሌ ባህላዊ ጨዋታ ብቻ አይደለም፤ አሆለሌ ድርድር ነው፤ አሆለሌ ፉክክር ነው፤ አሆለሌ ውድድር ነው፤ አሆለሌ አሸናፊነትንና አሸናፊን በሚዛን መቀበል ነው፤ አሆለሌ ሁለት ውበቶች አሸናፊ ለመሆን የሚደራደሩበት የመስጠት ባህል ነው። አሆለሌ በጥቅሉ ፍላጎቶች በነፃነት የሚገለጡበት፣ የሚቻቻሉበት፣ የሚከባበሩበትና ተቀባይነት ያገኘው ፍላጎት ”ውበት” በክብርና በጭብጨባ የሚተገበርበት ባህላዊም ዴሞክራሲያዊም መድረክ ነው። አሆለሌ አቃፊነት በተግባር የሚገለጥበት መድረክም ነው። የፍቅር መድረክም ነው። ኑና አስተዋውቁት! ይህ ፌስቲቫል ከደሴ-ሀይቅ ከተማ በደቡብ ወሎ ዞን ባህልና ቱሪዝም አስተባባሪነት ተከብሯል ። በአሆላሎ ባህል ፌስቲቫል ድንቅ የጎዳና ላይ የባህል ትእይንት እና የመድረክ ላይ የባህል ዝግጅት በደሴ ከተማ ተከናውኗል። ” በአሆላሎ ጨዋታ እጅግ ውብና ማራኪ የሆኑ አይረሴ ትዝታዎች ተከናውኗል። “ባህሌን ባህሌን ያደኩበትን እኔ እወደዋለሁ ጥበቡን ጥበቡን … ሆ ጥፊ ይለኛል ሆ ሂጂ ብረሪ ሆ ባገራችን ወግ በባህል ኑሪ” በ”ወሎ የትምህርት የሳይንስ እና የባህል ኮንፈረንስና ፌስቲቫል” በደሴ ተደርጓል። ከተለያዩ የደቡብ ወሎ ዞን ከወረዳዎች የተውጣጡ ከ26 በላይ የባህል ቡድኖች የመጡባቸውን አካባቢ ባህላዊ ክዋኔዎችን አቅርበዋል። ትንሿ ኢትዮጵያንም ወሎ ላይ ለማየት ተችሏል። ከማራ ሳይንት እስከ የዋግሹሞቹ መፍለቂያ አገው ምድር ፣ ከትንቢተኛው የሸህ ሁሴን ጅብሪል መንደር መቅድላ እስከ ራያ አላጆ ከጥበበኞቶቹ ሀገር ላስታ ላሊበላ እስከ ቃሉ ድረስ ያሉ ቱባ ባህሎቻችን ከነ ወዛቸው ለታዳሚያን አሳይተዋል ። በዘንድሮ የአሆላሎ ፌስቲባል የተሁለድሬ ወረዳ በሐይቅ ከተማ ፍፃሜውን ያገኘ ሲሆን በቀጣይ የአምባሰል ወረዳ በመረከብ ለ2016 ዓ.ም ከወዲሁ ስራ እንደሚጀምሩ አዘጋጆች ተናግረዋል። አሻራ ሚዲያ ሙሉ ዝግጅቱን በአሻራ ዩትዩብ ቻናል ወደ አድማጭ ተመልካቾች ያደርሳል። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- ቴሌግራም :- https://t.me/asharamedia24 Facebook :- https://www.facebook.com/asharamedia24 youtube :- https://www.youtube.com/channel/UChir2nIy58hlLQRYyHIQeHA Telegram (https://t.me/asharamedia24)

Source: Link to the Post

Leave a Reply