የአለም አቀፉ አማራ ህብረት ዋና ፀሀፊ ወጣት መሳፍንት መንግስቱ ከ12 ቀናት የእስር ቆይታ በኋላ ተፈታ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   ህዳር 15 ቀን 2013 ዓ.ም        አዲስ አበባ…

የአለም አቀፉ አማራ ህብረት ዋና ፀሀፊ ወጣት መሳፍንት መንግስቱ ከ12 ቀናት የእስር ቆይታ በኋላ ተፈታ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 15 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ…

የአለም አቀፉ አማራ ህብረት ዋና ፀሀፊ ወጣት መሳፍንት መንግስቱ ከ12 ቀናት የእስር ቆይታ በኋላ ተፈታ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 15 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአለም አቀፍ አማራ ህብረት ዋና ፀሀፊ ወጣት መሳፍንት መንግስቱ በባህር ዳር የጦር መኮንኖችን የምስክር ሂደት ለመከታተል ካቀናበት በአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን መታሰሩን መግለጻችን ይታወሳል። ወጣት መሳፍንት መንግስቱ በአደራ እስረኛ መልክ በባህር ዳር 6ኛ ፖሊስ ጣቢያ ለተከታታይ 12 ቀናት ከታሰረ በኋላ ትናንት ህዳር 14 ቀን 2013 ዓ.ም አመሻሹን ስለመፈታቱ የማህበሩ ም/ሰብሳቢ አማረች አስራቴ አስታውቃለች። አማረች እንደገለፀችው ችሎት መታደም መብት መሆኑ ቢታወቅም በፌስ ቡክ ገጹ ጽፏል በሚል ውሀ የማይቋጥር ምክንያት በመጥቀስ ታስሮ የሰነበተው ወጣት መሳፍንት መንግስቱ በ2 ሽህ ብር ዋስትና ከእስር ተለቋል። ጉዳዩን የተመለከተው የባህር ዳር ወረዳ ፍ/ቤት ነው ትናንት በዋለው ችሎት በገንዘብ ዋስትና የፈታው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply