You are currently viewing የአላማጣ ከተማ ነዋሪዎች ስቃይ  ታህሳስ 27/2014/ አሻራ ሚዲያ / በአሸባሪው ህወሃት ቁጥጥር ስር የምትገኘው የአላማጣ ከተማ ማህበረሰብ የወራሪው ቡድን ሃይሎች እያደረሱባቸው የሚገኘውን…

የአላማጣ ከተማ ነዋሪዎች ስቃይ ታህሳስ 27/2014/ አሻራ ሚዲያ / በአሸባሪው ህወሃት ቁጥጥር ስር የምትገኘው የአላማጣ ከተማ ማህበረሰብ የወራሪው ቡድን ሃይሎች እያደረሱባቸው የሚገኘውን…

የአላማጣ ከተማ ነዋሪዎች ስቃይ ታህሳስ 27/2014/ አሻራ ሚዲያ / በአሸባሪው ህወሃት ቁጥጥር ስር የምትገኘው የአላማጣ ከተማ ማህበረሰብ የወራሪው ቡድን ሃይሎች እያደረሱባቸው የሚገኘውን ግፍ እና በደል በመሸሽ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በቆቦ ከተማ ተጠልለው እንደሚግኙ ነዋሪዎቹ የገለፁ ሲሆን የመንግስት ይፀጥታ ሃይሎች እንዲደርሱላቸውም ጠይቀዋል። የመከላከያ ሰራዊቱ ከአላማጣ በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኘውን የዋጃ ጥሙጋ አከባቢን ሲቆጣጠር የወራሪው ሃይሎች በመደናገጥ የአላማጣ ከተማን ለቀው ወጥተው ነበር ያሉት ነዋሪዎቹ, ነገር ግን ሰራዊቱ ባለህበት ፀንተህ ቁም በመባሉ ወራሪዎቹ ዳግም ወደ ከተማዋ በመመለስ ህዝብን እየገደሉ ነው ብለዋል። ነዋሪዎቹ የህወሃት ሃይሎች በከተማዋ የሚገኙትን ወጣቶች፣ህጻናት፣ሴቶችና አረጋውያንን እየገደሉና ቤት ለቤት እየዞሩ እየዘረፉ ነው ያሉ ሲሆን, አብዛኻኛው ነዋሪ ከተማዋን ለቆ በመውጣት በቆቦ ተጠልሎ እንደሚግኝም ተናግረዋል። ወደ ቆቦ ከተማ ለመምጣት አቅም አጥተው እዛው በአላማጣ ከተማ ሆነው በአሸባሪው ህወሃት የመከራ ገፈት እየተሸከሙ ያሉ ወገኖች አሉ ያሉት ነዋሪዎቹ, የመከላከያ ሰራዊት የአማራ ልዩ ሃይል እና ፋኖ በአስችኳይ እንዲደርስላቸው ተማጽነዋል። via የኛ ቲቪ

Source: Link to the Post

Leave a Reply