የአልሸባብ የጥፋት ቡድን አባላት ወደ ሶማሌ ክልል ሰርገው ለመግባት ያደረጉት ሙከራ በሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል ከሸፈ።በትላንትናው እለት በሶማሌ ክልል ሙስተሂል ወረዳ ሰበድ ሁሜ በተሰኘ ድንበ…

የአልሸባብ የጥፋት ቡድን አባላት ወደ ሶማሌ ክልል ሰርገው ለመግባት ያደረጉት ሙከራ በሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል ከሸፈ።

በትላንትናው እለት በሶማሌ ክልል ሙስተሂል ወረዳ ሰበድ ሁሜ በተሰኘ ድንበር ወደ ሀገር ውስጥ በመዝለቅ ጥፋት እና ሽብር ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ በነበሩ የአልሸባብ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የሶማሌ ክልል ፀጥተ ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሁሴን አብዱላሂ ቃሲም ገለፁ።

ድንበር እየጠበቀ በሚገኘው የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል እርምጃ የተወሰደበት ቡድን ወደ ሶማሊያ የሸሸ ሲሆን ከቡድኑ አባላት መካከል አንዱ ሲገደል ሌላኛው ቆስሎ በቁጥጥር ስር መዋሉንም ኃላፊው ተናግረዋል።

የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል ወደ ግዳጅ ቀጠና መሰማራቱን እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም ወደሀገር ውስጥ ለመዝለቅ የተለያዩ ሙከራዎችን እያደረገ ለሚገኘው የአልሸባብ ቡድን በቂ ምላሽ የሚሰጥ ሐይል አለን ያሉት ኃላፊው የክልሉንም ሆነ የሀገርን ዳር ድንበር ለመጠበቅ የሶማሌ ክልል ፀጥታ አካላት ከመቼውም ግዜ በላይ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሐምሌ 21 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply