የአመቱ በጎ ሠው! መሐመድ አል አሩሲ

የአመቱ በጎ ሠው!
መሐመድ አል አሩሲ …. እንኳን ደስ አለህ !

ፖለቲከኛው ስልጣን አክቲቪስቱ ጥቅማ ጥቅም በሚፈልግበት ሃይማኖተኛው አስመሳይና አጨብጫቢ በሆነበት በዚህ ወቅት ስለሐገር የቆመ ሰው ማግኘት መታደል ነው።

መሀመድ አልአሩሲ محمد بن محمد العروسي ለኢትዮጵያ ስለኢትዮጵያ ኢትዮጵያዊነትን ያላጓደለ ከታላቅም አልፎ ታላቅ ስለሐገር ደሕንነትና ልማት ሰላምና ብሔራዊ ጥቅም በግንባር ቀደምትነት ታላቅ ስራ እየሰራ የሚገኝ ውድ ኢትዮጵያዊ ነው።

ፖለቲከኞች የውስጥ ቀውስን ተገን አድርገው ከውጪ ኃይሎች ጋር በሚያሴሩበት ዘመን ጋዜጠኛ፣ የፖለቲካ ተንታኙና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ መሐመድ አል አሩሲ ግን ሐገራችንን ለመበጥበጥ የሚያሴሩ የውጪ ኃይሎችን ፊት ለፊት የተጋፈጠ እንቁ ኢትዮጵያዊ ነው።

ሃገር እንምራ ሕዝብ እናስተዳድር የሚሉ ፖለቲከኞች ስለሐገርና ሕዝብ ጥቅም ቆመናል ብለው ጥቅማቸውን የሚያደላድሉ አክቲቪስቶችንና ስማቸው የማይጠቀስ ምናምናቸውን ሽፋን አድርገው የሚያጨበጭቡትን አቅፈን እርር ድብን በምንልበት በዚህ ወቅት ስለሕዳሴው ግድብና ስለ አባይ ወንዝ ባለቤትነታችን ጠላቶቻችንን ፊት ለፊት በመቅረብ በዓለም ሚዲያዎች ፊት ያሳፈረልን ውድ ወንድማችን ዜጋችን የኢትዮጵያዊነት ድምቀታችን ነው ሰው የጠፋ እለት ሰው ሆኖ የተገኘ መሐመድ አል አሩሲ።#MinilikSalsawi

Source: Link to the Post

Leave a Reply