የአማራነት ፈተና ከዘመነ ወያኔ እስከ ብልጽግና ትንሳኤ በሚል በደራሲ ዶ/ር አብይ ይመር በዳኔ የተጻፈ መጻፍ በደብረ ብርሃን ከተማ ተመርቋል:: (አሻራ ሚዲያ ሚያዚያ 22/2014 ዓ.ም)…

የአማራነት ፈተና ከዘመነ ወያኔ እስከ ብልጽግና ትንሳኤ በሚል በደራሲ ዶ/ር አብይ ይመር በዳኔ የተጻፈ መጻፍ በደብረ ብርሃን ከተማ ተመርቋል:: (አሻራ ሚዲያ ሚያዚያ 22/2014 ዓ.ም)በመጻፍ ምርቃ ስነ ስርዓቱ ላይ በክብር እንግድነት የታደሙት ረዳት ፕ/ር ትንግርቱ ገብረ ጻድቅ እንዳሉት ሸዋ የትንሳኤውም የፈተናውም በግ ሊሆን አይገባም ብለዋል:: ትውልዱ ባገኘው አጋጣሚ መማርና ለመማር ዝግጁ መሆን አለበት፣ በጉዞየ ሁሉ ትምህርት ቤት አላየሁም ምነው ህዝባችን መማር አቁሟል እንዴ በማለት በዚህ መንገድ ሳናስተምር እኛ የገፋነውን ህዝብ ማን ሊያከብረው እንደሚችል ገልጸዋል:: ሰው በዘውድና በቋንቋ እየተገደለ ባለበት በዚህ ወቅት መማር ሊበረታታ እንጂ ሊቆም አይገባም ያሉ ሲሆን ህዝባችን በድህነት አዘቅት እንዲኖር መፍቀድ የለብንም ህዝብንና ከተማውን ታሳቢ አድርጎ መስራት ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል :: ስንወልድ የምናሻግራት ሀገር እንዳለች አስበን ከሆነ ልጆቻችንን ማስተማር ግድ ይላል ብለዋል:: የሚገፉ ጉዳዮችን በደንብ መመልከት ይኖርብናል የሚተካኩት ፈተናዎች ቀላል አደሉም የሚፈናቀለውን ማየት አለብን ከሚፈናቀለው መካከል 50%ቱ ተፈናቃይ አማራ በመሆኑ ለምን ሆነ ብለን መስራት ይገባናል ብለዋል:: የአማራነት ፈተና የሚለውን ይህን መሰል መጻፍ ለመጻፍ የሚያፍሩ ይኖራሉ አማራነትን መመስከር ታላቅነት ነው የህዝባችንን ባህላዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ለመግፋትና ከፍ ለማድረግ የድርሻችንን መወጣት ይኖርብናል ሲሉ አሳስበዋል:: የክልሉ ባለሀብቶች ደብረ ብርሃን ከተማን ማልማት ይኖርባችኋል ደብረ ብርሃን ከተማ የሀገሪቱ ህልውና ነች ብለዋል:: በመጨረሻም ረዳት ፕ/ር ትንግርቱ ገብረ ጻድቅ የአማራነት ፈተና ከዘመነ ወያኔ እስከ ብልጽግና ትንሳኤ የሚለውን መጻፍ ለህዝብ ላበረከቱት ለዶክተር አብይ ይመር ምስጋናቸውን ለግሰዋል:: አሻራ ሚዲያ በቦታው ተገኝቷል ሙሉ የመጻፍ ምረቃ ስነ ስርዓት ዝግጅትን በምስል ዘገባ በዩቲቭ ቻናሉ ያቀርባል:: ዘጋቢ:- አማኑኤል ካሰው ከደብረ ብርሃን

Source: Link to the Post

Leave a Reply