“የአማራን ህልውና ለማስጠበቅ በሚደረገው ማንኛው ትግል ከፊት መስመር በመሰለፍ መስዋት ለመክፈል ዝግጅ ነን፤ … የአማራ ትግል ያሸንፋል!” የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ አዴኃን! አ…

“የአማራን ህልውና ለማስጠበቅ በሚደረገው ማንኛው ትግል ከፊት መስመር በመሰለፍ መስዋት ለመክፈል ዝግጅ ነን፤ … የአማራ ትግል ያሸንፋል!” የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ አዴኃን! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ሀምሌ 6 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ አዴኃን በወቅታዊ ጉዳይ የተሠጠ አጭር መግለጫ! የአማራን ህልውና ለማስጠበቅ በሚደረገው ማንኛው ትግል ከፊት መስመር በመሰለፍ መስዋት ለመክፈል ዝግጅ ነን። አማራ ድሮም ደም እና አጥንቱን እየከሰከሰ እንጅ ህልውናውን የሚያስከብረው በሌሎች ኃይሎች ጠባቂነት አይደለም። የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ አዴኃን ትግሉ የሚጠይቀውን መስዋትነት በመክፈል ታግሎ ያታግላል። ከፊት መስመር በመሠለፍ ቆራጥ ተጋድሎ ለማድረግ መዘጋጀቱን እየገለጠ የአማራ ሕዝብ ከመቸውም በላቀ ሁኔታ ውስጣዊ አንድነቱን አጠናክሮ የተደቀነበትን የህልውና አደጋ በጋራ ለመመከት ሌት ተቀን ይዘጋጅ። የአማራ ወጣት ከድርጅታችን ጋር በመሆን ለአማራ ሕዝብ ህልውና ትግል ሳያመነታ እንዲታገል ጥሪያችን እናሰተላልፋለን። የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከአሁን በፊት ወታደራዊ ስልጠና ለወሰዱ ታጋዮቻችን የትጥቅ አቅርቦት እንዲያሟላ በአስቸኳይ እንጠይቃለን። የአማራ ትግል ያሸንፋል!

Source: Link to the Post

Leave a Reply