የአማራን ህዝብ ለማዳከምና አማርኛ ቋንቋን ለማጥፋት የሚደረገው ትህነጋዊ አካሄድ እንዲቆም ተጠየቀ                 አሻራ ሚዲያ         ታህ…

የአማራን ህዝብ ለማዳከምና አማርኛ ቋንቋን ለማጥፋት የሚደረገው ትህነጋዊ አካሄድ እንዲቆም ተጠየቀ አሻራ ሚዲያ ታህ…

የአማራን ህዝብ ለማዳከምና አማርኛ ቋንቋን ለማጥፋት የሚደረገው ትህነጋዊ አካሄድ እንዲቆም ተጠየቀ አሻራ ሚዲያ ታህሳስ፡-17/04/13/ዓ.ም ባህር ዳር አማራ እየገፉት የሚቀርብ እየጠሉት የሚወድ እየካዱት የሚያምን እየገደሉት የሚበዛ፣ ሰበርነው ሲሉት የሚጠነክር ሕዝብ ነው። ሀገራዊነትና ኢትዮጵያዊነትን አብዝቶ ይወዳል። ከኢትዮጵያዊነት ልክ መውረድ አይስማማውም። በደልን ሁሉ ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያውያን ሲል ይተዋል። ኢትዮጵያ ጫፍ እስከ ጫፍ የጋራችን ናት ብሎ ያምናል። በሰፋች ውብ ሀገር ጠቦ መኖር አይመኝም።ኢትዮጵያዊ ሁሉ ወንድምና እህቱ ነው። የእርሱ ጠላት ኢትዮጵያን የሚነካና የሚከዳ ነው። ስለ ውድ ሀገሩ ኢትዮጵያ አያሌ መስዋትነት ከፍሏል አማራ። አሁንም በመክፈል ላይ ይገኛል። ወደፊትም ለኢትዮጵያ ዋጋ እየከፈለ የቀደመቸውን ሀገሩን ያስቀጥላል። የአማራ ሕዝብ ሲጠላ የሚናገረው አማርኛ ቋንቋም በእንቶኔዎች ተጠልቷል። በመሰረቱ ቋንቋ የተገልጋዩ ሁሉ እንጂ በዘርና በወሰን የሚከለል አይደለም። አማርኛን ቋንቋ ለአማራው ብቻ በመስጠት ቋንቋው እንዳያድግ ሲሰራበት መቆየቱ ይታወቃል። ወራሪው፣ ተስፋፊውና አሸባሪው ትህነግ ስልጣን ስትይዝ የአማራ ግዛት የነበሩ አካባቢዎችን ወደ ትግራይ በማካለል እንዲተዳደሩ አድርጎ መቆየቱም ይታወሳል። ወደ ትግራይ በተካለሉት የአማራ ግዛቶች ወልቃይት ጠገዴና ራያ ውስጥ አማርኛ ቋንቋ እንዲጠፋና የአማራ ማንነት፣ ወግና እሴት እንዲዳከም በርካታ ሥራዎችን ሠርቷል። በእነዚህ አካባቢዎች የሚማሩ ተማሪዎች በአማርኛ እንዳይማሩ፣ እንዳይዳኙና ማንነታቸውን እያጡ እንዲሄዱ ለማድረግ ተጥሯል። የአማርኛ ቋንቋ እንዳይማሩና እንዳያስተምሩ ከተደረጉት ውስጥ በራያ ዋጃ ከተማ የሚኖሩ ነወሪዎች ተጠቃሽ ናቸው ። በትህነግ የግፍ አገዛዝ ዘመን አስቸጋሪ ጊዜያት ማሳለፋቸውን የራያ ዋጃ ከተማ የ ነወሪዎች ለአሻራ ሚዲያ ተናግረዋል። የራያ ልጆች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ባለመማራቸው ለከፍተኛ ኪሳራ ይዳረጉ እንደነበርም ጠቁመዋል። የማንነቱ ጉዳይ ጊዜውን ጠብቆ ይፈታል ቢያንስ ህፃናት በቋንቋቸው ይማሩ ብለው በተዳጋጋሚ ሲጠይቁ እንደቆዩና እንግልት ይፈጸምባቸው እንደነበር ምንጫችን ተናግረዋል። አማራውን ከደርግ ሥርዓት ጋር የማያያዝና የማሸማቀቅ ድርጊት ይፈጸም እንደነበርምምንጫችን ነግረውናል። ራያ ውስጥ ማንነትን ብቻ ሳይሆን ዘርን ለማጥፋትም ትህነግ ዕቅድ ይዞ ይሰራ እንደነበርም ነው ያስረዱን። አካባቢው በትግራይ ክልል በጉልበት ሲከለል ለምን ብለው ለሚያነሱት ጥያቄ ሰሚ እንዳልነበራቸውም ነዋሪዎች አስታውሰዋል። በመጨረሻም ትህነግ ማንነትን ለማጥፋት የቻለችውን ሁሉ ብታደርግም የሕዝቡን ትግል መቋቋም እንዳቃታት ነው የራያ ዋጃ ነዋሪዎች የተናገሩት። አሁን ባለው መንግስትም አማራውን ለማዳከምና አማረኛ ቋንቋን ለማጥፋት እየተደረገ ያለው መንገድ የትህነግን አካሄድ ያሳያልና መንግስት ከእንዲህ አይነቱ ድርጊት እንዲቆጠብ ሲሉ ምንጫችን ለአሻራ ሚዲያ ተናግረዋል ፡፡ ይህን ማድረግ ካልቻለ ግን የትህነግ እጣ ፈንታ ይደርሰዋል ብለዋል የመረጃ ምንጫችን፡፡ ዘጋቢ፡-ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply