የአማራን ህዝብ ለእልቂት የዳረጉ የቤኒሻንጉል አመራሮች በቤኒሻንጉል ጉምዝ ምክር ቤት አባላት በትናንቱ አስቸኳይ ጉባኤ አካሂዶ ነበር  ፡፡ በስብሰባው የተነሱ ሀሳብ ሚከተሉት ነበሩ፡፡…

የአማራን ህዝብ ለእልቂት የዳረጉ የቤኒሻንጉል አመራሮች በቤኒሻንጉል ጉምዝ ምክር ቤት አባላት በትናንቱ አስቸኳይ ጉባኤ አካሂዶ ነበር ፡፡ በስብሰባው የተነሱ ሀሳብ ሚከተሉት ነበሩ፡፡…

የአማራን ህዝብ ለእልቂት የዳረጉ የቤኒሻንጉል አመራሮች በቤኒሻንጉል ጉምዝ ምክር ቤት አባላት በትናንቱ አስቸኳይ ጉባኤ አካሂዶ ነበር ፡፡ በስብሰባው የተነሱ ሀሳብ ሚከተሉት ነበሩ፡፡ ( ታህሳስ 22፣ 2013 ዓ.ም ባህር ዳር ) የአማራ ህዝብ በርስቱና በቤታው እንዲገደል፤ እንዲፈናቀልና ለርሀብ ፤ለእርዛት የዳረጉ አመራሮች ዛሬም በማያባራው የግድያ መንበር ላይ ሆነው የይስሙላ ስብሰባ ማድረጋቸው በጫካ ያሉ ገዳዮችን ልቦና አያራራም፤የሟቾችን ነፍስ አይመልስም፤ለተፈናቃዮችም ዳቦ አይገዛም፡፡ ከታች የተዘረዘሩ 14 ነጥቦችም ለታሪክ ይቀመጡ 1/ በመተከልን ከተቋቋመው ኮማንድ ፖስት አባላት ውስጥ አንዳንዶቹ ሃላፊነታቸውን አልተወጡም፣ 2/ የመተከል ጉዳይ ገና ብዙ አመራሮችን ይነካል፤ የህዝብ ጉዳት ሊያመጣብን ይገባል፣ 3/ ካማሽ እና አሶሳ ዞን የተፈጠረውን ችግር በመገምገም በቀላሉ መፍታት ችለናል ነገር ግን የመተከል ችግር ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ከድምጸ ወያኔ ቴሌቪዥን ጋር ሲሰሩ ስለነበረ ሳይፈታ ቆይቷል፣ 4/ ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳባቸው የምክር ቤቱ አባላት ጉዳይ ቀደም ሲል በተደጋሚ መፍትሔ እንዲሰጠው ጠይቀናል በክልሉ ምክር ቤት የጁንታውን ሴራ የሚያራምዱ አባላት አሉ፣ 5/ በዞኑ የጸጥታ ሀይሉን ሥራ ውጤታማ ለማድረግ ሌሎች ቀሪ የግጭቱ ተሳታፊ የምክር ቤት አባላትም ካሉ እየፈተሽን ለህግ ካላቀረብን የመተከልን ችግር መፍታት ያዳግተናል። 6/ እንደህዝብ ተወካይ ከማህበራዊ ሚዲያ ከምናገኘው መረጃ ባሻገር ስለመረጠን ህዝብ በቂ እውቀት ሊኖረን ይገባል፣ 7/ ችግሩ ለክልላችንም ሆነ አገራችንን የሚያሳፍር ጉዳይ በመሆኑ ከጁንታው ጋር አብሮ እንዲቀበር መስራት አለብን፣ 8/ የጸጥታውን ዘርፍ በተደጋጋሚ ገምግመን ችግሩን ብንደርስበትም ተሸፋፍኖ አልፏል፣ 9/ የችግሩ ምንጭ አመራሩ በጉዳዩ መሳተፉ ነው፣ 10/ ህብረተሰቡ በየቦታው ግጭት ሳይከሰት አስቀድሞ ሲጮህ ነበር፣ 11/ ህዝባችንን የምንታደገው በችግሩ የተሳተፉትን የምክር ቤት አባላትን ጭምር አሳልፈን በመስጠት ቆራጥ እርምጃ በመውሰድ ብቻ ነው፣ 12/ ምክር ቤቱ በመተከል ጉዳይ አስቸኳይ ጉባኤ መጥራት ከነበረበት ጊዜ ዘግይቷል፣ 13/ በአስቸኳይ ጉባኤው ያልተገኙ በርካታ የምክር ቤት አባላት አሉ፣ 14/ የመተከል ጉዳይ አሳፋሪ ነው፤ ተጨማሪ ሞት እና መፈናቀል እንዳይከሰት እና ከታሪክ ተወቃሽነት መውጣት አለብን የሚል ሀሳብ አንስተዋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply