የአማራን ህዝብ ማወረድ ኢትዮጵያን ማዋረድ ነው ሲሉ የጅግጅጋ ዪኒቨርሲቲ የህግ መምህር እና አክቲቪስት ሙክታር ኡስማን ተናገሩ                  አሻራ ሚዲያ…

የአማራን ህዝብ ማወረድ ኢትዮጵያን ማዋረድ ነው ሲሉ የጅግጅጋ ዪኒቨርሲቲ የህግ መምህር እና አክቲቪስት ሙክታር ኡስማን ተናገሩ አሻራ ሚዲያ…

የአማራን ህዝብ ማወረድ ኢትዮጵያን ማዋረድ ነው ሲሉ የጅግጅጋ ዪኒቨርሲቲ የህግ መምህር እና አክቲቪስት ሙክታር ኡስማን ተናገሩ አሻራ ሚዲያ ህዳር 29/2013 ዓ.ም ባህር ዳር ስለ አማራ ህዝብ መገፋት ዘወትር የሚቆረቆሩት፤ ስለ አማራ ህዝብ መሞትና መፈናቀል የሚጽፉት እና የሚመሰክሩት ፤ ስለ አማራ ህዝብ ታሪካዊና ሁለንተናዊ ጀግንነትና ሀገር ወዳድነት ዘወትር የሚናገሩት የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የህግ መምህር እና አክቲቪስት ሙክታር ኡስማን ከአሻራ ሚዲያ ጋር ባደረጉት የስልክ ቃለ ምልልስ እንደተናገሩት የአማራ ህዝብ ሀገርን ከሀገር በፊት የመሰረተ እና ለሌሎች ህዝቦችም አስተማሪ የሖነ ነው ብለዋል፡፡ በአማራ ህዝብ ላይ ባለፉት አርባ ዓመታት የተዘራው ሀሰተኛ የጥላቻ ትርክት እና በህገ መንግስታዊ ስርዓት የተደገፈ ጭቆናን ያስተናገደ ሲሆን አሁን ላይ ትልቁ የጥላቻ ሰንኮፍ የእየተነቀለ በመሆኑ የአማራ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ህዝቦችም ከገዳይነትና ከተገዳይነት ስሜትና አስተሳሰባቸው ይቆጠባሉ ብለዋል፡፡ በዚህ ሰዓት እና ባለፉት አርባ ዓመታት ብቻ ሳይሆን ከእውነት እስከ መቼም ቢሆን ከአማራ ህዝብ ጋር መቆም ከእውነት ጋር መቆም መሆኑን ሁሉም ሊያውቀው የሚገባ እና በተግባር የታየን እውነት መመስከርና ከእውነት ጋር መቀጠል እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ፤ የአፍሪካ ህዝብ እና መላው የዓለም ህዝብ ሊረዳው ይገባል ሲሉ ሀሳባቸውን ሰንዝረዋል፡፡ ‹‹ለመጭዋ ኢትዮጵያ ምን አይነት አስተዳደራዊና ህጋዊ የአሰራር ማዕቀፎች ቢኖር…? መቢል ከአሻራ ሚዲያ ለተነሳላቸው ጥያቄ ሙክታር ‹‹ ትህነግ በአማራ ህዝብ ላይ በህግና ህገ መንግስታዊ ሰነድ የተደገፈ አድሎዓዊ አስተዳደር ሲያራምድ ነበር›› ያሉ ሲሆን ለአብነትም የህገ መንግስቱን ‹‹አንቀጽ 25 ፡- ሰው ሁሉ በህግ ፊት እኩል ነው›› ፡፡ይልና የአማራን ህዝብ በእኩል አለማየቱን ያስረዳሉ፡፡ በተያያዘ ‹‹አንቀጽ 42፡- ሁሉም ዜጋ የመምረጥና የመመረጥ መብት አለው››፡፡ የሚለው በሀረር የሚኖሩ አማራዎች ከሀደሬው ቀጥለው በህዝብ ቁጥር አብላጫውን እንደሚይዙ እና በክልል እና ከተማ አስተዳደር ምርጫ ግን ዋናው ተመራጭ ሀደሬ ሆኖ ሁለተኛው ተመራጭ ኦሮሞ እንዲሆን የሚደረግበት አግባብ በመኖሩ ህገ መንግስታዊ ማሻሻያው አጽኖት ሊደረግበት ይገባል ብለዋል፡፡ እንደ ሙክታር ገለጻ ህገ መንግስቱ ሉዓላዊነት የሰጠው ለሀገሩቱ እና ለዜጎች ሳይሆን ለብሄር ብሄረሰቦች በመሆኑ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ተገዶ በብሄር እንዲወከል እንደተደረገ እና ኢትዮጵያዊነትን አውጥቶ እንዲጥል ተደርጓል ብለዋል፡፡ ከተወሰኑት የሚከተለውን አደረግሁ ባቸው። ግን ዪትዩቡ ሪዳይሬክት አያረግም ዘወትር አዳዲስ መረጃ እንዲደርስዎ https://t.me/asharamedia24 በመጫን ይቀላቀሉን። ዩትዩብ፥ https://bit.ly/33XmKro ላይክ እና ሰብስክራይብ ያድርጉን ዘጋቢ፡- ማርሸት ጽሀው

Source: Link to the Post

Leave a Reply