You are currently viewing የአማራን ህዝብ የከዱትን አሳማ ብሄረተኞችን በደንብ ካስተዋልኩ ብኋላ ግንቦት ሰባትን/ኢሳትን እንዲሁም የቀድሞዉ የአንድነት ፓርቲን ይቅርታ ለመጠዬቅ እያሰብኩ ነዉ::. ለምን አትሉኝ??? –…

የአማራን ህዝብ የከዱትን አሳማ ብሄረተኞችን በደንብ ካስተዋልኩ ብኋላ ግንቦት ሰባትን/ኢሳትን እንዲሁም የቀድሞዉ የአንድነት ፓርቲን ይቅርታ ለመጠዬቅ እያሰብኩ ነዉ::. ለምን አትሉኝ??? –…

የአማራን ህዝብ የከዱትን አሳማ ብሄረተኞችን በደንብ ካስተዋልኩ ብኋላ ግንቦት ሰባትን/ኢሳትን እንዲሁም የቀድሞዉ የአንድነት ፓርቲን ይቅርታ ለመጠዬቅ እያሰብኩ ነዉ::. ለምን አትሉኝ??? —————– ሸንቁጥ አየለ ——- 1.የአንድነት ፓርቲን በአንድ ነገር ደጋግሜ ስወቅሰዉ ነበር::ይሄዉም አማሮች በመላ ሀገሪቱ ሲጨፈጨፉ “አማራ ተጨፈጨፈ ብላችሁ ሪፖርት አታድርጉ::ኢትዮጵያ ትፈርሳለች” የሚል አቋም ስለነበረዉ ነዉ:: እንዴዉም አንድ ጊዜ ስለ ጉራ ፋርዳ አማራ ተፈናቃዮች 1000 አንድ ገጽ (ሽህ ገጽ) ሰነድ አዘጋጅተን የተቃዋሚ ፓርቲዎች መግለጫ እንዲያወጡ ብንጠይቅ የአንድነት ፓርቲ አላወጣም አለ::ሰዉ ልከን አስጠዬቅነዉ::እሱም “አማራ ተፈናቀለ ካልን ሀገር ይፈርሳል::እኛንም የአማራ ፓርቲ ይሉናል” ሲል መለሰ::ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እከዛሬ ድረስ የአንድነት ፓርቲ እና በወቅቱ ይሄን የወሰኑ ሰዎችን በማገኘዉ አጋጣሚ እወቅሳለሁ:: 2.በወቅቱ ከላይ የተባለዉ ተመሳሳይ ሰነድ (1000 ገጽ) ሰነድ ዉጭ ሀገር ተልኮ አሜሪካን ለሚገኘዉ የኢሳት ቴሌቪዥን እንዲደርሰዉ ተደረገ::ኢሳትም የአማራ ስም አንዳች መጥቀስ ስላልፈለገ አማርኛ ተናጋሪዎች ተፈናቀሉ ብቻ ብሎ በደምሳሳዉ አለፈዉ:: በሌላ ወቅት እነሱ ገንዘብ ለመሰብሰብ በሚያመቻቸዉ መልክ ስለ አማርኛ ተናጋሪ ተፈናቃዮች ይዘግቡ ነበር::አማሮች ተፈናቀሉ ማለት ግን ሀገር ያፈርሳል ባይ ነበሩ:: 3.ግንቦት ሰባት የፖለቲካ ፍልስፍናዉ እንደ 60ቹ ፓርቲዎች ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ተፈጠረች::አማራም ወራሪ እና ቅኝ ገዥ ህዝብ ነዉ የሚል መሆኑ ይታወቃል:: በኢትዮጵያ ዉስጥ ቅኝ ገዥ እና ቅኝ የተገዛ አለ የሚለዉ ፍልስፍና በአማራ ህዝብ ላይ ለሰላሳ አመታት የዘለቀ የዘር ጭፍጨፋ ዋና ምንጭ ብቻ ሳይሆን አማራ የዘር ጭፍጨፋ እየተደረገበት አማራ ተጨፈጨፈ ብላችሁ አትናገሩ ዝም በሉ የሚል አቋም እንዲያዝበትም ሁሉ ትልቁን ሚና ተጫዉቷል::ይሄንንም አቋም በዋናነት የአማራ ልጆች እራሳቸዉ በስፋት ያራመዱበት ምክንያት አማራዉ ጨፍጫፊ እና ሌሎች አካባቢዎችን ሄዶ የወረረ ስለሆነ የጁን ሊያገኝ ይገባዋል የሚል ታሳቢ ተይዞ ነዉ::የአማራ ልጆች እንኳን መላዉ ኢትዮጵያ የአባቶቻቸዉ ጥንታዊ ምድር እና ሀገር መሆኑን ክደዉ መሆኑ ነዉ:: በዚህም የተነሳ ግንቦት ሰባትን በብዙ መልክ ተችተንዋል::ጸረ አማራ ነው ብለንዋል::አማራ ሲጨፈጨፍ ዝም በሉ በማለቱ ብዙ ተከሷል:: 4.የግልም የመንግስትም ሚዲያዎች የአማራን ህዝብ ተፈናቀለ:ተሰደደ:ተገደለ ብለዉ ለመዘገብ በአንድ ላይ ተነጋግረዉ ያደሙ እስኪመስል መረጃ እየቀረበላቸዉ:ተፈናቃዮች ሄደዉ እያነጋገሯቸዉ እንኳን ዝም ጭጭ ማለት ቢመርጡ የህዝብ ድምጽ የሚሆን አማራጭ ሚዲያ ለመፍጠር ብዙ ተሞክሮ ነበር::የግል እና የመንግስት ሚዲያዎች በህዝብ መፈናቀል እና መገደል ላይ የሚያሳዩት ዝምታም ብዙ ሲወቀስ ነበር:: ——- አሁን ግን ከሁሉም የከፋዉን ነገር በህይወት ዘመኔ አስተዋልኩ::በህይወቴም ይሆናል ብዬ አስቤዉ የማላዉቀዉን ጉድንም ተመለከትኩ:: ይሄዉም የአማራ ህዝብ ጠበቃ እንሆናለን:የአማራ ህዝብ ድምጽ እንሆናለን ብለዉ በአማራ ህዝብ ስም የተደራጁ ሀይሎች የአማራን ህዝብ ጭፍጨፋ “ለጊዜዉ አትዘግቡት::አሁን ይሄ ቅድሚያ የሚሰጠዉ ጉዳይ አይደለም::ስለ አማራ ህዝብ መጨፍጨፍ አሁን ከተናገርን ኦህዴድ/ኦዴፓ ይቀዬማል::ከሁሉ መቀያዬም አንችልም::ስለዚህ አማራ እየተጨፈጨፈም ቢሆን ለጊዜዉ ዝም በሉ” ከማለትም ዘለዉ ይሄን የአማራ ህዝብ በወለጋ እና በመተከል መጨፍጨፍ ለመዘገብ የሚሞክሩትን ሚዲያዎች እና በግላቸዉ ስለ ህዝባቸዉ የሚጮሁ አንቂዎችን ተደራጅተዉ መሳደብ እና ስም ማጥፋት ላይ ተጠምደዋል::ለአማራ ህዝብ ተደራጁለት ያልናቸዉ በአማራ ህዝብ ላይ ተደራጅተዉበታል::አደረጃጀታቸዉን እና ሰልፋቸዉንም አማራን ከሚያርዱና ከሚያሳርዱ ጋር ሆኗል:: በዚህ ምክር ዉስጥ ማንም አብሯቸዉ ሊሰለፍ ይችላል::የግንቦት ሰባት ትርፍራፊ ኔትወርክ አማራን መጨፍጨፍ ይቁም ብሎ ለመናገር አሁን ጊዜዉ አይደለም ብሎ ሊመክራቸዉ ይችላል::የሆኖ ሆኖ የአማራን ህዝብ በመክዳት እንደ ጲላጦስ እጁን ታጥቦ ከአማራ አራጆች ጋር የተሰለፈዉ የአሳማ ብሄረተኛ ንቅናቄ ኔትወርክ በሙሉ ግን ህዝብን ድብን አድርጎ ክዶ ከህዝብ አራጆች ጋር ሰልፉን አድርጓል:: ————- የአማራን ህዝብ የከዱትን አሳማ ብሄረተኞችን በደንብ ካስተዋልኩም ብኋላ ግንቦት ሰባትን/ኢሳትን እንዲሁም የቀድሞዉ የአንድነት ፓርቲን ይቅርታ ለመጠዬቅ እያሰብኩ ነዉ::ምክንያቱም ግንቦት ሰባትም/ኢሳትም እንዲሁም የቀድሞዉ የአንድነት ፓርቲም አማራም ወራሪ እና ቅኝ ገዥ ህዝብ ነዉ የሚል መሆኑ ይታወቃል:: በኢትዮጵያ ዉስጥ ቅኝ ገዥ እና ቅኝ የተገዛ አለ የሚል ፍልስፍና ስላላቸዉ አማራ ይለቅ ምክንያቱም አሁን የጁን ነዉ ያገኘዉ ብለዉ ዝም ቢሉ ወይም ሌሎች ዝም እንዲሉ ቢያግባቡ አይገርምም::ያደረጉት የሚያምኑበትን ነው::የሚያምንበትን የሚያደርግ ደግሞ ሊወቀስ አይገባዉም::የማምንበት ይሄ ነዉ ብሎ በገሃድ ተናግሮ ተነስቷል እና:: እንዲህ አይነቱን መዉቀስ አይገባም::እንዲህ አይነትን መዉቀስ ማለት አላማህን እርሳ ብሎ መጠዬቅ ነዉ::አንድን ቡድን አላማህን እርሳ ማለት ደግሞ አግባብ አይሆንም:: —— አሁን መራራዉ ሀቅ በአማራ ህዝብ ስም ተደራጅተዉ አማራ የለም የሚሉ ሀይሎችን የአስተሳሰባቸዉ ማዕከል አድርገዉ “ለጊዜዉ አማራዉ በብዙ መቶ ሽህ ቢያልቅም ዝም በሉ:: አሁን የአማራ ጭፍጨፋ ይቁም ለማለት ጊዜዉ አይደለም:ኦህዴድን ከምናስቀይም አማራ ይለቅ ” ብለዉ ህዝቡን እንደከዱት መረዳቱ ላይ ነዉ:: ይሄን መራራ ሀቅ መረዳት ሲመጣ ነዉ እንግዲህ “በአማራ ስም የተደራጁት አማራ ለጊዜዉ ይለቅ ካሉ አማራ ቅኝ ገዥ ነበር/በዝባዥ ነበር ብለዉ የተነሱት እማ ምን እንዲሉ ነበር የሚጠበቀዉ?” የሚለዉ አንጀት ድብን:ነብስ ኩምትር የሚያደርግ ተጠይቅ የሚከተለው::መራራዉ የስላቅ መልስም “እነ ግንቦት ሰባትን እማ በዚህ አይነት ይቅርታ መጠዬቅ ይገባል” የሚል ነዉ:: —-

Source: Link to the Post

Leave a Reply