የአማራዉ ደም መፍሰስ እንዴት ይቁም? ከአማራ ጀግኖች አደራ የተላለፈ ጥብቅ መልዕክት ሕዳር 25 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር የአማራ ህዝብ ለኢትዮጵያ ሃገረ መንግስት…

የአማራዉ ደም መፍሰስ እንዴት ይቁም? ከአማራ ጀግኖች አደራ የተላለፈ ጥብቅ መልዕክት ሕዳር 25 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር የአማራ ህዝብ ለኢትዮጵያ ሃገረ መንግስት ምስረታ ያደረገዉ አበርክቶ የአንበሳዉን ድርሻ የሚይዝ እና አገር በተደፈረች ወይም ችግር ላይ በወደቀች ጊዜ ከማንም ቀድሞ ግንባር በመሰለፍ ደሙን የሚያፈስ ህግ አክባሪና ከማንኛዉም የአገራችን ብሄር ብሄረሰቦች ጋር ለዘመናት በፍቅር አብሮ የኖረ ህዝብ ነዉ።ባህርዳር በአገራችን የስርዓት ለዉጥ ለማምጣትም ከፊት በመሰለፍ ከፍተኛዉን መስዋዕትነት የሚከፍለዉ አማራ ቢሆንም የመሪነቱን ሚና ለሌሎች አማራ ጠል ግለሰቦች በይሉኝታ አሳልፎ በመስጠት የራሱን ህዝብ ለተደጋጋሚ የህልዉና አደጋ እየዳረገዉ ይገኛል። በአገራችን የስርዓት ለዉጥ በመጣ ቁጥር ስርዓቱን የሚረከበዉ አካል የመጀመሪያ ጠላት አድርጎ የሚወስደዉ አማራዉን ነዉ። የደርግ መንግስት ለዉጥ በተረከበ ማግስት አማራዉን ለማዳከምና ለማጥፋት በማሰብ የአማራዉን የነቃ የህብረተሰብ ክፍል ማጥፋትና የአማራዉን ሃብት መቀራመት የመጀመሪያ ስራዉ አድርጎ እንደፈፀመ ይታወቃል። በመቀጠልም የአማራዉን ድጋፍ ተንተርሶ ወደ ስልጣን የመጣዉ የትህነግ/ህወሃት ዘረኛ መንግስት የሃሰት ትርክት በመፍጠር አማራዉ በሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች እንዲጠላና እንደ ጠላት እንዲታይ በማድረግ ለ27 ዓመታት በመላዉ ኢትዮጵያ የሚገኘዉን አማራ ከኖረበት እና እትብቱ ከተቀበረበት ቀዬ ሃብቱንና ንብረቱን እየጣለ እንዲሰደድ እና በግፍ እንዲገደል አደረገ። በአሁኑ ሰዓትም የአማራዉን ቀናዒነት በመጠቀም የትግል አጋር አድርጎ ወደ ስልጣን የመጣዉ የኦሮሙማዉ ዘረኛ መንግስት የመጀመሪያ ስራ አድርጎ የወሰደዉ አማራዉ እረፍት አልባ እንዲሆን አማራዉ በሚኖርበት የአገሪቱ ክፍል በጅምላ እንዲገደልና እንዲፈናቀል ፕሮጀክት ቀርፆ ማስፈፀምን ነዉ። በኦሮሞ ዘረኞች የአማራ ደም እንደ ጅረት መፍሰስ የጀመረዉ በደርግ መንግስት ከአሶሳዉ ከ200 በላይ አማሮችን በአንድ ቤት ዘግቶ ከማቃጠል ጀምሮ እስከ አሁኑ የወለጋዉ የአማራ ደም እንደ ጅረት የሚፈስበት ጊዜ ነዉ። በተለይም የአማራዉ እልቂት በወለጋ ኦሮሚያ በክልሉ ልዩ ኃይልና በኦነግ ሸኔ ትብብር የሚካሄድና የማያባራ ሆኖ የቀጠለ ሲሆን በየቀኑ የሚያልቀዉን የአማራ ህዝብ ለመቁጠር እስኪያስቸግር ድረስ በቶሌ ቀበሌ በሶስት ሰዓት ብቻ ከተጨፈጨፉት 1500 በላይ እስክ ሰሞኑ በመጠለያ ዉስጥ ታግተዉ እስከተቃጠሉት ክ200 በላይ አማራዎች ያለርህራሄ እየተጨፈጨፉ ይገኛሉ። አሁን በዚህ ሰዓት በአንገር ጉተን ወረዳ የሚኖሩ አማራዎች በክልሉ ልዩ ኃይልና በኦነግ ሸኔ ትብብር በጅምላ እየተጨፈጨፉ ይገኛሉ። የቀጠለዉ ጭፍጨፋ ባለመቆሙ በህይወት የተረፉ አማራዎች ከዚህ የሞት መንደር (The Circle of Death) የሚያወጣቸዉ የነፍስ አድን ጥሪ ቢያሰሙም የሚደርስላቸዉ ሳይሆን ዘራቸዉ እንዳይተርፍ የሚጨፈጭፍ የክልሉ ገዳይ ኃይል ከቧቸዉ ይገኛል። እንዲሁም በምስራቅ ወለጋ ጊዳ ያና ወረዳ የሚኖሩ አማራዎች የሞት ቀለበት (Village of Death) ዉስጥ ገብተዉ የሞትን ፅዋ እየተጠባበቁ የሚገኝበት ሁኔታ ላይ ናቸዉ። በአሁኑ ወቅት ይህ ዘረኛ የኦሮሙማ መንግስት ስልጣኑን ተቆጣጥሮ በመንግስታዊ መዋቅር ታግዞ የሚፈፅመዉ አማራን የማጥፋት ተግባር በአጭር ጊዜ ዉስጥ የሚቆም አለመሆኑ እና የምዕራቡ ዓለም የአማራዉን እልቂት እያወቁም ለይምሰል እንኳን መግለጫ የማይሰጡበት ደረጃ ላይ ተደርሷል። ለዚህም ምክንያቱ የምዕራቡ ዓለም በህወሃት አገዛዝ ዘመን የአማራ ህዝብ ለአገሩ ያለዉን ቀናዒነትና አርበኝነት መስበር ባይችሉም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መስበር የሚቻለዉ በዚህ ዘረኛ የኦሮሙማዉ መንግስት አማካኝነት መሆኑን በማመን ነዉ። በተጨማሪም አማራዉ እርስ በእርሱ እንዳይተማመን እና በአንድነት ራሱን እንዳይከላከል በጎጠኝነት አረንቋ ዉስጥ እንዲገባ ከፍተኛ በጀት ተመድቦና ፕሮጀክት ተቀርፆ በስራ ላይ ዉሏል። ይህ የሚያሳየዉ አማራዉ በምን ያህል የከፋ የህልዉና አደጋ ላይ እንደሚገኝ ነዉ። ይህን በመንግስታዊ መዋቅር እየታገዘ የሚፈፀም አማራዉን የማጥፋት ፕሮጀክት አሁን ላለዉ ዘረኛ መንግስት እንዲያስቆምልን መጠየቅ በሌላ አካል የተፈፀመ እንዲመስል ድጋፍ መስጠት ካልሆነ በስተቀር ዉጤቱን እንደማይቀይረዉ ድርጅታችን በጽኑ ያምናል። የአማራ ጀግኖች አደራ የሚከተሉትን ጥሪዎች ለአማራ ህዝብ ያስተላልፋል። 1. ማንኛዉም አማራ ከተቋቋመዉ የአማራ ፋኖ አንድነት ማህበር ጎን በመሰለፍ የሚጠበቅበትን አስተዋፆ እንዲያደርግ እንጠይቃለን 2. ለኦሮሙማዉ ዘረኛ መንግስት ተላላኪ በመሆን አማራዉን እጅ ተወርች አስሮ እንዳይደራጅና እራሱን እንዳይከላከል ያደረገዉን ነቀርሳ ብዓዴንን የአሁኑ የአማራ ብልፅናን ከስሩ ነቅሎ ለመጣል ሁሉም አማራ በአንድነት እንዲነሳ እንጠይቃለን 3. በአሁኑ ወቅት አማራዉ በአገሩ እንደ ሌላ ዜጋ የሚታይበትና በየትኛዉም የኢትዮጵያ ክፍል የመንቀሳቀስ፤ የመኖር እና ሃብት ንብረት የማፍራት መብት የሌለዉ እና በመንግስታዊ መዋቅር ህልዉናዉ አደጋ ላይ የወደቀበት በመሆኑ አማራዉ ራሱን ከመጥፋት ለመታደግ የመጨረሻ አማራጭ የሆነዉን ስር ነቀል የስርዓት ለዉጥ ለማምጣት መላዉ አማራ ለሁለገብ ትግል ራሱን ዝግጁ እንዲያደርግ እንጠይቃለን 4. በመላዉ ዓለም የሚገኙ የአማራ ድርጅቶች በተናጠል በሚደረግ ትግል የሚመጣ ለውጥ አለመኖሩን በመገንዘብ የተቀናጀና ዉጤታማ ትግል ለማድረግ የጋር ግብ እና ርዕዮተ ዓለም በመንደፍ በአንድነት እንዲሰሩ እናሳስባለን 5. ለጊዚያዊ ጥቅም በነቀርሳዉ ብዓዴን ዉስጥ እና አማራን በጎጥ ለመከፋፈል በተቀረፀዉ ፕሮጀክት ስር ሆናችሁ የአማራዉን የህልዉና ትግል እያጨናገፋችሁ የምትገኙ የአማራ ልጆች አቋማችሁን በማስተካከል ከዚህ እኩይ ተግባራችሁ እንድትታቀቡ እናሳስባለን 6. የአማራዉ ጅምላ ፍጅት፤ መፈናቀል እና መሰደድ ባልደረሰባቸዉ አካባቢዎች የምትገኙ የአማራ ምሁራን፤ ባለሃብቶች እና የማህበረሰብ አንቂዎች አሁን በሌላ አካባቢዎች የሚታየዉ የህልዉና አደጋ በቅርብ ጊዜ በሁሉም አካባቢ የሚፈፀም መሆኑን አዉቃችሁ ለሚደረገዉ የአማራን ህልዉና የመታደግ ሁለገብ ትግል የበኩላችሁን አስተዋፆ እንድታደርጉ እንጠይቃለን !ክብር ዋጋ ለከፈሉ የአማራ ጀግኖች! የአማራ ጀግኖች አደራ፣ ለንደን፣ ዩናይትድ ኪንግደም ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:-Youtube:- https://www.youtube.com/…/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJ…/Facebook:- https://www. Ashara Media – አሻራ ሚዲያ ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24 Facebook (https://www.facebook.com/asharamedia24%E1%89%B4%E1%88%8C%E1…) Log in or sign up to view See posts, photos and more on Facebook.

Source: Link to the Post

Leave a Reply