የአማራ ህብረት የበርሊን ግብረ ኃይል በአማራ ላይ እየተፈጸመ ያለው የዘር ፍጅት እንዲቆም ጠይቋል፤ የወለጋ ሰማዕታትን በሻማ ማብራት ስነ ስርዓት እንዲዘከሩ አድርጓል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አ…

የአማራ ህብረት የበርሊን ግብረ ኃይል በአማራ ላይ እየተፈጸመ ያለው የዘር ፍጅት እንዲቆም ጠይቋል፤ የወለጋ ሰማዕታትን በሻማ ማብራት ስነ ስርዓት እንዲዘከሩ አድርጓል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 2 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በጀርመን በርሊን ከተማ ጥቁር በመልበስ ሀዘናችንን እናሰማ በሚል የአማራ ህብረት የበርሊን ግብረ ኃይል ባደረገው ጥሪ መሰረት በርካቶች በሰዓቱ እና በስፍራው ተገኝተው ኦሮሚያን ጨምሮ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በግፍ እና በጅምላ እየተጨፈጨፉ ላሉ አማራዎች ሀዘናቸውን ገልጸዋል። በአማራ ላይ እየቀጠለ ያለው ጭካኔ የተሞላበት የጅምላ ዘር ማጥፋት በአስቸኳይ እንዲቆምም ጠይቀዋል። አንድ ሆኖ የዘር ማጥፋት ወንጀልን ማውገዝ እና መታገል የግድ ስለመሆኑም ሰልፈኞች በመፎክራቸው ገልጸዋል። STOP AMHARA GENOCIDE!

Source: Link to the Post

Leave a Reply