የአማራ ህዝባዊ ሀይል (ፋኖ) እና አማራ ተማሪዎች ማህበር በግንባር ለተሰዉ ጀግኖች ቤተሰቦች የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ። ታህሳስ 04/2014/አሻራ ሚዲያ/ የአማራ ህዝባዊ ሀይል(ፋኖ) እናየ…

የአማራ ህዝባዊ ሀይል (ፋኖ) እና አማራ ተማሪዎች ማህበር በግንባር ለተሰዉ ጀግኖች ቤተሰቦች የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ። ታህሳስ 04/2014/አሻራ ሚዲያ/ የአማራ ህዝባዊ ሀይል(ፋኖ) እናየአማራ ተማሪዎች ማህበር ከአማራ አደጋ ጊዜ ፈንድ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ ለአማራ ህዝብ ነፃነት ሲሉ ከጠላት ጋር ጉሮሮ ለጉሮሮ ተናንቀው በጀግንነት ለተሰዉ በአዴት ከተማ ለሚገኙ የወንድማማች ቤተሰቦችየገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል ። የአማራ ህዝባዊ ሀይል (ፍኖ) አስተዳደርና ፍይናስ ሀላፊ የሆኑት አቶ ተስፈየ ታሪኩ ህዝብ ህልዉና አደጋ ላይ ሲወድቅ ሀገር ስትደፈር እህቶቻችን እናቶቻችን ሲደፈሩ ሀገር እንዳልነበረች ስትሆን ከምናይ ብለዉ በአማራ ህዝባዊ ሀይል ስር ሁነዉ የተሰዉ ጀግኖቻችን ናቸው ብለዋል።… አክለዉም ሀገር እና ትዉልድን ለመታደግ የሚከፈል መስዋዕትነት በሌላ በኩል ደግሞ ሰማትነት ነዉ ያሉ ሲሆን አማራ ለመታደግ ከፍተኛ መሰዋእትነት መክፈላቸዉን ገልፀዉ በአቀስታ ግንባር ጠላትን ድባቅ በመምታት ለተሰዉት ወንድማማቾች ፋኖ ይበልጣል ሀይሉ እና አለነ ሀይሉ 50ሽህ ብር በተጨማሪም ለአስር አለቃ ኤፍሬም አጥናፋ ድጋፍ ማድረጋቸዉን ገልፀዋል። የአማራ ህዝባዊ ሀይል(ፍኖ) በሁሉም ግንባር ለተሰዉ ፍኖ ቤተሰቦች አባላቱን በማስተባበር በዘላቂነት ድጋፍ ያደርጋል ብሏል ። ሌላኛው ለተሰዉ ጀግኖች ድጋፍ ያደረገው የአማራ ተማሪዎች ማህበር ከአማራ አደጋ ጊዜ ፈንድ ባገኘዉ ድጋፍ ነዉ የድርጅቱ ተጠሪ አቶ አብረሃም አበበ ለአማራ ብሎም ለኢትዮጵያ ሲሉ ቤተሰቦቻቸውን ትተዉ ለኛ ሲሉ ህይወታቸውን በጀግንነት ሰዉተዋል ብለዋል አክለዉም እነዚህን እና መሰል በግንባር የተሰዉቱን ሁሉም ልጆቻቸውን የመንከባከብ ሃላፊነት አለበት ያሉ ሲሆን ለያንዳንዳቸው 10ሽህ ብር ድጋፍ አድርገናል ብሏል በቀጣይም በዘላቂነት እንደሚያግዝ ነዉ የገለፀዉ በክልሉ በሁሉም ግንባሮች ለተሰዉ ጀግኖች ድጋፍ እንደሚደርግ አስታዉቋል ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply