You are currently viewing የአማራ ህዝባዊ ማህበራት  ፎረም በአማራ ፋኖ አንድነት ምክር ቤት ምስረታ  የአቋም መግለጫ:-  ሕዳር 17 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር “ጀግኖችን አመስግኖ ሽልማት ሰጥቶ እው…

የአማራ ህዝባዊ ማህበራት ፎረም በአማራ ፋኖ አንድነት ምክር ቤት ምስረታ የአቋም መግለጫ:- ሕዳር 17 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር “ጀግኖችን አመስግኖ ሽልማት ሰጥቶ እው…

የአማራ ህዝባዊ ማህበራት ፎረም በአማራ ፋኖ አንድነት ምክር ቤት ምስረታ የአቋም መግለጫ:- ሕዳር 17 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር “ጀግኖችን አመስግኖ ሽልማት ሰጥቶ እውቅና ከመስጠት ይልቅ የፋኖ ስም ሲነሳ የሚያንዘረዝራቸው ጠላቶች ፋኖን ለማጥፋት ረጅም ጉዞ ተጉዘዋል።” የአማራ ህዝባዊ ማህበራት ፎረም ከአማራ ፋኖ አንድነት ምክር ቤት ጋር በጋራ ለመስራት የአጋርነት መግለጫ:_ በመጀመሪያ ለአማራና ለኢትዮጵያ ህዝብ እውነተኛ ደጀን የሆነው ፋኖ ወደ አንድነት በመምጣቱ እንኳን ደስ አለን፣ እንኳን ደስ አላችሁ፣ ለመላው የአማራ ፋኖዎችም እንኳን ለታሪካዊ የምስረታ ጉባኤችሁ እንኳን አደረሳችሁ። ለእናት ሀገር ኢትዮጵያ ታላቅ ህዝብ፣ ለአማራ ደምና ላባቸውን ያፈሰሱ፣ ሥጋቸውን የሚቆርሱ፣ አጥንታቸውን የከሰከሱ፣ ለክብር የተሰለፉ የአማራ ፋኖዎች ናቸው፡፡ ዓላማን በጀግንነት የሚደግም፤ ዓላማቸውን ለጊዜያዊ የነፍስ ፍላጎት፤ ለሥጋ ምኞትና ድሎት ሳይሆን ለህዝብ የሚኖሩ ሀገር ወዳድ ጀግኖችም ናቸው። ከሦስት ሺህ ዘመናት በላይ በደምና አጥንት፤ በጥቁር ህዝቦች ታሪክ ወደር የማይገኝለት መስዋዕትነት፣ ከሰንደቋ ሳትወርድ የኖረችው ዓርማችንን ህልውና የማስቀጠል ጉዳይ የዛሬም የነገም ግዳጃቸው መሆኑን አምነው ለአማራ ህዝብ ዘብ ለኢትዮጵያ ህዝብ መከታ የሆነ የጦር ሜዳ ጀብደኞች የአማራ ፋኖዎች ናቸው። የሀገር ፍቅራቸው የእውነት፣ ሰንደቅ ዓላማቸውን በልብ ቃልኪዳን የታተመ፣ ሀገርን በምትወክለው አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ አርማ ፊት ለፊት ምለው ቃላቸውን በመጠበት ሀገር አፍራሽ አሸባሪውን ከሀዲ ትህነግ ? የተባበሩ፤ ዛሬም የአማራና የኢትዮጵያ ህዝብን ጠላት እየቀበሩ ያሉ የአማራ ፋኖዎች ክብር ይገባቸዋል፡፡ ያለ መካካድ ቃል ኪዳን ብቻ ሳይሆን፣ ለጓድ ውድ ህይወትን እስከ መስጠት የዘለቀ፣ የማይፈርስ፣ የማያረጅ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ መንፈሳዊ እምነት ቅርስ ባለቤቶችም ናቸው። ፋኖነትን ከፍ ሲል ኢትዮጵያዊነት ዝቅ ሲል አማራነት ነው፡፡ በነፍጠኛ ትምክተኛ ስድብ ቅስማቸው ሳይሰበር፣ ክፉ በገጠመን ቁጥር ደከሙ ሲባል እየበረቱ፣ አነሱ ሲባል እልፍ እየሆኑ ወደቁ ሲባሉ ግርማ ጨምረው እየበዙ፣ አጠፋናቸው የሚሉትን ታሪክ ያደረጉ ጀግኖች የአማራ ፋኖ አባላት ናቸው፡፡ የውስጥ ባንዳ የውስጥ ተረኛ ወራሪ እንግዳ በትኛውም ኃይል ቢመካ መስመር ካለፈ በብርቱ ክንዳችን የንብ ዓይነት ህብረታቸው አጠናክረው ጠላትን የውርደትና ሞት ሊቀምሱት የተዘጋጁ ሐይሎችም ናቸው። በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ የሰሜን ዕዝ ውስጣዊ ክህደት ሲፈፅም የአማራ ፋኖ ትህነግን በሣምንታት ውስጥ ከሰውነት ወደ አይጥነት የቀየሩ ባለታሪኮችም ናቸው፡፡ እነዚህ ጀግኖችን አመስግኖ ሽልማት ሰጥቶ እውቅና ከመስጠት ይልቅ የፋኖ ስም ሲነሳ የሚያንዘረዝራቸው ጠላቶች ፋኖን ለማጥፋት ረጅም ጉዞ ተጉዘዋል። ዳሩ ግን በአማራነት ጠንካራ ስነልቦና የተገነባው ፋኖ ህዳር 13 /2005 ዓ.ም በጎንደር ክፍለ ህገር የአማራ ፋኖ አንድነት ምክር ቤት አቋቁሟል። በዚህ ምስረታ ጉባኤ የሸዋ፣ የወሎ፣ የጎንደር፣ የጎጃም ፋኖዎች ተገኝተዋል፡፡ ጠላትን ያስደነገጠ የአቋም መግለጫም አውጥተዋል፡፡ ይህ የምስረታ ጉባኤ የአማራ ህዝባዊ ማህበራት ፎረም የአማራ ፋኖ ወደ አንድነት እንዲመጣ ሲሰራ የነበረው ስራም አንድ እርምጃ ወደፊት እንዲራመድ አድርጓል፡፡ ፎረም ለአማራ ህዝብ ትንሳኤ ለኢትዮጵያ ሉአላዊነት መጠበቅ ታላቅ ስራ የሚሰራ አደረጃጀት መመስረቱን በማመን ከአማራ ፋኖ አንድነት ምክር ቤት ጋር በአጋርነት ለመስራት ተዘጋጅቷል፡፡ ሌሎች በምክር ቤቱ ያልተካተተቱ የፋኖ አደረጃጀቶችም ወደ ምክር ቤቱ በፍጥነት ልዩነትን ውበት በማድረግ እንዲቀላቀሉ ፎረሙ ጥሪ ያቀርባል። መላው የኢትዮጵያ ህዝብ፤ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም የኢፌዲሪ መንግስትና የአብክመ ከዚህ መዳኛ አደረጃጀት ጎን እንድትቆሙ በድጋሚ ጥሪችን እናስተላልፋለን፡፡ ፋኖነት አማራዊነት ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያዊነት ነው። የአማራ ህዝባዊ ማህበራት ፎረም ህዳር 17/2015 ዓ.ም ባህርዳር- ኢትዮጵያ ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply