የአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) በሸዋ ሜዳ (ጅሩ) እና በጎጃም ብቸና ስልጠናቸውን አጠናቀው ተመርቀዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 27 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ…

የአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) በሸዋ ሜዳ (ጅሩ) እና በጎጃም ብቸና ስልጠናቸውን አጠናቀው ተመርቀዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 27 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) የአማራ ህዝብ እንደ ህዝብ የመኖር መብቱ ተከብሮለት ሌሎች መሰረታዊ የመብት፣ ጥቅም፣ ፍላጎት እና የአጽመ ርስት ጥያቄዎቹ ይመለሱ ዘንድ ተደራጅቶ ከአማራ ልዩ ኃይል፣ከሚሊሾችና ከሀገር መከላከያ ሰራዊትና ከህዝቡ ጋር በመሆን አኩሪ ተጋድሎ እየፈጸመ መሆኑ ይታወቃል። በተለያዩ የአማራ አካባቢዎች መሰባሰቡ፣ መሰልጠኑና መደራጀቱ ተጠናክሮ ቀጥሎ በርካታ የሚሆኑ የአማራ ፋኖ ሰልጣኞች በሸዋ ሜዳ(ጅሩ) እና በጎጃም ብቸና ወገናቸውን ለመታደግ በክብር ተመርቀዋል። በጀግናው አርበኛ ራስ አበበ አረጋይ የትውልድ ቦታ ሸዋ ሜዳ (ጅሩ) በእነዋሪ ከተማ የመጀመሪያ ዙር ሰልጣኝ የአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) አባላት ናቸው ወታደራዊ ስልጠናቸውን በብቃት አጠናቀው የተመረቁት። በተመሳሳይ ህዳር 27 ቀን 2014 በጀግናው አርበኛ በላይ ዘለቀ የትውልድ ቀዬ ብቸና ላይ የአማራ ሕዝባዊ ኃይል (ፋኖ) በርካታ ፋኖዎችን በብቃት አሰልጥኖ አስመርቋል። ለተመራቂዎችም ከፊታችን ብዙ ይጠብቀናል፤ ልክ እንደ ጀግናው በላይ ዘለቀ ከጠላቶቻችን በላይ ዘልቀን፣ ልቀን መገኘት ይኖርብናል_በመድረኩ የተላለፈ መልዕክት ነው። የእነ እምዬ ምኒልክን፣ የእነ አጼ ቴዎድሮስን፣ የእነ በላይ ዘለቀን፣ የእነ ንጉስ ሚካኤል አሊንና የሌሎች አንበሶች እና አናብስቶችን ሀገርና ወገንን ከውስጥና ከውጭ ጠላት የመታደግ የአርበኝነት ኃላፊነትን መወጣት ጊዜውና ትውልዱ የሚጠይቀው ጉዳይ መሆኑ ግልጽ ነው። አማራ እና ሌሎች ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን የውጭ ጠላትንና ባንዳን የሚያንበረክኩበት እንጅ እጃቸውን በመስጠት ከቀደምት ጀግኖች የተረከቧትን ሀገር የሚያስረክቡበት የተሸናፊነት ታሪክ የላቸውም! አማራ ላይጨርስ አይጀምርም! አማራ አሁንም ተደራጅ ሰልጥን ታጠቅ!

Source: Link to the Post

Leave a Reply