የአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) በደብረ ብርሃን ከተማ ሲያሰለጥናቸው የነበሩ ከ800 በላይ አባላቱን አስመርቋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 2 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበ…

የአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) በደብረ ብርሃን ከተማ ሲያሰለጥናቸው የነበሩ ከ800 በላይ አባላቱን አስመርቋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 2 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) በደብረ ብርሃን ከተማ ሲያሰለጥናቸው የነበሩ ከ800 በላይ አባላቱን በደብረ ብርሃን አስመርቋል። ህዝባዊ ኃይሉ ጥር 1 ቀን 2014 በደብረ ብርሃን ከተማ ላለፉት ሶስት ወራት ሲያሰለጥናቸው የነበሩ ከ800 በላይ የሚሆኑ ሰልጣኞችን ነው በድምቀት ያስመረቀው። በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የአማራ ሕዝባዊ ኃይል (ፋኖ) የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አስረስ ማረ ዳምጤ እና የህዝባዊ ኃይሉ ወታደራዊ ዘርፍ ኃላፊ ሀምሳ አለቃ ታዬ ብርሃኑን ጨምሮ ሌሎች እንግዶችም መገኘታቸው ተገልጧል። አሸባሪ እና ወራሪዎችን ግምባር ድረስ በማቅናት ሲፋለሙ በክብር ለተሰው ፋኖዎች እና በተለያዩ አውደ ውጊያዎች ተሰልፈው ለተዋደቁ ሰማዕታት ሁሉ የህሊና ፀሎት ተደርጎላቸዋል። የአማራ ሕዝባዊ ኃይል ለስልጠናው እና ለምረቃው መሳካት ለተባበሩ ሁሉ ምስጋናም አቅርቧል። በእለቱም አርቲስት አሸብር በላይ እና መብሬ መንግስቴን ጨምሮ ሌሎችም የዘርፉ ባለሙያዎች በምርቃቱ ተገኝተው ዝግጅቱን አድምቀው ስለመዋላቸው ተሰምቷል። በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይም ተመራቂ የአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) አባላት ወታደራዊ ትርኢት ማሳየታቸውና በመድረኩ መልዕክቶች መተላለፋቸው ተጠቁሟል። በተመሳሳይ የደቡብ ወሎ ፋኖ አስተባባሪ ፋኖ ኤርሚያስ አያሌው ለአሚማ እንደገለጸው የፊታችን እሁድ ጥር 8 ቀን 2014 በደሴ ከተማ ለ1 ወር ከ15 ቀናት የሰለጠኑ 200 ፋኖዎች ይመረቃሉ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply