
የአማራ ህዝባዊ ግንባር ትልቅ የዲፕሎማሲ ድል በጀርመን ፍራንክፈርት ማስመዝገቡ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 10/2015 ዓ/ም_አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ዕጅግ የተከበሩት ልዑል ዶ/ር አስፋወስን አስራት ካሳ የአማራ ህዝባዊ ግንባር የመላው አውሮፓ እና አፍሪካ የዲፕሎማሲ እና የፖለቲካ ስራውን ለመስራት ከሻለቃ ዳዊት ጋር ስምምነት ላይ ደርሰዋል። የግንባሩ የውጭ ድጋፍ አስተባባሪ የሆኑት ሻለቃ ዳዊት በጀርመን/ፍራንክፈርት ከዶክተር ልዑል አስፋው ወሰን ጋር ሐምሌ 9/2015 ዓ.ም ባደረጉት ምክክር ነው የመላው የአውሮፓና የአፍሪካ የዲፕሎማሲና የፖለቲካ ስራ ሊሰሩ የተሰማሙት። ዕዉቁ ልዑል ዶ/ር አስፋወሰን የግንባሩን ስራ ተቀብለው ለመስራት መስማማታቸው የዓለም አቀፍ ትግሉን ወደተለየ ከፍታ ለማሸጋገር የሚያስችል የዲፕሎማሲ ስራ ሆኗል። ለመሆኑ ዕዉቁ የተከበሩ ዶ/ር ልዑል አስፋወሰን አስራት ካሳ ማናቸው:- ዶ/ር ልዑል አስፋ ወሰን አስራት አዲስ አበባ በ1948 ተወለዱ። እዚያ በሚገኘው የጀርመን ትምህርት ቤት የጀርመን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያን በማለፍ በአውሮፓ በጀርመን ቱቢንገን እና በእንግሊዝ ካምብሪጅ ዪኒቨርስቲዎች ታሪክ እና ህግን ተምረዋል። የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በፍራንክፈርት በጎተ ዩኒቨርሲቲ ሠርተዋል። በጀርመን አገር ቆይታቸው ላይ በጋዜጠኝነት እና በፕሬስ ኦፊሰርነት አገልግለዋል። በአሁኑ ሰዓት ለአፍሪካ እና ለመካከለኛው ምስራቅ የንግድ አማካሪ በመሆን ይሰራሉ። በጀርመንኛ ቋንቋ አንቱታን ያተረፉላቸው ከአስር (10) በላይ መጽሐፍትን ያሳተሙ ሲሆን በተለይ ደግሞ “Manieren” “ስነሥርዓት” የተሰኘው መፅሐፋቸው በሃያሲዎቹ ዘንድ ከፍተኛ ዝናን አትርፎላቸዋል። የተለያዩ ሽልማቶችንም አስገኝቶላቸዋል። ለብዙ አመታት በአፍሪካ በተለይም በሀገራቸው ኢትዮጵያ ውስጥ አዲስ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ስርአት እንዲኖር ቁርጠኛ በመሆን በአውሮፓ ጆርናሎች ላይ በርካታ ጽሑፎችን አሳትመዋል። በጀርመን አገር እውቅና እና ሽልማቶች 2004: አደልበርት ቮን ቻሚሶ ለሥነ ምግባር ሽልማት 2010፣ የቱቢንገን ዩኒቨርሲቲ የክብር ሴናተር[16] እ.ኤ.አ. በ 2011 የዋልተር ሼል የፌዴራል ኢኮኖሚ ትብብር እና ልማት ሚኒስቴር ሽልማት፣ [17] 2015 ያዕቆብ Grimm ሽልማት 2016፣ የክብር መስቀል ከሪባን ጋር እ.ኤ.አ. 2019፣ የወርቅ ፍሌይስ ትዕዛዝ ናይት (የኦስትሪያ ቅርንጫፍ) የፌዴራል ኢኮኖሚ ትብብር እና ልማት ሚኒስቴር የኢኖቬሽን አማካሪ ቦርድ አባል፣ የጄ ደብሊው ጎተ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ተማሪዎች ምክር ቤት አባል፣ የ ORBIS AETHIOPICUS የባለአደራ ቦርድ መስራች እና ሰብሳቢ፣ የኢትዮጵያ ባህል ጥበቃና ማስፋፊያ ማህበር ኢ.ቪ. የባለአደራ ቦርድ ሰብሳቢ “ማህበር ፎር ሙዚየም በኢትዮጵ ስራዎችን በመስራት ሽልማቶችን ስለማግኘታቸው ተገልጧል።
Source: Link to the Post