You are currently viewing “የአማራ ህዝብ ሸኔ የሚል መደበቂያ ስም ከተሰጠው ገዳይ ቡድን እና ከአሸባሪው የትህነግ ኃይል ባሻገር በብልጽግና ስርዓት ጋባዥነት እና ይሁንታ በውጭ ወራሪ አገራት ጭምር እንዲወጋ፣ እንዲገደ…

“የአማራ ህዝብ ሸኔ የሚል መደበቂያ ስም ከተሰጠው ገዳይ ቡድን እና ከአሸባሪው የትህነግ ኃይል ባሻገር በብልጽግና ስርዓት ጋባዥነት እና ይሁንታ በውጭ ወራሪ አገራት ጭምር እንዲወጋ፣ እንዲገደ…

“የአማራ ህዝብ ሸኔ የሚል መደበቂያ ስም ከተሰጠው ገዳይ ቡድን እና ከአሸባሪው የትህነግ ኃይል ባሻገር በብልጽግና ስርዓት ጋባዥነት እና ይሁንታ በውጭ ወራሪ አገራት ጭምር እንዲወጋ፣ እንዲገደል እና እርስቶቹ እንዲወረሩ ተደርጓል፡፡” የአማራ ፋኖ አንድነት በሸዋ ሰ.ሜሪካ :- ሐምሌ 27/2014 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ከአማራ ፋኖ አንድነት በሸዋ በወቅታዊ ጉዳይ የተሰጠ መግለጫ:_ አባቶቻችን ለመላው ኢትዮጵያዊያን ምቹ ቤት እንድትሆን አድርገው በደም እና አጥንታቸው ያቆሟት ኢትዮጵያ ዛሬ ለአማራው ህዝብ ተራ ሆናለች፡፡ አንገት መድፊያ ፣ መሳቂያ እና መሳለቂያ ተደርጋለች፡፡ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ የበኩር ልጅ ለሆነው የጅምላ መቃብር ሆና ተሰርታለች፡፡ አልፎ ተርፎም በየቦታው ያለጠባቂ በአላፊ አግዳሚው እየተኮረኮመ ወላጅ እንደሌለው ህፃን አማራው ሲያነባ ኖሯል፡፡ አሁንም ቀጥሏል፡፡ ዛሬ ላይ በኢትዮጵያ ሰማይ ስር የሚገኙ እስር ቤቶች በሞላ የአማራው ማጎሪያ መጋዘን ሆነዋል፡፡ የአማራ ታሪካዊ ቅርሶች እርስቶች በወራሪው ትህነግ እና የገዥው ስርዓት የጡት ልጅ በሆነው የኦነግ ታጣቂ ኃይል ተወሯል፣ ወድሟል፣ ጠፍቷል ፡፡ አገራችን ኢትዮጵያ አሁን የገባችበት የእርስ በእርስ እልቂት ጦርነት እና የአማራ ህዝብ የዘር ማጥፋት ድርጊት ከገዥው ስርዓት ጌቶች እና ሎሌዎቻቸው እሳቤ የሚመነጭ እንጅ የሰፊው ህዝብ አለመሆኑን በውል ለይተናል፡፡ የአማራ ህዝብ ሸኔ የሚል መደበቂያ ስም ከተሰጠው ገዳይ ቡድን እና ከአሸባሪው የትህነግ ኃይል ባሻገር በብልጽግና ስርዓት ጋባዥነት እና ይሁንታ በውጭ ወራሪ አገራት ጭምር እንዲወጋ፣ እንዲገደል እና እርስቶቹ እንዲወረሩ ተደርጓል፡፡ ቅርሶቹ ወድመዋል፣ ታሪክ፣ እሴቱ እና ባህሉ ሆን ተብሎ እንዲበረዝ፣ እንዲጠፋና አሁን ደግሞ በኦዴድ ወረራ በኃይል እንዲተካ እየተደረገ ነው፡፡ ይህም አማራን በሁሉም አቅጣጫ እረፍት በመንሳት አገር የማፍረስ ውጥናቸውን ለማሳካት ገዥው ስርዓት እና ሌሎች የሚያደርጉት መፍጨርጨር አንዱ አካል ነው፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ለኢትዮጵያ የአገር ግዛት አንድነት እና ብሔራዊ ደህንነት እና ሰላይ ስንል በገዥው ፓርቲ እና አሽከሮቹ በመዋቀር ለዓመታት በአማራነታችን ይደርስብን የነበረውን እና እየተፈፀመብን ያለውን እልቆ ቢስ መከራና ግፍ እስኪያገሸግሸን በፍጹም ትዕግስት ተሸክመን ቆይተናል፡፡ ሆኖም ግን የምንፈልገው የኢትዮጵያ የግዛት አንድነት ብሐየራዊ ደህንነት እና ሰላሟ በአማራው ህዝብ እና ፋኖ ፍላጎት፣ እልቂት መከራና ግፍን በመሸከም ብቻ ሊመጣ እንደማይችል አረጋግጠናል፡፡ በቅቶናልም፡፡ አሁን ላይ የፋኖ የአማራ ህዝብና የኢትዮጵያ ቁጥር አንድ ጠላት በስልጣን ላይ የሚገኘው ገዥው ስርዓት መሆኑን ለመላው ህዝባችን ከመጠራጠር ወጥቶ እንዲገነዘብ እየገለጽን ፡- 1ኛ. በህግ ነጻ መሆናቸውን ከተረጋገጠ በኋላ በኃይል በባህር ዳር ሰባታሚት ማረሚያ ቤት ታግተው የሚገኙ ሁሉም የአማራ ፋኖዎች ባስቸኳይ ማለትም ይህ እስከ 29/11/2014 ዓ.ም ድረስ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የማይለቀቁ ከሆነ በአራቱም አቅጣጫዎች ህዝባዊ እምቢተኝነቱን በማቀጣጠል የስራ ማቆም አድማ ይደረጋል፡፡ 2ኛ. አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ማጎሪያ ቤቶች ያለሀጥያታቸው አማራ በመሆናቸው እና የአማራ ድምጽ ስለሆኑ ብቻ በስርዓቱ ታግተው እየተሰቃዩ የሚገኙ ፋኖዎች፣ ጋዜጠኞች፣ የማህበረሰብ አንቂዎች ጦማሪዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና አባላት፣ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና ሙህራን ባስቸኳይ እንዲለቀቁ እንጠይቃለን፡፡ ይህ የማይሆን ከሆነ ግን ህዝባዊ እምቢተኝነት አጠናክረን የምንቀጥል መሆኑን በአጽንኦት እናሳውቃለን፡፡ 3ኛ. ህግ ማስከበር በሚል ያለፈበት ፋሽን ለአማራ አንድነት እና ለኢትዮጵያ እንደሀገር መቀጠል የድርሻቸውን እየተወጡ የሚገኙትን የአማራ ህዝባዊ ኃይል/ፋኖ/ አመራሮችን እና አባላቱን በየጫካው ማሳደዱ ባስቸኳይ እንዲቆም እንጠይቃለን፡፡ 4ኛ. በኦሮሚያ የአማሮች ጭፍጨፋ እና የዘር እልቂት ፍፃሜዎች ለህግ ሊቀርቡና ወንጀሉ በመላው የአማራ አጽመ ርእስቶች ከቀበሌ ጀምሮ እስከ ላይኛው መዋቅር ድረስ በመንግስት ከፍተኛ ኃላፊት የተቀመጣችሁ አማራ ነን ባዮች ከላይ ያስቀመጥናቸው ጥያቄዎች እንዲመለሱ የማትሰሩ ከሆነና በተለመደው የገዥው ስርዓት አሽከር ሁናችሁ በመፅናት ለአማራው ዘር መጥፋትና አገር መፍረስ እንሰራለን የምትሉ ከሆነ በማንኛው ሰርዓት እና ቦታ የማያዳግም የኃይል እርምጃ የምንወስድባችሁ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ በአውራ ፓርቲነት አገሪቱን በኃይል እየገዛ ለሚገኘው የኦህዴድ ባለስልጣናት የሌለው የብአዴን ተላላኪ ኃይሎች ከላይ ያስቀመጥናቸውን ጥያቄዎች ባፋጣኝ የማትመልሱ ከሆነ በግልፅ ሁለንታናዊ የትግል አማራጮችን የምንጠቀም መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ በስተመጨረሻም ለአማራ ልዩ ኃይል፣ አድማ ብተና፣ መከላከያ ፖሊስና ሚሊሻ በቅድሚያ የአማራ ህዝብ እና ፋኖ ለሚያደርገው ሁለንተናዊ በአማራዊ ማንነታችሁ በጋራ ክብራቸው እንድትቆሙ ስንል በአፅኖት በታላቅ ወንድማዊ ክብር እንጠይቃለን፡፡ ሌላው የአማራ ህዝብ፣ የአማራ ፋኖ እና የተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ ለምንወስዳቸው ፍትሃዊ እርምጃዎች በማንኛውም ጊዜና ስፍራ በምትችሉት ሁሉ ከጎናችን እንድትቆሙ እንጠይቃለን፡፡ በማኛውም ጊዜ ለምናስተላልፈው ጥሪ ወንድማዊ ምላሽ እንድትሰጡን በአክብሮት እናሳስባለን፡፡ የአማራ ፋኖ አንድነት በሸዋ አማራ ፩ ኢትዮጵያ!

Source: Link to the Post

Leave a Reply