You are currently viewing የአማራ ህዝብ በሁሉም አቅጣጫ የተቃጣበትን ግድያና መፈናቀል የሚቃወም ማንኛውም አገር ወዳድ ሁሉ ከወገኑ ከአማራ ህዘብ ጋር በመቆም ሊታገለው ይገባል ። አማራ የኢትዮጵያን ጥንታዊ ታሪክ ጠብቆ…

የአማራ ህዝብ በሁሉም አቅጣጫ የተቃጣበትን ግድያና መፈናቀል የሚቃወም ማንኛውም አገር ወዳድ ሁሉ ከወገኑ ከአማራ ህዘብ ጋር በመቆም ሊታገለው ይገባል ። አማራ የኢትዮጵያን ጥንታዊ ታሪክ ጠብቆ…

የአማራ ህዝብ በሁሉም አቅጣጫ የተቃጣበትን ግድያና መፈናቀል የሚቃወም ማንኛውም አገር ወዳድ ሁሉ ከወገኑ ከአማራ ህዘብ ጋር በመቆም ሊታገለው ይገባል ። አማራ የኢትዮጵያን ጥንታዊ ታሪክ ጠብቆና አስከብሮ ፣ በአፍሪካ ብቸኛ የሆነውን ፊደል ቀርጾ ፣ ዳር ድንበሩን ከጠላት ታድጎ እና ለባንዲራው ቀናኢ ሆኖ የዘለቀ ኩሩ ህዝብ ነው ። እነዚህን እሴቶች አስጠብቆ ለትውልድ ከማሳለፍና ኢትዮጵያን እንደ አገር ከማስቀጠል ውጭ ሌላ አጀንዳ የለውም። ታዲያ ይህን ባደረገ ላለፉት 40 አመታት እንደ ጠላት ተቆጥሮ ራሱ ባቀናውና እትብቱ በተቀበረበት ቦታ እንዳይኖር ሰብዓዊ ፍጡር ይፈፅመዋል ተብሎ በማይገመት ጭካኔ እየተጨፈጨፈና ዘሩ ከምድረ ገፅ እንዲጠፋ እየተደረገ ይገኛል ። ህይወታቸውን ያተረፉና የተፈናቀሉ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ወገኖቻችን በአገራቸው ስደተኛ ሆነው በ…መጠለያ ውስጥ በረሀብና በእርዛት ይገኛሉ ። በመሆኑም “እኔም ለወገኔ !” በሚል መሪ ቃል ሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት እና የአማራ ሚዲያ ማዕከል አሚማ ከሸዋ የአማራ ወጣቶች ማህበር ጋር በመተባበር በአይነት ሰብአዊ ድጋፍ ማለትም ፦ – ምግብ ነክ ነገሮች፤ ዱቄት፣ ፓስታ፣ መኮሮኒ፣ ሩዝ፣ የህፃናት አልሚ ምግቦች እና የማይበላሹ የታሸጉ ምግቦች – የአልባሳት ድጋፍ ፤ ብርድ ልብስ፣ ፍራሽ፣ የህፃናትና የአዋቂዎች ልብስ – የንፅህና መጠበቂያዎች፤ ሳሙና፣ ላርጎ፣ የሴቶች የንፅህና መጠበቂያዎችና ጠቃሚ ቁሳቁሶችን በማሰባሰብ ለወገን ለመድረስ ጥሪ አድርገዋል ። አድራሻ ፤ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ካዛንችስ ወረዳ 8 እዮቤድ ህንጻ ማንኛውም አገር ወዳድ የሆነ ሁሉ የፕሮግራሙ ታዳሚ እንዲሆንና እርዳታ እንዲያደርግ አስተባባሪ ኮሚቴው በትህትና ይጠይቃል ! ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ ይበቃል ! @ ሼር በማድረግ ላልሰሙት ያሰሙ !

Source: Link to the Post

Leave a Reply