You are currently viewing “የአማራ ህዝብ የሚታገልላቸው ዋና ዋና ጥያቄዎች”        በዶ/ር ምስጋናው አንዷለም        አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … ሀምሌ 18/2015 ዓ/ም_አዲስ አበባ ኢትዮጵያ የአማራ ህ…

“የአማራ ህዝብ የሚታገልላቸው ዋና ዋና ጥያቄዎች” በዶ/ር ምስጋናው አንዷለም አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … ሀምሌ 18/2015 ዓ/ም_አዲስ አበባ ኢትዮጵያ የአማራ ህ…

“የአማራ ህዝብ የሚታገልላቸው ዋና ዋና ጥያቄዎች” በዶ/ር ምስጋናው አንዷለም አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … ሀምሌ 18/2015 ዓ/ም_አዲስ አበባ ኢትዮጵያ የአማራ ህዝብ የሚታገልላቸው ዋና ዋና ጥያቄዎች:_ 1) ህገ መንግስት:_ የአሁኑ ህገመንግስት ሲረቀቅም ሆነ ሲጽድቅ የአማራን ህዝብ ያገለለ ነበር፡፡ አሁን አማራ የሚሳተፍበት አዲስ ህገ መንግስት ያስፈልጋል፡፡ 2) መንግሥት:_ ሀ) ስልጣን ለህዝብ ማስረከብ፦ አሁን በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ ወንጀለኛ፣ ዘር አጥፊ፤ የኢትዮጵያ ጠላቶች ቀኝ እጅ፣ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ያስደፈረና በጥቅሟ የተደራደረ፣ የኢትዮጵያ አገራዊ ህልውና ዋና የስጋት ምንጭ፣ ዘረኛ እና ምንም አይነት እምነት የማይጣልበት፤ የአማራን እና የመላውን ኢትዮጵያ ህዝብ አደጋ ውስጥ የጣለ በመሆኑ በአስቸኳይ ስልጣን ለኢትዮጵያ ህዝብ ማስረከብ አለበት፡፡ ለ) የሽግግር መንግስት፦ አሁን የአማራም የኢትዮጵያም ቁጥር አንድ የህልውና ፈተና እና የአገሪቱ ቀጣይነት አደጋ የሆነው ብልጽግና በአስቸኳይ ፈርሶ በምትኩ ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ፤ በአሁኑ አገዛዝ ቅንጣት ታክል ተሳትፎ የሌላቸው ተሰባስበው ጊዜያዊ የሽግግር መንግስት እንዲመሰርቱ ማድረግ፤ ሐ) በኢትዮጵያ ህዝብ በአጠቃላይ በአማራ ህዝብ ደግሞ በተለይ የመከራ ዶፍ ያወረዱት የብልጽግና ባለስልጣናት ለፍርድ እንዲቀርቡ፡፡ 3) ማንነትና ወሰን:_ ሀ) የተመለሱ ግዛቶች ጉዳይ፦ የወልቃይት ጠገዴ ጠለምትና ራያ ህዝብ የዘር ጭፍጨፋ ሰለባ ሆኖ መቆየቱ በሁሉም የኢትዮጵያ የፖለቲካ ኃይሎች የእምነት ቃል እንዲሰጥበት፤ የትግራይ ክልል የሚያራምደውን መልሶ የመውረር ህልም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በይፋ እንዲሰርዝ፤ በዘር ጭፍጨፋ የተሳተፉ አካላት ለፍርድ እንዲቀርቡ፤ ለዚህ ህዝብ ከዘር ጭፍጨፋ መትረፉን እውቅና የሚሰጥ የሞራል፣ የስነልቦናና የቁሳቁስ ካሳ እንዲደረግለት፡፡ ለ) ያልተመለሱ ግዛቶች ጉዳይ፦ ከቀድሞው ሸዋ ክፍለ ሀገር ተቆርሰው ወደኦሮሚያ ክልል የገቡ የአማራ አካባቢዎች ባስቸኳይ እንዲመለሱ፤ መተከል ወደነበረበት ጎጃም ክፍለ ሀገር እንዲመለስ፤ ሐ) የአዲስ አበባ ጉዳይ፦ የአዲስ አበባ ህዝብ አብላጫ የአማራ ህዝብ በመሆኑ የህዝብ ቁጥሩን ግምት ውስጥ ያስገባ መብትና ጥቅሙን የሚያስከብር አስተዳደር እንዲመሰረት፤ በአዲስ አበባ የአማራና ደቡብ ኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የተፈጸመ የማፈናቀል፤ የማዋከብ፣ ቤት የማፍረስ እና ንብረት የመዝረፍ ወንጀል የቁሳቁስ፣ የሞራልና የስነልቦና ካሳ እንዲጠየቅበት፤ ቤታቸው የፈረሰባቸውና የተፈናቀሉ ባስቸኳይ ከበቂ ካሳ ጋር ወደይዞታቸው እንዲመለሱ፤ መ) አዲስ አበባን የሬሳ ሳጥን ውስጥ ያስገባ የሸገር ከተማ የሚባል የአፓርታይድ ድንበር ባስቸኳይ እንዲሰረዝ፣ በሸገር ከተማ ምክንያት የተፈናቀሉ ኢትዮጵያዊያን ባስቸኳይ ከበቂ ካሳ ጋር ወደይዞታቸው እንዲመለሱ፤ የፈረሰው ቤታቸው እንዲገነባላቸው፤ በአገዛዙ ይፋዊ ይቅርታ እንዲጠየቁ፤ ሠ) በኦሮሚያ ክልል የተፈጸመው አማራን ዘሩን የማጥፋት እና የማጽዳት ወንጀል ተዋንያን ለፍርድ እንዲቀርቡ፤ የግፍ ሰለባ ቤተሰቦች ካሳ እንዲከፈላቸው፤ የተፈናቀሉ ከበቂ መልሶ ማቋቋሚያ ጋር ወደቀያቸው እንዲመለሱ፤ ወደፊት ተመሳሳይ ወንጀል እንዳይፈጸምባቸው ማስተማመኛ ዘዴዎች እንዲቀየሱ፤ በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው የመማር እና ባህላቸውን የማበልጸግ መብታቸው እንዲከበር፤ 4) በአማራ ክልል ብልጽግና ሙሉ በሙሉ ፈርሶ በምትኩ ህዝባዊ አስተዳደር በአስቸኳይ እንዲቋቋም፤ በአማራ ህዝብ ላይ በደል የፈጸሙ የፖለቲካና የደህነንት መዋቅሮች አባላት ለፍርድ እንዲቀርቡ፤ የክልሉ ገዥ ፓርቲ ለአማራ ህዝብ መወገን ሲገባው፤ ከጠላት ወግኖ ህዝቡን ሲወጋ በመኖሩ በአደባባይ ህዝቡን ይቅርታ እንዲጠይቅ፡፡ 5) ሀይማኖት:_ መንግስትና ሀይማኖት የተለያዩ ናቸው የሚለውን መርህ በመጣስ አገዛዙ በሀይማኖቶች ውስጥ ገብቶ የፈተፈተው ሁሉ ወደነበረበት እንዲመለስ፤ ይሄንን ያደረጉ አካላትም ህዝብን ይቅርታ እንዲጠይቁ፤ በህግ የሚጠየቁም እንዲጠየቁ፡፡ 6) ወያኔ እና ኦነግ፤ ወያኔያዊ እና ኦነጋዊ አስተሳሰቦች:_ ወያኔ እና ኦነግ በአማራ ህዝብ ላይ ላደረሱት በደል ከታሪክ እንዲፋቁ፤ እነሱን የሚያስታውስ ምንም አይነት ምልክት በህግ ክልክል እንዲሆን፤ የነሱን አስተሳሰብ ማራመድ በህግ የሚያስቀጣ እንዲሆን፤ አባላቱ በህዝቡ ላይ ላደረሱት በደል እየታደኑ ለፍርድ እንዲቀርቡ እና ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ፡፡ እነዚህ ድርጅቶች ለፈጸሙት ታሪክ ይቅር የማይለው የዘረኝነት ወንጀል የአማራን ህዝብ ይፋዊ ይቅርታ እንዲጠይቁ፡፡ 7) የጥላቻ ንግግር:_ በወያኔና ኦነግ ፊታውራሪነት በአማራ ህዝብ ላይ የተካሄደ ግማሽ ክፍለ ዘመን የወሰደ የማጥላላት ዘመቻ ይቅርታ እንዲጠየቅበት፤ በሀሰት ለጠፋው ስም ማካካሻ ይሆን ዘንድ ማስተካከያ እንዲደረግበት፤ መልካምን ስምን ማደስና ማስመለስ በሚል ሰፊ የተዛባ ትርክት ማስተካከያ ስራ እንዲሰራ፤ 8)) የዘር ማጥፋት:_ የአማራ ህዝብ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሰለባ መሆኑ አገራቀፍ እና አለማቀፍ እውቅና እንዲሰጠው ማድረግ፤ የዘር ማጥፋቱ ተዋንያን ተለቅመው ለፍርድ እንዲቀርቡ፤ የዘር ማጥፋት ሰለባ ቤተሰቦች ካሳ እንዲከፈላቸው፤ መላው የአማራ ህዝብ ይፋዊ ይቅርታ እንዲጠየቅ፤ የዘር ማጥፋት ሰለባዎችን ማንነት የሚገልጽ መረጃ ተሰባስቦ የሚቀመጥበት ብሄራዊ ማለትም አገራቀፋዊና አለማቀፋዊ እውቅና ያለው “የአማራ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሰለባዎች ሙዚየም” እንዲቋቋም፤ 9) የጦር ወንጀል:_ ባለፉት ሁለት አመታት፤ ማለትም በአንደኛውና በሁለተኛው ዙር የወያኔ ወረራ ወያኔ በአማራ ህዝብ ላይ የጦር ወንጀል ፈጽሟል፡፡ ይሄንን ያደረጉ በሙሉ በአገራቀፍ እና በአለማቀፍ የጦር ወንጀለኝነት ህግ እንዲዳኙ፤ አሁን በብልጽግና አመራር ሰጭነት በደብረ ኤልያስና ሌሎች ስፍራዎች የጦር ወንጀሎች ተፈጽመዋል፤ የዚህ ተዋንያን በአገራቀፍ እና በአለማቀፍ የጦር ወንጀለኝነት ህግ እንዲዳኙ ማድረግ፤ ድል ለአማራ ህዝብ! ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ! 1) ህገ መንግስት:_ የአሁኑ ህገመንግስት ሲረቀቅም ሆነ ሲጽድቅ የአማራን ህዝብ ያገለለ ነበር፡፡ አሁን አማራ የሚሳተፍበት አዲስ ህገ መንግስት ያስፈልጋል፡፡ 2) መንግሥት:_ ሀ) ስልጣን ለህዝብ ማስረከብ፦ አሁን በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ ወንጀለኛ፣ ዘር አጥፊ፤ የኢትዮጵያ ጠላቶች ቀኝ እጅ፣ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ያስደፈረና በጥቅሟ የተደራደረ፣ የኢትዮጵያ አገራዊ ህልውና ዋና የስጋት ምንጭ፣ ዘረኛ እና ምንም አይነት እምነት የማይጣልበት፤ የአማራን እና የመላውን ኢትዮጵያ ህዝብ አደጋ ውስጥ የጣለ በመሆኑ በአስቸኳይ ስልጣን ለኢትዮጵያ ህዝብ ማስረከብ አለበት፡፡ ለ) የሽግግር መንግስት፦ አሁን የአማራም የኢትዮጵያም ቁጥር አንድ የህልውና ፈተና እና የአገሪቱ ቀጣይነት አደጋ የሆነው ብልጽግና በአስቸኳይ ፈርሶ በምትኩ ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ፤ በአሁኑ አገዛዝ ቅንጣት ታክል ተሳትፎ የሌላቸው ተሰባስበው ጊዜያዊ የሽግግር መንግስት እንዲመሰርቱ ማድረግ፤ ሐ) በኢትዮጵያ ህዝብ በአጠቃላይ በአማራ ህዝብ ደግሞ በተለይ የመከራ ዶፍ ያወረዱት የብልጽግና ባለስልጣናት ለፍርድ እንዲቀርቡ፡፡ 3) ማንነትና ወሰን:_ ሀ) የተመለሱ ግዛቶች ጉዳይ፦ የወልቃይት ጠገዴ ጠለምትና ራያ ህዝብ የዘር ጭፍጨፋ ሰለባ ሆኖ መቆየቱ በሁሉም የኢትዮጵያ የፖለቲካ ኃይሎች የእምነት ቃል እንዲሰጥበት፤ የትግራይ ክልል የሚያራምደውን መልሶ የመውረር ህልም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በይፋ እንዲሰርዝ፤ በዘር ጭፍጨፋ የተሳተፉ አካላት ለፍርድ እንዲቀርቡ፤ ለዚህ ህዝብ ከዘር ጭፍጨፋ መትረፉን እውቅና የሚሰጥ የሞራል፣ የስነልቦናና የቁሳቁስ ካሳ እንዲደረግለት፡፡ ለ) ያልተመለሱ ግዛቶች ጉዳይ፦ ከቀድሞው ሸዋ ክፍለ ሀገር ተቆርሰው ወደኦሮሚያ ክልል የገቡ የአማራ አካባቢዎች ባስቸኳይ እንዲመለሱ፤ መተከል ወደነበረበት ጎጃም ክፍለ ሀገር እንዲመለስ፤ ሐ) የአዲስ አበባ ጉዳይ፦ የአዲስ አበባ ህዝብ አብላጫ የአማራ ህዝብ በመሆኑ የህዝብ ቁጥሩን ግምት ውስጥ ያስገባ መብትና ጥቅሙን የሚያስከብር አስተዳደር እንዲመሰረት፤ በአዲስ አበባ የአማራና ደቡብ ኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የተፈጸመ የማፈናቀል፤ የማዋከብ፣ ቤት የማፍረስ እና ንብረት የመዝረፍ ወንጀል የቁሳቁስ፣ የሞራልና የስነልቦና ካሳ እንዲጠየቅበት፤ ቤታቸው የፈረሰባቸውና የተፈናቀሉ ባስቸኳይ ከበቂ ካሳ ጋር ወደይዞታቸው እንዲመለሱ፤ መ) አዲስ አበባን የሬሳ ሳጥን ውስጥ ያስገባ የሸገር ከተማ የሚባል የአፓርታይድ ድንበር ባስቸኳይ እንዲሰረዝ፣ በሸገር ከተማ ምክንያት የተፈናቀሉ ኢትዮጵያዊያን ባስቸኳይ ከበቂ ካሳ ጋር ወደይዞታቸው እንዲመለሱ፤ የፈረሰው ቤታቸው እንዲገነባላቸው፤ በአገዛዙ ይፋዊ ይቅርታ እንዲጠየቁ፤ ሠ) በኦሮሚያ ክልል የተፈጸመው አማራን ዘሩን የማጥፋት እና የማጽዳት ወንጀል ተዋንያን ለፍርድ እንዲቀርቡ፤ የግፍ ሰለባ ቤተሰቦች ካሳ እንዲከፈላቸው፤ የተፈናቀሉ ከበቂ መልሶ ማቋቋሚያ ጋር ወደቀያቸው እንዲመለሱ፤ ወደፊት ተመሳሳይ ወንጀል እንዳይፈጸምባቸው ማስተማመኛ ዘዴዎች እንዲቀየሱ፤ በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው የመማር እና ባህላቸውን የማበልጸግ መብታቸው እንዲከበር፤ 4) በአማራ ክልል ብልጽግና ሙሉ በሙሉ ፈርሶ በምትኩ ህዝባዊ አስተዳደር በአስቸኳይ እንዲቋቋም፤ በአማራ ህዝብ ላይ በደል የፈጸሙ የፖለቲካና የደህነንት መዋቅሮች አባላት ለፍርድ እንዲቀርቡ፤ የክልሉ ገዥ ፓርቲ ለአማራ ህዝብ መወገን ሲገባው፤ ከጠላት ወግኖ ህዝቡን ሲወጋ በመኖሩ በአደባባይ ህዝቡን ይቅርታ እንዲጠይቅ፡፡ 5) ሀይማኖት:_ መንግስትና ሀይማኖት የተለያዩ ናቸው የሚለውን መርህ በመጣስ አገዛዙ በሀይማኖቶች ውስጥ ገብቶ የፈተፈተው ሁሉ ወደነበረበት እንዲመለስ፤ ይሄንን ያደረጉ አካላትም ህዝብን ይቅርታ እንዲጠይቁ፤ በህግ የሚጠየቁም እንዲጠየቁ፡፡ 6) ወያኔ እና ኦነግ፤ ወያኔያዊ እና ኦነጋዊ አስተሳሰቦች:_ ወያኔ እና ኦነግ በአማራ ህዝብ ላይ ላደረሱት በደል ከታሪክ እንዲፋቁ፤ እነሱን የሚያስታውስ ምንም አይነት ምልክት በህግ ክልክል እንዲሆን፤ የነሱን አስተሳሰብ ማራመድ በህግ የሚያስቀጣ እንዲሆን፤ አባላቱ በህዝቡ ላይ ላደረሱት በደል እየታደኑ ለፍርድ እንዲቀርቡ እና ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ፡፡ እነዚህ ድርጅቶች ለፈጸሙት ታሪክ ይቅር የማይለው የዘረኝነት ወንጀል የአማራን ህዝብ ይፋዊ ይቅርታ እንዲጠይቁ፡፡ 7) የጥላቻ ንግግር:_ በወያኔና ኦነግ ፊታውራሪነት በአማራ ህዝብ ላይ የተካሄደ ግማሽ ክፍለ ዘመን የወሰደ የማጥላላት ዘመቻ ይቅርታ እንዲጠየቅበት፤ በሀሰት ለጠፋው ስም ማካካሻ ይሆን ዘንድ ማስተካከያ እንዲደረግበት፤ መልካምን ስምን ማደስና ማስመለስ በሚል ሰፊ የተዛባ ትርክት ማስተካከያ ስራ እንዲሰራ፤ 8)) የዘር ማጥፋት:_ የአማራ ህዝብ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሰለባ መሆኑ አገራቀፍ እና አለማቀፍ እውቅና እንዲሰጠው ማድረግ፤ የዘር ማጥፋቱ ተዋንያን ተለቅመው ለፍርድ እንዲቀርቡ፤ የዘር ማጥፋት ሰለባ ቤተሰቦች ካሳ እንዲከፈላቸው፤ መላው የአማራ ህዝብ ይፋዊ ይቅርታ እንዲጠየቅ፤ የዘር ማጥፋት ሰለባዎችን ማንነት የሚገልጽ መረጃ ተሰባስቦ የሚቀመጥበት ብሄራዊ ማለትም አገራቀፋዊና አለማቀፋዊ እውቅና ያለው “የአማራ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሰለባዎች ሙዚየም” እንዲቋቋም፤ 9) የጦር ወንጀል:_ ባለፉት ሁለት አመታት፤ ማለትም በአንደኛውና በሁለተኛው ዙር የወያኔ ወረራ ወያኔ በአማራ ህዝብ ላይ የጦር ወንጀል ፈጽሟል፡፡ ይሄንን ያደረጉ በሙሉ በአገራቀፍ እና በአለማቀፍ የጦር ወንጀለኝነት ህግ እንዲዳኙ፤ አሁን በብልጽግና አመራር ሰጭነት በደብረ ኤልያስና ሌሎች ስፍራዎች የጦር ወንጀሎች ተፈጽመዋል፤ የዚህ ተዋንያን በአገራቀፍ እና በአለማቀፍ የጦር ወንጀለኝነት ህግ እንዲዳኙ ማድረግ፤ ድል ለአማራ ህዝብ! ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

Source: Link to the Post

Leave a Reply