“የአማራ ህዝብ የተቃጣበትን አደጋ በተባበረ ክንድ ይቀለብሳል” አሻራ ሚዲያ ሰሜን አሜሪካ ከአለም አቀፍ የአማራ ፋኖ ደጋፊዎች እና አስተባባሪዎች የተሰጠ መግለጫ!! እንደሚታወ…

“የአማራ ህዝብ የተቃጣበትን አደጋ በተባበረ ክንድ ይቀለብሳል” አሻራ ሚዲያ ሰሜን አሜሪካ ከአለም አቀፍ የአማራ ፋኖ ደጋፊዎች እና አስተባባሪዎች የተሰጠ መግለጫ!! እንደሚታወቀው ላለፉት 31 ዓመታት የአማራ ህዝብ ማህበራዊ ረፍት አጥቶ ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ በመጣ የመከራ ሂወት ኑሮውን እየገፋ ይገኛል።ለዚህም እንደ ዋነኛ ምክንያት ሆኖ የሚጠቀሰዉ ት*ህ*ነ*ግ ሲሆን ወደትግል ሲገባ ጀምሮ የአማራ ህዝብ ታሪካዊ ጠላቴ ነው የሚል ማታገያ ማንፌስቶ ቀርጾ ወደ ትግል የገባው ሁዋላ ላይ ህወሃት መራሹን ስርዓት ኢህአዴግን በመዉለድ በአማራ ህዝብ ትከሻ ላይ ተረማምዶ መንበረ ስልጣኑን የተመቆጣጠርወና ስልጣን ላይ በነበረባቸው 27 ዓመታት ውስጥ አንድን ህዝብ ነጥሎ የሚጎዳ ህገ መንግስት በመቅረጽ ጠላቴ ብሎ የሰየመውን የአማራ ህዝብ መዋቅራዊ በሆነ መንገድ ሲበድል እና የዘር ጭፍጨፋ ሲያካሂድበት ነበር። ጭቁኑ የአማራ ህዝብም ይህን ስርዓታዊ ጭቆና በመታገል ላንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ታግሎ ቢጥለውም የአማራ ህዝብ ያገኘውን ወርቃማ እድል በራሳቸው በማይተማመኑ እና ከመምራት ይልቅ መመራትን ከነጻነት ይልቅ ባርነትን በመረጡ አድር ባይ የብአዴን አመራሮች አማካይነት እድሉን እንዲያጣ እና ሌላው ባለተረኛ ጨቋኝ ስርዓት እንዲተካ ሆኗል። እናም ላለፉት አራት አመታት ጭራሽ በዚህ በሰለጠነ እና አለማችን ከሰው መብት አልፎ ለእንሰሳት መብት መቆርቆር በጀመረበት ዘመን የሰው ልጅ ላይ ይፈጸማል ተብሎ የማይገመት ግፍ አማራ ህዝብ ላይ መንግስት መር በሆነ ስርዓት እየተፈጸመ ይገኛል። በዚህ አገዛዝ እንዝህላልነት እና ቸልተኝነት ምክንያት በተፈጠረ ጦርነት የሃገሪቷ ሉዓላዊነት ጥያቄ ውስጥ ሲገባ አገዛዙ የህልውና ዘመቻ ብሎ ሰይሞ አግዙኝ ባለው መሰረት የአማራ ህዝብ ከአገዛዙ ጋር በመሆን የማይተካ ህይወቱን ሰውቶ የተቃጣውን አደጋ መመከት ችሏል። ይሁን እና በዚህ ዘመቻ ወቅት የአማራ ህዝብ ህይወት ቤት ንብረት መሰረተ ልማቶች ማለትም ትምህርት ቤቶች ሆስፒታሎች የጠፉ ቢሆንም እነዚህን መሰረተ ልማቶች ከማሟላት እና ሰበዓዊ ድጋፎች ከማድረስ ይልቅ በጭንቅ ሰዓት ከጎኑ የቆመውን ህዝብ ህግ በማስከበር ሰበብ እያሸበረው ይገኛል። ከምንም በላይ ደግሞ ፋኖነት የአማራ ህዝብ የነጻነት፣የሃገር ወዳድነት፣ ከራስ በላይ ለሃገር መሰዋትን ታጋይነትን የጋራ ወይም የወል ስም የሆነውን ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣውን ማንነታችንን ለማጥፋት ሃገሪቷን ሲያተራምሱ፣ህዝባችንን ሲያፈናቅሉ ፣ ባንክ ሲዘርፉ፣ በጅምላ ሲገሉ ከነበሩ አሸባሪዎች ጋር እኩል አብሮ በመፈረጅ ህግ በማስከበር ሰበብ ፋኖዎቻችንን እያሳደደ ይገኛል። ማሳደድ ብቻ ሳይሆን አስተዳድረዋለሁ በሚለው ህዝብ ላይ የማይደረግ ድርጊት በከባድ መሳርያ የፋኖዎችን ድብደባ አለፍ ሲልም ሰው አልባ የጦር አውሮፕላን/ድሮን እጠቀማለሁ ብሎ ማስፈራራት ጀምሯል።ደግሞ የሚገርመው ከባለፈው ስርዓት ውድቀት እንኳን መማር ያልቻለው አገዛዝ ይህን እኩይ የሆነ ተግባሩን የአማራ ህዝብ ድጋፍ እንዳለው አርጎ በመግለጫ መልኩ በተለያዩ ሚዲያዎች እያስተጋባ ይገኛል። ስለሆነም ህብረታችን የሚከተሉትን ባለ 6 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥቷል። 1) ማንኛውም የአማራ ህዝብ ይህንን አፋኝ የሆነ ስርዓት ላንዴ እና ለመጨረሻ ገርስሶ ለመጣል ራሱን እንዲያዘጋጅ ጥሪ እናስተላልፋለን። 2) ከአማራ ህዝብ አብራክ ወታችሁ በሁለቱ ጸረ አማራ አገዛዝ ጋር በመሆን የአማራውን ህዝብ ስትበድሉ የኖራችሁ ሹማምንቶች ጊዜው የአማራውን ህዝብ የምትክሱበት ነውና ከማይቋረጠው የአማራ ህዝብ አቢዮት ጎን እንድትሰለፉ ጥሪ እናስተላልፋለን። 3) ማንኛውም የአማራ ወጣት አዛውንት ልጅ ሴት ወንድ ሳይል ከፋኖ ጎን በመቆም ራሱን ለመራራ ትግል እንዲያዘጋጅ ጥሪ እናስተላልፋለን። 4) ከሃገር ውጪ ያላችሁ ደግሞ ወገኔ የምትሉት ህዝብ ይጠፋ ዘንድ ባራት አቅጣጫ ተከቦ ከአለም አቀፍ እስከ ሃገር አቀፍ ጠላቶች ተነስተውበታል እና ይህን ከበባ ለመስበር በሚደረግ የፋይናንስ፣የፕሮፓጋንዳ፣እየተደረገ ያለውን የዘር ፍጅት በማጋለጥ ሂደት ውስጥ ደከመኝ ሰለቸኝ ወይም አቅም አነሰኝ ሳትሉ ሌት ከቀን እንድታግዙ ስንል ጥሪ እናስተላልፋለን። 5) ከፈጣሪ በታች የአማራን ህዝብ ሊያድነው የሚችለው ወቅቱን ያማከለ ጠንካራ ሚሊተሪያዊ እና ዲፕሎማሳዊ ትግል መሆኑ ታውቆ ሁሉም ለዚህ ትግል ራሱን ዝግጁ እንዲያረግ ስንል ጥሪ እናስተላልፋለን 6) በተለያየ የመንግስት የሚሊተሪ መዋቅር ስር ያላችሁ አማራዎች አማራ ህዝብ ላይ እየተሰራበት ያለውን መዋቅራዊ ሸፍጥ በመረዳት ከወገናችሁ ጎን እንድትሰለፉ ስንል ጥሪ እናስተላልፋለን። “የአማራ ህዝብ የተቃጣበትን አደጋ በተባበረ ክንድ ይቀለብሳል” ሰኔ 4/2014 ዓ.ም አንድ አማራ ያሬድ አላዩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply