
“የአማራ ህዝብ የተጋረጠበትን የህልውና አደጋ ይቀለብስ ዘንድ ፋኖነት የሀገራችንን ነባራዊ ሁኔታ የዋጀ ብቸኛው የትግል መስመራችን ነው።” ሲሉ በአማራ ወጣቶች የራያ ጢነኛ ሲቪክ ማህበር ያዘጋጀው ህዝባዊ የምክክር መድረክ ተሳታፊዎች አቋማቸውን አስታወቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 4 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በአማራ ወጣቶች ማህበር የራያ ጢነኛ ሲቪክ ማህበር ባዘጋጀው ህዝባዊ የውይይት መድረክ:_ የመልካም አስተዳደር ችግሮች እና መፍትሔዎች፣ በህገ-ወጥ የመሬት ወረራ ጉዳዮች፣ በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳይ፣ በራያ እና አካባቢው ስላለው የፀጥታ ጉዳይ ምክክር መደረጉ ተገልጧል። በህዝባዊ የውይይት መድረኩ መጨረሻም የሚከተለውን የአቋም መግለጫ በማውጣት ስብሰባውን አጠናቋል። 1) የተነሱትን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን የሚመለከተው የመንግስት አካላት ትኩረት በመስጠት በአጭር ጊዜ መፍትሄ እንዲሰጥ እንጠይቃለን። 2) በከተማችን ላይ በሚደረገው ህገወጥ ድርጊቶች የሚሳተፉ ማናቸኛውም አካላት ከድርጊቶቻቸው እንዲቆጠቡ እና ህገወጥ ድርጊት የሚፈፅሙትን የምንታገል እና ለህግ አካላት አሳልፈን የምንሰጥ መሆኑን እናሳውቃለን። 3) በአማራ ክልል ብሎም በዞን እና በወረዳችን ላይ የኑሮ ውድነት እንዲኖር የሚያደርጉ ስግብግብ ነጋዴዎች ከዚህ ስራቸው እንዲቆጠቡ እና መንግስትም የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት ከፍተኛ የሆነ ስራ እንዲፈጠር ስንል እናሳስባለን። 4) የአማራ ህዝብ የተጋረጠበትን የህልውና አደጋ ይቀለብስ ዘንድ ፋኖነት የሀገራችንን ነባራዊ ሁኔታ የዋጀ ብቸኛው የትግል መስመራችን ነው። ስለሆነም ማንኛውም ግለሰብ ይሁን ቡድን በፋኖ ስም ወንጀል ሲፈፅም ቢገኝ ፋኖነትን እና ፋኖን ለጠላት አጋልጦ ቢሰጥ የማያዳግም እርምጃ የምንወስድ መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን የሚል አቋምም ተወስዷል። 5) በማንኛውም ቦታ የሚገኝ የአማራ ህዝብ ወቅቱ የፈጠረብንን የህልውና አደጋ ከግምት ውስጥ በማስገባት ከመቸውም ጊዜ በላይ አንድነታችንን እና አደረጃጀታችንን አጠናክረን የምንታገልበት ጊዜ መሆኑን እናሳስባለን። 6) በማንኛውም ቦታ ያላችሁ የአማራ ወጣቶች ማህበር አደረጃጀት ከመቸውም ጊዜ በላይ ማህበራችሁን በማንቀሳቀስ ለአማራ ህዝብ ሁለንተናዊ ጥቅም መከበር ከፍተኛ ትግል እንድታደርጉ ስንል እናሳስባለን። 7) ከራያ እስከ ወልቃይት፣ከመተከል እስከ ደራ ሸዋ ያለው አማራ እንዲሁም ከአማራ ክልል ውጭ በአማራነታቸው የሚገደሉ እና የሚፈናቀሉ ቤታቸው የሚፈርስባቸውን ለማስቆም የክልሉ መንግስት በአፅኖት ይዞ እንዲሰራበት እናሳስባለን የሚሉት ይገኙበታ።
Source: Link to the Post