
“የአማራ ህዝብ የኦነግን እና የህወሃትን ስሁት ብያኔ ቀዳዶ ለመጣል ቆርጦ ተነስቷል።” – ሻ/ቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ ግንቦት 15 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ላለፉት 50 አመታት በኦነግና በህወሃት አክራሪ ፖለቲከኞች የተሳሳተ ብያኔ ተወስኖ ኖሯል። አሁን የአማራ ህዝብ ይሄን ስሁት ብያኔ ቀዳዶ ለመጣል ቆርጦ ተነስቷል። ስሙ ብቻ አታጋይ የሆነው እስክንድር ነጋ እና ጓዶቹ የአማራ ህዝባዊ ግንባር ለአማራ መድህን ሆኖ መጥቷል። እኔ ጡረታ መውጫዬ ላይ ደርሻለሁ። ነገር ግን በእስተርጅና የአማራን ትግል ለማገዝ ስጠየቅ እምቢ ማለት አልቻልኩም። ነገር ግን በመሪነት አይደለም የተመረጥኩት። በውጭ ሀገር ሆኜ ድጋፍ እንዳደርግ ነው የተፈለገው፣ ደስተኛ ነኝ። የአማራ ትግል የምዕራባውያን ድጋፍ የለውም የሚባለው ስህተት ነው። የአማራ ትግል ፍሬ ካፈራ፣ ሀይል መፍጠር ከቻለ ምዕራባውያኑ ወደው ሳይሆን በግዴታቸው የአማራን ትግል ይደግፉታል። ደግሞም የምዕራባውያንን ጥቅም እና የአማራን ጥቅም አስተሳስረን ለመስራት አቅሙም፣ ፍላጎቱም አለን። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post