You are currently viewing “የአማራ ህዝብ የዘር ጭፍጨፋ ክስተታዊ ሳይሆን መዋቅራዊና ስርዓታዊ ስለሆነ የሚቆመውም በመዋቅራዊና  ስርዓታዊ ለውጥ ነው‼️”።  ከአማራ ወጣቶች ማህበር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ የተላለፈ መል…

“የአማራ ህዝብ የዘር ጭፍጨፋ ክስተታዊ ሳይሆን መዋቅራዊና ስርዓታዊ ስለሆነ የሚቆመውም በመዋቅራዊና ስርዓታዊ ለውጥ ነው‼️”። ከአማራ ወጣቶች ማህበር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ የተላለፈ መል…

“የአማራ ህዝብ የዘር ጭፍጨፋ ክስተታዊ ሳይሆን መዋቅራዊና ስርዓታዊ ስለሆነ የሚቆመውም በመዋቅራዊና ስርዓታዊ ለውጥ ነው‼️”። ከአማራ ወጣቶች ማህበር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ የተላለፈ መልዕክት ። ህዳር 27 /2015 ዓ.ም አማራ-ጠሉ አስተሳሰብ የሃገራችንን መንግስታዊ ስልጣን ከተቆናጠጠበት ከ1983 ዓም ጀምሮ እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ … በአማራ ህዝብ ላይ እወረደ ያለው ሰቆቃ ቃላት ሊወክሉት፣ የሰው ህሊና ሊሸከመው የሚችል አይደለም፡፡ ይህ አማራ- ጠል ስርዓት ስልጣን ላይ የመውጣቱ ዋነኛ አላማ አማራውን ማሳደድ፣መጨፍጨፍና አንገት ማስደፋት ነው፡፡በመሆኑም የስልጣን ጊዜውን ስኬታማነት የሚለካው አማራውን እንዳይናገር አፍኖ፣እንዳይታገል እግር-ተወርች አስሮ በገደለበት፣ባፈናቀለበት፣በዘረፈበትና ባሳደደበት የጭካኔ ልክ ነው፡፡ ከ1983 ዓም ጀምሮ ስልጣን ላይ የወጣው አማራ-ጠሉ ሃይል በትህነግ በሚመራበትም ሆነ አሁን በኦነግ/ኦሮሞ ብልፅግና በሚመራበት ዘመን የአማራ ህዝብ በማንነነቱ የተቃጣበት ማንነት ተኮር እልቂት እየተባባሰ እንጅ እየቀነሰ አልሄደም፡፡ የአማራ ህዝብ በእነዚህ ስርዓቶች የገጠመው የዘር ዕልቂት በሁለት የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ወይም ጎሳዎች በውሃ ወይም በግጦሽ ሳር አይነት የሚፈጠር ድንገተኛ ፣አልፎ አልፎ የሚፈጠር ክስተት ሳይሆን ህገ- መንግስታዊ መሰረት ያለው፣ ታስቦበት የሚፈፀም፣ቀጣይነት ያለውና መዋቅራዊ የዘር ጭፍጨፋ ነው። የአማራን ህዝብ የዘር ጭፍጨፋ ሀገሪቱ የምትመራበት ህገ-መንግስት እውቅና የሚሰጠው ስለሆነ የአማራ እልቂት ህገ- መንግስታዊ እውቅና ያለው መሆኑን በመረዳት አማራ በህይወት የመኖር ተፈጥሯዊ መብቱን ለማስከበር እልቂቱን ህጋዊ እውቅና በሚሰጠው ህገ-መንግስት ሀገሪቱን ከሚገዛው መንግስት የሚጠብቀው በጎ ነገር የለም፡፡ ማንኛውም ሀገር የሚመራው በህገ መንግስት ነው።ሃገራችንን የሚመራው ህገ መንግስት ደግሞ አማራን ለማጥፋት በተነሱ አማራጠል ሃይሎች ተፅፎ በእነሱው እየተተገበረ ያለ የአማራው የሞት ደብዳቤ ነው። ስለሆነም ህገ-መንግስቱ የበለጠ በተተገበረ ልክ የአማራ እልቂትና የዘርጭፍጨፋ በተጠናከረ መልኩ ይፋፋማል። ይህን የተረዳና መሞት መጨፍጨፍ የማይሻ፣ውርደት የበቃው አማራ ሁሉ መንግስት በህገ መንግስቱ በኩል ጨፍጭፎና አስጨፍጭፎ ሳይጨርሰ/ሳያስጨርሰው ራሱን ለተፈጥሯዊው ራስን የመከላከልና ህልውናን የማስጠበቅ የማይቀረው አርነት ማዘጋጀት ይኖርበታል። ሌሎች ጉዳዮች እንዳሉ ሆነው ገዥዎች አማራው ወደ ፊት በኦሮሚያ ክልል የፖለቲካ ውክልና ይጠይቀናል በሚል ኋላቀር እሳቤ ኦሮሞ ብቻ የሚኖርበት የኦሮሞ ክልል ለመፍጠር ያላቸውን ምኞት እውን ለማድረግ ሌት ተቀን እየሰሩ ነው፡፡ ህልማቸው እውን እንዲሆን በኦሮሚያ ክልል የሚኖር አማራን ሁሉ የመፍጀት ፋታ የሌለው፣የተናበበ፣በመንግስታዊ በጀትና ታጣቂ በሚታገዝ የፍጅት አዋጅ አውጀው ህዝባችንን እየጨረሱ ነው፡፡ በመሆኑም አማራው ተነስቶ ታግሎ ሰብዓዊ ክብሩን ማስከበር ካልቻለ አሁን በወለጋ ለይ እየተደረገ ያለው እልቂት በመላው ኦሮሚያን ክልል ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና መላው የኦሮሚያ ክልል ማንም ጠያቂ በሌለው ሁኔታ የአማራ ህዝብ መታረጃ ቄራ እንደሚሆን የታወቀ ነው ። ሃቁ ይህ ሆኖ ሳለ አማራው እየሞተ ዝም በማለቱ “ተበዳይ ዝም ሲባል ተከሳሽ ይሆናል” እንደሚባለው ያለ የርምቢጥ እየተከሰሰ ያለበት ነገርም ደርሶበታል ፡፡ ኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሚያስታጥቀው የኦሮሞ ልዩ ሃይል መሪነት በተለያየ ስም የሚጠራ የኦሮሞ ታጣቂ ሁሉ ተመካክሮና ተናቦ ህዝባችንን በአማራ ማንነቱ ለይቶ የሰው ህሊና ሊያስበውም ሊሸከመውም የማይችለውን እልቂት እያወረደበት መሆኑን የውጭ ሃገር ሚዲያዎች ሁሉ እየዘገቡ ባለበት በአሁኑ ወቅት የሞት ፅዋ እየተጎነጨ ያለው አማራ ራሱ በአራጆቹ በጨፍጫፊነት እየተከሰሰ ይገኛል፡፡ ይህን ውርደት መሸከም የሚችል የአማራ ትከሻ የለም! ትዕግስትም ማስተዋልም ወሰን አለውና አማራ ክብሩን ለማስጠበቅ የመነሻው ሰዓት አሁን ነው ! ሞትን መላመድ፣ ውርደትን መሸከም፣እልቂትን እንደ ፀጋ ልብስ መጎናፀፍ ይብቃን?እንደ ህዝብ ከገጸ-ምድር መጥፋት አደጋ የተጋረጠበት ህዝብ ቤቱ አይቀመጥም፤ ከዚህ በላይ የምንወርድበት የሃፍረትና የውርደት አዘቅት የለም! በአሁኑ ወቅት በኦሮሞ ክልል በአማራ ህዝብ ላይ እየተካሄደ ያለው ማንነት ተኮር ጭፍጨፋ አማራ እንደ ህዝብ የመጥፋትና ያለመጥፋት የሽግግር ወቅት ላይ መሆኑን ነው። ስለሆነም የአማራ ልሂቅ፣ የአማራ ልዩ ልዩ አደረጃጀቶች፣ ተጽኖ ፈጣሪ ግለሰቦች፣ፖለቲከኞች፥አክቲቪስቶችና የሚድያ ባለሙያዎች እንደ አንድ ልብ መካሪ፣ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ በመሆን እንደ ህዝብ የመጣብንን የከፋ የውርደት ዘመን ለመቀልበስ ከወትሮው በተለየ መንገድ ወገባችንን ጠበቅ አድርገን የምንታገልበት የታሪክ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን፡፡ስለሆነም የአማራ ህዝብ የዘር ጭፍጨፋ ይቆም ዘንድ ከፍተኛ የሆነ ህዝባዊ ትግልና ንቅናቄ በአስቸኳይ መፍጠር ይኖርብናል፤ለዚህም አማራ የተባለ ሁሉ ነቅቶ ይጠብቅ። በተባበረ ክንዳችን፣ ለህልውናችን‼️ የአማራ ወጣቶች ማህበር ህዳር 27 /2015 ዓ.ም ዘላለማዊ ዕረፍት አማራ በመሆናቸው ለተጨፈጨፉት ለወለጋ አማራ ወገኖቻችን‼

Source: Link to the Post

Leave a Reply