#የአማራ ልዩ ሀይል ተከዜ ብርጌድ ደመወዝና ሎጂስቲክስ መቋረጡ ተገለፀ!! ባህርዳር:- መጋቢት 06/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ተወርዋሪው የአማራ ልዩ ኃልል ተከዜ ብ…

#የአማራ ልዩ ሀይል ተከዜ ብርጌድ ደመወዝና ሎጂስቲክስ መቋረጡ ተገለፀ!! ባህርዳር:- መጋቢት 06/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ተወርዋሪው የአማራ ልዩ ኃልል ተከዜ ብርጌድ 3 ወር ሙሉ ደሞዝ መቋረጡንና እና ሎጅስቲክ አለመቅረቡ ተገለፀ። በአማራ ልዩ ሃይል ላይ የታቀደው ሴራ እጅግ በጣም ከባድ በመሆኑየልዩ ሃይል አመራር እና አባላት ይሄን ጉዳይ ብስለት በተሞላበት መልኩ በመያዝ ታሪካዊ ሀላፊነታቸውን መወጣት እንዳለባቸውም ተገልጿል። በዚሁ ምክንያት ከባህር ዳር ጎንደር ዛሬ ከጧት ጀምሮ ትራንስፖርት ተቋርጦ ውሏል:: የአማራ ልዩ ሀይል ከተለያዩ ግንባሮች በክልሉ መንግስት በቂ ድጋፎች እየተደረገላቸው ባለመሆኑ ሰላም የማስከበር ስራ አንሰራም በማለት ለክልሉ መንግስት ቅሬታ ለማቅረብ ወደ ባህር ዳር እየተጓዙ ባለበት ወቅት አዲስ ዘመን አካባቢ ከመንግስት አካላት በቀረበላቸው ጉዳዩን በውይይት እንፍታው የሚል ጥያቄ መሰረት ውይይት እያካሄዱ በመሆኑ የትራንስፖርት አገልግሎት እንደተቋረጠ የአዲስ ዘመን ከተማ ብልጽግና ሀላፊ አቶ ምስጋናው ማስረሻ ለአሻራ ሚዲያገልጸዋል:: ሀላፊው ለትራንስፖርት መቋረጡ በምክንያትነት ያነሱት ለቅሬታ ከመጡ የልዩ ሃይል አባላት ጋር የሚደረገው ውይይት አስፓልት ላይ በመሆኑ ነው የሚል ምላሽ ሰጠዋል:: ውይይቱ ለሁለት ቀን ያክል አስፓልት ላይ እየተካሄድ መሆኑን በመግለጽ በማህበራዊ ሚዲያ የሚናፈሰው ተኩስ ተከፈተ የሚባለው ወሬ ውሸት ነው ሲሉም ተናግረዋል :: ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- ቴሌግራም :- https://t.me/asharamedia24 Facebook :- https://www.facebook.com/asharamedia24 youtube :- https://www.youtube.com/channel/UChir2nIy58hlLQRYyHIQeHA

Source: Link to the Post

Leave a Reply