የአማራ ልዩ ኃይል አባላት በሸዋሮቢት ከተማ በመንገድ ላይ ሲንቀሳቀስ የነበረ ወጣትን ተኩሰው አቆሰሉ፤ የቆሰለውን ፋኖ ታደለ ወርቁን ጨምሮ 3 ፋኖዎችንም ከፖሊስ ጋር በመሆን አስረዋል። አማራ…

የአማራ ልዩ ኃይል አባላት በሸዋሮቢት ከተማ በመንገድ ላይ ሲንቀሳቀስ የነበረ ወጣትን ተኩሰው አቆሰሉ፤ የቆሰለውን ፋኖ ታደለ ወርቁን ጨምሮ 3 ፋኖዎችንም ከፖሊስ ጋር በመሆን አስረዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ነሃሴ 29 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ነሃሴ 28/2014 ከምሽቱ 2 ሰዓት አካባቢ ከሸዋሮቢት ከተማ ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) የደወሉ ነዋሪዎች እንደሚሉት የአማራ ልዩ ኃይል መሃል ከተማ ላይ በተገኘው ወጣት ጌታቸው ጋሻው ላይ በሽጉጥ አነጣጥረው በመተኮስ በከባድ አቁስለውታል። የኩሪ በረት/የራሳ አካባቢ ልጅ የሆነው ወጣት ጌታቸው ጋሻውን በሽጉጥ ግንባሩን ለመምታት በማሰብ የተኮሱት ጥይት አገጩን ስላገኘው በከባድ መቁሰሉን ከሸዋሮቢት የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ወጣት ጌታቸው ወደ ይፋት ሆስፒታል የህክምና ትብብር እየተደረገለት መሆኑ ተገልጧል። ወጣት ጌታቸው የፋኖዎች የቅርብ ጓደኛ መሆኑም ተነግሯል። ነሃሴ 27/2014 ምሽት ላይ ልዩ ኃይል እና ፖሊስ በአራት የይፋት ፋኖ አመራሮች ላይ በቡድን መሳሪያ የታገዘ ተኩስ በመክፈት 3 ሲያቆስሉ፣ 3 ማሰራቸው ይታወቃል። በተመሳሳይ ነሃሴ 28/2014 ረፋድ ላይ ልዩ ኃይሉ አሁንም በፋኖዎች ላይ ተኩስ መክፈቱን ተከትሎ እዮብ ለማ የተባለ የአማራ ፋኖ በይፋት አባልን ሲያቆስሉ ከልዩ ኃይሎችም የሞተ እና የቆሰለ መኖሩ ተሰምቷል። ከአማራ ፋኖ በይፋት አባላት ቆስለው በህክምና ላይ የሚገኙትም:_ 1) እዮብ ለማ፣ 2) ዮሃንስ እና 3) ታደለ ወርቁ ናቸው። በዘሁኑ ሰዓት በሸዋሮቢት ፖሊስ ጣቢያ በእስር ላይ የሚገኙ የአማራ ፋኖ በይፋት አመራሮችም:_ 1) ታደለ ወርቁ (በመጠኑ የቆሰለ ቢሆንም ወደ እስር ቤት ተወስዷል) 2) አማኑኤል እና 3) እንዳለ አራጋው ናቸው። ከእያቅጣጫው የጋራ ጠላት ያለበት ኃይል በጋራ ተናቦ መመከት ሲገባው በአንዳንድ ከፋፋይ ካድሪዎች ትዕዛዝ በመነሳት እርስ በርስ ለመጋጨት አልሞ መንቀሳቀስ በዘላቂነት ለማንም የማይጠቅም ነውረኛ ተግባር ነውና በአስቸኳይ መስተካከል እንዳለበት ብዙዎች ይናገራሉ። የተፈጠረውን ችግር በሀገር ሽማግሌዎችና በሀይማኖት አባቶች ጣልቃገብነት ለመፍታት ጥረት እየተደረገ መሆኑን የመረጃ ምንጮች ነግረውናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply