የአማራ ልዩ ኃይል ከከሚሴ እንዲወጣ መደረጉ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 19 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በጀብውሃ፣ በጀጀባ፣ በመንተኬ ሸረፋ፣ በሰ…

የአማራ ልዩ ኃይል ከከሚሴ እንዲወጣ መደረጉ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 19 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በጀብውሃ፣ በጀጀባ፣ በመንተኬ ሸረፋ፣ በሰንበቴ፣ በአጣዬ እና በዙሪያው፣ በሸዋሮቢት ዙጢ እንዲሁም በጨፋ ሮቢት በታቀደ እና በተጠና መልኩ በቡድን መሳሪያ በመታገዝ ከተሽከርካሪ ላይ ሳይቀር በአሸባሪ እና ወራሪ ኦነጋዊያን ጥቃት የተፈጸመበት የአማራ ልዩ ኃይል በአማራ ክልል ከልዩ ዞኑ ከኪሚሴ እንዲወጣ ተደርጓል። በልዩ ዞኑ ማህበረሰብ እና በመስተዳድሩ ልዩ ኃይል ይውጣ በሚል ጥያቄ መቅረቡን ተከትሎ በአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አማካኝነት ስለመፈጸሙ በአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ምንጮች ተጠቁሟል። የአማራ ልዩ ኃይል የአማራ ክልል አካል ከሆነው ከከሚሴ እንዲወጣ የመደረጉ አላማ እና ፍላጎት በግልጽ ባይነገርም አካባቢውን በአሸባሪ ኦነጋዊያን ሙሉ በሙሉ ለማስያዝ ይሆናሉ ብዙዎች ናቸው። በተመሳሳይ ጥር 18/2015 በበሰሜን ሸዋ አንጾኪያ ገምዛ መኮይ አካባቢ ወራሪ ቡድኑ የትንኮሳ የተኩስ ሙከራ ያደረገ ቢሆንም በወትሮ ዝግጁ ጀግና ፋኖዎች የተነሳ እንደፈለገ ለመውረር እና ለመዝረፍ አልተሳካለትም ተብሏል። በአጣዬ እና ዙሪያው የመንግስት የጸጥታ አካላት እንቅስቃሴ በመኖሩ በጦርነቱ እና በስጋት ከሸሹ ወገኖች መካከል አንዳንዶች ሲመለሱ መስተዋሉም ተነግሯል። ከሸዋሮቢት በቅርብ ርቀት በሚገኘው ዙጢ፣ በጀብውሃ፣ በመንተኬ ሸረፋ፣ በአጣዬ እና አካባቢው በርካታ ቤቶች እና ሀብት ንብረት በኦሮሞ ልዩ ዞን እና በኦሮሚያ ክልል መንግስት አካላት ጭምር በሚደገፉ አሸባሪ እና ወራሪ ኦነጋዊያን እንዲወድም ተደርጓል። በዙጢ አካባቢ ለወረራ እና ለዝርፊያ ከመጡት መካከል በነበረው ራስን የመከላከል እርምጃ ዙጢ ላይ ከተገደሉት 6 የሚሆኑ ከወለጋ የመጡ ታጣቂዎች መሆናቸው ታውቋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply