You are currently viewing “የአማራ ሕዝብ ለትግል የተነሳው ለዘመናት የደረሰበትን አረመኔያዊ በደል ታግሶ ኖሮ ነው።” ሲል የአማራ ሕዝባዊ ኮሚቴ ገለፀ።                   ግንቦት 1/2015 ዓ.ም…

“የአማራ ሕዝብ ለትግል የተነሳው ለዘመናት የደረሰበትን አረመኔያዊ በደል ታግሶ ኖሮ ነው።” ሲል የአማራ ሕዝባዊ ኮሚቴ ገለፀ። ግንቦት 1/2015 ዓ.ም…

“የአማራ ሕዝብ ለትግል የተነሳው ለዘመናት የደረሰበትን አረመኔያዊ በደል ታግሶ ኖሮ ነው።” ሲል የአማራ ሕዝባዊ ኮሚቴ ገለፀ። ግንቦት 1/2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ከአማራ ሕዝባዊ ኮሚቴ የተሰጠ አስቸኳይ መግለጫ፦ የአማራ ሕዝብ “የለውጥ አመራር ነኝ” በሚለው የኦሮሞ ብልፅግና-መር አገዛዝ በደረሰበት ወደር የለሽ በደል ምክንያት ወደማይቀለበስ ሕዝባዊ ትግል ገብቷል። ይህ ትግል የአማራ ሕዝብ ሁሉ ትግል መሆኑን ኦሮሞ-መራሹ የብልፅግና መንግሥት ሊያውቀው ይገባል። በተጨማሪም የአማራ ሕዝብ ትግል የእኩልነት፣ የዴሞክራሲና ሰብዓዊ ክብሩን የማስመለስ እንጅ ሀገር የማፍረስ አለመሆኑን መንግስሥት ቢያውቀውም ደግመን ማስረገጥ እንፈልጋለን። የአማራ ሕዝብ ለትግል የተነሳው ለዘመናት የደረሰበትን አረመኔያዊ በደል ታግሶ ኖሮ ነው። አሁን ላይ ያለው በደል ግን ከትዕግስት በላይ የሆነ በመሆኑ አማራው ታግሎ መብቱን ማስከበር፣ ሃገሩን ማስመለስ እንዳለበት ተግባብቷል። ይህ በአማራ ሕዝብ ዘንድ የተደረሰበትን የወል መግባባት የኦሮሞ ብልፅግና ፓርቲ የሚዝውረው መንግሥት ሊያውቅ ይገባል። በአማራ ሕዝብ ትግል ላይ የመጣውን እምርታ ተረድቶ መንግሥት “በድሮ በሬ” ማረሱን ካላቆመ ሃገራችን መታመሷ ይቀጥላል። አሁን ላይ የአማራ ሕዝብ የጀመረው ትግል ታጋዮችን በማሰርም ሆነ በመግደል የሚቆም አይደለም፤ በሽምግልና ስምም ሊቀለበስ የሚችል አይደለም። የአማራን ሕዝብ ትግል ሃገርን ወደሚጠቅም ሁኔታ ለመቀየርና ለመደራደር ከተፈለገ የኦሮሞ ብልፅግና-መራሹ መንግሥት የሚከተሉትን ቅድመ-ሁኔታዎችን ማሟላት አለበት፦ በአዲስ አበባና በአማራ ክልል የታሰሩ የአማራ ተወላጆችን፣ ምሁራንንና ጋዜጠኞችን በአስቸኳይ መፍታት፣ ክሳቸውን ማቋረጥ፣ በእነዚህ የታሰሩ የአማራ ተቆርቋሪዎች ላይ የተነዛውን የሃሰት ፕሮፓጋንዳና የውሸት ክስ ክሱ በተነዛባቸው የመንግሥት ሚዲያዎች እንዲስተካከል ማድረግ፣ የክልሎችን ህገ-መንግሥታዊ የሉአላዊነት መብት በመጣስ አማራ ክልል በገፍ ገብቶ በንፁሃን ላይ እየተኮሰ የሚገኘው በኦሮሞ ጄኔራሎች የሚዘወረው መከላከያ ሰራዊት ያለምንም ቅድመ-ሁኔታ ከአማራ ክልል ለቆ እንዲወጣ፤ ላጠፋው ነፍስ ካሣ እንዲከፍል፣ ኢ-ህገመንግሥታዊ በሆነ ሁኔታ በአማራ ክልል ፖለቲካ ውስጥ ጣልቃ ገብቶ የክልሉን ሁኔታ ወደባሰ ምስቅልቅል የወሰደው የመከላከያ ሠራዊት አዛዦች ጣልቃ ገብነት ህገወጥ መሆኑ ታውቆ ይቅርታ እንዲጠየቅበት፣ የመከላከያ ሠራዊትን የሚመሩ የኦሮሞ ጄኔራሎች በአማራ ፋኖዎች፣ የልዩ ሃይል አባላት ላይ የሚነዙትን የጦረኝነት ክስ በአስቸኳይ እንዲያቆሙ፣ የብልፅግናው መንግሥት የህልውና ትግል የሚያደርገውን የአማራ ታጋይ፣ ምሁር፣ ልሂቅና ፋኖ በፅንፈኝነት ለመክሰስና በዓለም አቀፍም ሆነ በሀገር አቀፍ ፖለቲካው ውስጥ እንደጦረኛ፣ ትምክህተኛና የበላይነት ፈላጊ ጠብ አጫሪ አድርጎ ለማሳጣት የሚደረገውን እኩይ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ በአስቸኳይ እንዲያቆም፣ የአማራ ሕዝብ ለዘመናት የደም ዋጋ የከፈለባቸውን ታሪካዊ ግዛቶቹን ለወያኔ አሳልፎ ለመስጠት በመንግሥት በኩል እየተደረገ ያለው ሩጫ በፍጥነት እንዲቆም። እነዚህን ግዛቶች ለወያኔ ለመስጠት ሲባል በአማራ ሕዝብ ላይ የተከፈተው ጦርነት ሀገሪቷን ወደባሰ የጦርነትና መተላለቅ አዘቅት እንደሚወስዳት ታውቆ ግዛቶቹ ለባለቤቱ የአማራ ሕዝብ እንደመለሱ በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ የአማራና የትግራይ ፖለቲከኞችን ወደማነጋገር በአስቸኳይ እንዲገባ። ይህ ሲሆን አማራው በእውነተኛ ወኪሎቹ መወከል አለበት፣ የብልፅግናው መንግሥት በአሁኑ ወቅት በሽምግልና ስም የአማራ ሕዝብን ትግል ለመቀልበስ የሚደረገውን ከንቱ ድካም አቁሞ በምትኩ ያሰራቸውን እውነተኛ የአማራ ሕዝብ ታጋዮችን ከእስር ፈትቶ ከእነሱ ጋር በመነጋገር የአማራን ሕዝብ ጥያቄዎች በአስቸኳይ እንዲመልስ፣ የአማራ ሕዝብ ህገመንግስታዊ መብቱን ተጠቅሞ የሚያደርጋቸውን እንደሰላማዊ ሰልፍ፣ የቤት መቀመጥና የስራ ማቆም አድማና መንግሥት እንደሽብርተኝነትና ነውጠኝነት ቆጥሮ ታጋዮችን ማሳደዱና የአማራ ሕዝብን በፅንፈኝነት መፈረጁን በአስቸኳይ እንዲያቆም፣ ሁሉም ክልሎች የታጠቁ ሃይሎቻቸውን ይዘው ባሉበት ሁኔታ የአማራ ልዩ ሃይል ላይ የተከፈተው ትጥቅ የማስፈታት ጥድፊያ የአማራን ሕዝብ በማንነቱ ለይቶ የማጥቃት አካል መሆኑ ከማንም የተሰወረ ስላልሆነ፣ በዚሁ አማራን ለይቶ በማጥቃቱ የመንግሥት አደገኛ አካሄድ ለአሰቃቂ ሞት የተዳረጉ ወደ 41 የሚጠጉ የአማራ ልዩ ሃይል አባላት ቤተሰቦች የህይወትና የሞራል ካሣ በአስቸኳይ እንዲከፈል። የአማራ ሕዝባዊ ኮሚቴ ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ :-Youtube:-https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:-https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply