የአማራ ሕዝብ ላለፉት 30 እና 40 አመታት ብዙ ማይካድራዎችን አይቷል ሲሉ ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ ተናገሩ አሻራ ሚዲያ 04/10/13/ዓ.ም ባህር ዳር የአማራ ሕዝብ ላለፉት 30 እና 40 አመታት…

የአማራ ሕዝብ ላለፉት 30 እና 40 አመታት ብዙ ማይካድራዎችን አይቷል ሲሉ ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ ተናገሩ አሻራ ሚዲያ 04/10/13/ዓ.ም ባህር ዳር የአማራ ሕዝብ ላለፉት 30 እና 40 አመታት…

የአማራ ሕዝብ ላለፉት 30 እና 40 አመታት ብዙ ማይካድራዎችን አይቷል ሲሉ ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ ተናገሩ አሻራ ሚዲያ 04/10/13/ዓ.ም ባህር ዳር የአማራ ሕዝብ ላለፉት 30 እና 40 አመታት ብዙ ማይካድራዎችን አይቷል ያሉት ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ እኛ የማይካድራ ሰማዕታት ባለ እዳዎች ነን ብለዋል፡፡ በመሆኑም የማይካድራን አደባባይ የማይካድራ ሰማዕታት አደባባይ ብለን ሰይመናል ያሉ ሲሆን በቀጣይም የሰማዕታቱን ሀውልት ከዚሁ ማይካድራ ላይ አናቆማለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡ በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ በካድራ ወንዝ ማይካድራ ከተማ የአሸባሪው ሕወሃትን ግፍ የሚያወግዝና የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚቃወም ሰልፍ ተካሂዷል። በሰልፉ ላይ መልእክት ያስተላለፉት የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ አስተዳደር ምክትል አስተዳዳሪና የሰላምና የሕዝብ ደኅንነት መምሪያ ኀላፊ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ በአሸባሪው ትህነግ የአገዛዝ ዘመን ብዙ ማይካድራዎች ማየቱን ተናግረዋል። አሸባሪው ትህነግ በመጨረሻው ጊዜ በማይካድራ ነዋሪዎች ላይ አረመኔያዊ ተግባር ፈፅሞ ማለፉን አስታውሰዋል። የማይካድራ ጭፍጨፋ በመላ ኢትዮጵያውያን ልብ ሲታወስ ይኖራልም ብለዋል። ሀገር ያቀና፣ ተቻችሎ መኖር የሚችል ታላቅ ሕዝብ ለ30 ዓመታት ግፍ ሲፈጸምበት መኖሩንም ተናግረዋል። የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ከብዙ ትግል በኋላ ነፃነቱን አግኝቷል ያሉት ኮሎኔል ደመቀ አሜሪካና መሰሎቿ አሸባሪን ቡድን መልሶ ወደ ስልጣን ለማምጣት የአማራን ሕዝብ ግፈኛና ወራሪ አስመስለው፣ የአማራ ግፍ ሳይታያቸው ጫና ለመፍጠር መሞከራቸውን ማስተካከል ይገባቸዋልም ብለዋል። የትህነግ ኀይል አሸባሪነትን የጀመረው ዛሬ ሳይሆን ሲነሳ ጀምሮ እንደነበር ዓለም ያውቃልም ብለዋል ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ። የኢትዮጵያ በጎ ገፅታ የማይታያቸው ጠላቶች አሸባሪ እየደገፉ ነው፤ ከተሳሳተ አካሄዳቸው በመመለስ የወልቃይት ጠገዴን ግፍ በትክክል ሊረዱት ይገባል ነው ያሉት። አማራ የራሱን አይሰጥም የሰውም አይፈልግም፣ ትናንትናም የሰው አልወሰድንም፣ የአማራ ግፍና በደል ሊታይ ይገባል፣ ዓለም ፍትሐዊ ከሆነች በግፍ ከተገደሉ ወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ጎን ትሁን፤ ከዚህ በተረፈ የማንንም ጣልቃ ገብነት አንቀበልም” ብለዋል፡፡ ሕዝቡ ላይ ሽብር በመፍጠር ወደ ልማት እንዳይገባ የሚሠሩትን ማስቆም እንደሚገባም አስገንዝበዋል። ወቅቱ የእርሻ እና የልማት በመሆኑ ሕዝቡ ወደ ልማት እንዲገባም ጠይቀዋል። ሙሉ መረጃውን አሻራ ዩቲዩብ ቻናላችን ላይ ይጠብቁ!!

Source: Link to the Post

Leave a Reply